text
stringlengths
4
267
አንተ ደግሞ አመሻሹ ላይ ወይም ከመተኛትህ በፊት ታሰላስል ይሆናል።
አንዳንዶች ጠዋት እንዲሁም ማታ ከመተኛታቸው በፊት መጽሐፍ ቅዱስ ያነብባሉ።
በመሆኑም ቀንም ሆነ ሌሊት በሌላ አባባል አዘውትረው የአምላክን ቃል ያነብባሉ ሊባል ይችላል።
ዋናው ቁም ነገር፣ በአምላክ ቃል ላይ ለማሰላሰል እምብዛም አስፈላጊ ካልሆኑ ነገሮች ላይ ጊዜ መግዛት መቻላችን ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ በአምላክ ቃል ላይ የሚያሰላስሉና የተማሩትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚጥሩ ሰዎች በረከት እንደሚያገኙ ደጋግሞ ይናገራል።
ኢየሱስ ደስተኞችስ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው! በማለት ተናግሯል።
ከሁሉም በላይ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ በየዕለቱ ማሰላሰላችን አእምሯችንን ድንቅ አድርጎ ለፈጠረው አምላክ ክብር ያመጣል፤ እሱም በአሁኑ ጊዜ ደስተኛ እንድንሆን ያደርገናል፤ ወደፊት ደግሞ ጽድቅ በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የዘላለም ሕይወት በመስጠት ይባርከናል።
ይሖዋ በዛሬው ጊዜ ሰዎችን እየረዳ እንደሆነ እንድናምን የሚያደርገን አጥጋቢ ምክንያት አለን።
መንፈሳዊ እርዳታ ለማግኘት ጸልየው ጸሎታቸው መልስ ስላገኘ ግለሰቦች የሚገልጹ ተሞክሮዎችን ብዙ ጊዜ እንሰማለን።
አላን የሚባል አንድ ወንድም በፊሊፒንስ በምትገኝ አንዲት ትንሽ ደሴት ላይ ከቤት ወደ ቤት እያገለገለ ሳለ ያገኛት ሴት ድንገት ማልቀስ ጀመረች።
እንዲህ ብሏል፦ ሴትየዋ የዚያን ዕለት ጠዋት ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መገናኘት እንድትችል ወደ ይሖዋ ጸልያ ነበር።
አምላክ ለጸሎቷ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠቱ ስሜቷ በጥልቅ ተነክቷል።
ይህች ሴት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሕይወቷን ለይሖዋ ወስናለች።
ብዙ የአምላክ አገልጋዮች ከዚህ በፊት ከነበሯቸው እንደ ማጨስ፣ ዕፅ መውሰድ ወይም የብልግና ምስሎችን መመልከት ካሉ መጥፎ ልማዶች መላቀቅ እንዲችሉ አምላክ እንደረዳቸው በግልጽ ማየት ችለዋል።
አንዳንዶች በራሳቸው ጥረት ለማቆም በተደጋጋሚ ጊዜ እንደሞከሩና እንዳልተሳካላቸው ተናግረዋል።
ሆኖም እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ዘወር በማለታቸውና ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነ ኃይል ከእሱ በማግኘታቸው ድክመታቸውን ማሸነፍ ችለዋል።
የይሖዋ አገልጋዮች በመካከላቸው እውነተኛ ፍቅርና አንድነት መኖሩ የእውነተኛው ሃይማኖት ተከታዮች መሆናቸውን ያሳውቃል፤ ምክንያቱም ኢየሱስ እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ሰዎች ሁሉ ደቀ መዛሙርቴ እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ ብሏል።
ሐዋርያው ዮሐንስም እንዲህ ሲል ጽፏል፦ የአምላክ ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ በግልጽ ይታወቃሉ፦ በጽድቅ ጎዳና የማይመላለስ ሁሉ የአምላክ ወገን አይደለም፤ ወንድሙን የማይወድም የአምላክ ወገን አይደለም።
ከመጀመሪያ የሰማችሁት መልእክት እርስ በርሳችን መዋደድ አለብን የሚል ነውና።
የይሖዋ ምሥክሮች የክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች መሆናቸውን የሚያሳውቀው፣ ልዩ የሆነ አንድነት የሚያስገኝ ፍቅር ያላቸው መሆኑ ነው፤ ይሖዋ እነዚህን ሕዝቦች በመላው ምድር የመንግሥቱን ምሥራች ለማወጅ እየተጠቀመባቸው ነው።
ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ ኢየሱስን በራሱ ላይ እንዳይጨክን ይኸውም ራሱን ለሞት አሳልፎ እንዳይሰጥ የመከረው ለእሱ አስቦ ነው።
ይሁን እንጂ ኢየሱስ፣ ጴጥሮስ የተናገረው ነገር የተሳሳተ አመለካከት እንዳለው የሚጠቁም መሆኑን አስተውሏል።
ኢየሱስ ጴጥሮስንና ሌሎች ደቀ መዛሙርቱን ለመጥቀም ሲል ግልጽ ምክር ሰጥቷል፤ ለራስ መሳሳት ምን እንደሚያስከትል የተናገረ ከመሆኑም ሌላ የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ የሚያስገኘውን በረከት ጠቁሟል።
ጴጥሮስ ከዚህ ምክር ጥቅም እንዳገኘ ግልጽ ነው።
በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኘው ልጃችሁ በየትኛው አቅጣጫ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ለመረዳት የሚያስችል ማስተዋል እንዲሰጣችሁ ወደ ይሖዋ ጸልዩ።
ለምሳሌ የልጃችሁ እምነት እየተዳከመ እንደመጣ የሚጠቁሙ ነገሮች ምንድን ናቸው?
ደስታው እየጠፋ እንደሆነ፣ የእምነት ባልንጀሮቹን መተቸት እንደጀመረ ወይም ድብቅ እየሆነ እንደመጣ አስተውላችሁ ሊሆን ይችላል።
እነዚህ ነገሮች ከባድ ኃጢአት ፈጽሞ ሁለት ዓይነት ሕይወት እየመራ መሆኑን የሚጠቁሙ ናቸው ብላችሁ ለመደምደም አትቸኩሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህን ምልክቶች በቸልታ አትለፏቸው፤ ወይም በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኘው ልጃችሁ ራሱን ማግለሉ በዚህ ዕድሜ የሚያጋጥም የተለመደ ነገር እንደሆነ በማሰብ ሁኔታውን አቅልላችሁ አትመልከቱት።
የሰዎች ባሕልና ሃይማኖት ከቦታ ቦታ የሚለያይ በመሆኑ ለመናገር ተገቢ የሆነውን ጊዜ ስንመርጥ አስተዋዮች መሆን አለብን።
እንዲህ ማድረግ አስፈላጊ የሚሆንባቸው በርካታ ሁኔታዎች አሉ።
ለምሳሌ አንድ ሰው መልካም አስቦ የተናገረው ነገርም እንኳ ቅር ሊያሰኘን ይችላል።
የጉዳዩን ክብደት ለማጤንና ግለሰቡን ልናነጋግረው ይገባ እንደሆነ ለመወሰን ጊዜ ወስደን ማሰባችን አስተዋይነት ነው።
ቅር ያሰኘንን ሰው ለማነጋገር ከወሰንን፣ በተበሳጨንበትና ነገሮችን ሳናመዛዝን ልንናገር በምንችልበት ወቅት መናገራችን ጥበብ አይሆንም።
በተመሳሳይም ለማያምኑ ዘመዶቻችን እውነትን ስንነግራቸው አስተዋይ መሆን አለብን።
ይሖዋን እንዲያውቁ እንደምንፈልግ ግልጽ ነው፤ ሆኖም ትዕግሥተኛ መሆንና ነገሮችን ማመዛዘን ይኖርብናል።
በተገቢው ጊዜ ተገቢውን ቃል መናገራችን ልባቸው እንዲነካ ሊያደርግ ይችላል።
ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር አብረን ስንሠራ ይበልጥ የምንቀራረብ ከመሆኑም ሌላ ስለ እነሱ በደንብ ማወቅ እንችላለን።
ምን ማከናወን እንደሚፈልጉ ብቻ ሳይሆን ይህን የሚያደርጉት እንዴት እንደሆነም ጭምር መረዳት እንችላለን።
ኢየሱስ ከይሖዋ ጋር በቢሊዮን ለሚቆጠሩ ዓመታት አብሮ ሳይሠራ አይቀርም፤ በመሆኑም አንዳቸው ለሌላው በጣም ጥልቅ ፍቅር አዳብረዋል፤ እንዲሁም ፈጽሞ ሊበጠስ የማይችል ጠንካራ ወዳጅነት መሥርተዋል።
በመካከላቸው አስደናቂ አንድነት ያለ ሲሆን ምንጊዜም የሚሠሩት ፍጹም ስምም ሆነው ነው።
ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱን እንዲጠብቃቸው ወደ ይሖዋ ጸልዮአል።
እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው?
እኛ አንድ እንደሆንን ሁሉ እነሱም አንድ እንዲሆኑ በማለት ተናግሯል።
ከአምላክ መሥፈርቶች ጋር ተስማምተን ስንኖርና በስብከቱ ሥራ ስንካፈል የይሖዋን አስደናቂ ባሕርያት መረዳት እንችላለን።
በእሱ መታመንም ሆነ መመሪያውን መከተል የጥበብ እርምጃ የሆነበትን ምክንያት እንገነዘባለን።
ወደ አምላክ ስንቀርብ እሱም ወደ እኛ ይቀርባል።
በተጨማሪም ከመንፈሳዊ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር እንቀራረባለን፤ ምክንያቱም የሚያጋጥሙን ችግሮች፣ አስደሳች ነገሮች እንዲሁም ግቦቻችን ተመሳሳይ ናቸው።
ቅዱሳን መጻሕፍትን ስንመረምር መንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸው በርካታ የእምነት ሰዎችን እናገኛለን፤ ያም ሆኖ እነዚህ ሰዎች በሰማይ የመኖር ተስፋ አልነበራቸውም።
እንዲህ ካሉት ሰዎች መካከል መጥምቁ ዮሐንስ አንዱ ነው።
ኢየሱስ መጥምቁ ዮሐንስን በእጅጉ ያደነቀው ቢሆንም ወደ መንግሥተ ሰማያት እንደማይገባ ተናግሯል።
ዳዊትም የይሖዋን መንፈስ አግኝቶ ነበር።
ዳዊት ጥልቅ መንፈሳዊ እውቀት ያለው ሰው ከመሆኑም ባሻገር አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በመንፈስ መሪነት ጽፏል።
ያም ሆኖ ጴጥሮስ በጴንጤቆስጤ ዕለት ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣም ብሏል።
መንፈስ ቅዱስ በእነዚህ ሰዎች በመጠቀም ታላቅ ሥራ አከናውኗል፤ ሆኖም በሰማይ ሕይወት ለማግኘት መመረጣቸውን የሚያሳየውን ልዩ ምሥክርነት አልሰጣቸውም።
ይህ መሆኑ ግን ብቃት ጎድሏቸዋል ወይም እንከን አለባቸው ማለት አይደለም።
ከዚህ ይልቅ ይሖዋ ከሞት አስነስቶ በምድር ላይ ለዘላለም እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል ማለት ነው።
ለምን?
ጳውሎስ የሰውን አካል እንደ ምሳሌ በመጥቀስ የጉባኤው ራስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ አመራር ሥር አንድነት ሊኖረን እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጿል።
ሐዋርያው አስፈላጊ የሆነውን ነገር በሚያሟላው በእያንዳንዱ መገጣጠሚያ አማካኝነት መተባበር እንደሚያስፈልግ ተናግሯል።
ልጅ አዋቂ፣ ብርቱ ደካማ ሳይል ሁላችንም ለጉባኤው አንድነትና መንፈሳዊነት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት የምንችለው እንዴት ነው?
ቁልፉ ነገር ኢየሱስ በጉባኤ ውስጥ አመራር እንዲሰጡ የሾማቸውን ሽማግሌዎች ማክበርና ለእነሱ መገዛት ነው።
እርግጥ እንዲህ ማድረግ ሁልጊዜ ቀላል ላይሆን ይችላል።
ነገር ግን አምላክ እንደሚረዳን እርግጠኛ በመሆን አመራሩን መጠየቅ እንችላለን።
ቅዱስ መንፈሱ የጉባኤውን ዝግጅቶች በሙሉ ልባችን መደገፍ እንድንችል ይረዳናል።
ስለዚህ የተሰጠንን አመራር መከተል ከባድ በሚሆንብን ጊዜ በትሕትና መንፈስ ተባባሪ መሆናችን ለጉባኤው አንድነት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ማሰብ ይኖርብናል።
በተጨማሪም በዚህ ረገድ መተባበራችን ሁላችንም በፍቅር እንድናድግ ሊረዳን ይችላል።
ይሖዋ አንዳንድ ጊዜ ለምንጠይቀው ነገር አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጠን ለምንድን ነው?
ይሖዋ ከእሱ ጋር የመሠረትነውን ዝምድና በአባትና በልጅ መካከል ካለው ግንኙነት ጋር እንዳመሳሰለው አስታውስ።
አንድ ልጅ፣ የሚጠይቀውን ነገር ሁሉ ወላጆቹ እንዲያደርጉለት ወይም ፍላጎቱን በሙሉ ወዲያውኑ እንዲያሟሉለት መጠበቁ ተገቢ አይሆንም።
ልጁ አንዳንድ ነገሮችን የሚጠይቀው በስሜታዊነት በመሆኑ ብዙም ሳይቆይ ይረሳዋል።
የሚጠይቃቸውን ሌሎች ነገሮች ለማድረግ ደግሞ ተገቢው ጊዜ እስኪደርስ መጠበቅ ያስፈልግ ይሆናል።
አንዳንድ ጊዜ ልጁ የሚፈልገው ነገር እሱንም ሆነ ከእሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ሰዎች የሚጎዳ ሊሆን ይችላል።
በተጨማሪም ወላጆች ልጁ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ካደረጉለት ግንኙነታቸው የጌታና የባሪያ ዓይነት ይሆንና ልጁ አዛዥ ሆኖ ቁጭ ይላል።
በተመሳሳይም ይሖዋ ለጸሎታችን መልስ ከመስጠቱ በፊት የተወሰነ ጊዜ እንዲያልፍ የሚያደርገው ለእኛ ጥቅም ሲል ሊሆን ይችላል።
ይሖዋ ጥበበኛ ፈጣሪያችን፣ አፍቃሪ ጌታችንና ሰማያዊ አባታችን እንደ መሆኑ መጠን ይህን የማድረግ መብት አለው።
የጠየቅነውን ሁሉ ወዲያውኑ የሚያደርግልን ከሆነ በመካከላችን ያለው ግንኙነት ትክክለኛውን አካሄድ የጠበቀ አይሆንም።
አንዳንዶች ራስን በመወሰንና በመጠመቅ መካከል ያለው ልዩነት በግልጽ ላይገባቸው ይችላል።
ለምሳሌ ያህል፣ አንዳንድ ወጣቶች ራሳቸውን ለይሖዋ እንደወሰኑ፣ ለመጠመቅ ግን ዝግጁ እንዳልሆኑ ይናገራሉ።
ይህ አባባል ያስኬዳል?
ራስን መወሰን ማለት ይሖዋን ለዘላለም እንደምታገለግለው በጸሎት መንገር ማለት ነው።
አንድ ሰው ሲጠመቅ፣ ራሱን መወሰኑን ሌሎች እንዲያውቁ ያደርጋል።
በመሆኑም ጥምቀት፣ ለይሖዋ ባቀረብከው የግል ጸሎት አማካኝነት ቀደም ሲል ራስህን መወሰንህን ሰዎች እንዲያውቁ ማድረግ ማለት ነው።
ከመጠመቅህ በፊት ራስን መወሰን ምን ትርጉም እንዳለው በሚገባ መረዳት ይኖርብሃል።
በቀላል አነጋገር፣ ራስህን ለይሖዋ ስትወስን ሕይወትህ የአንተ ንብረት መሆኑ ያበቃል ማለት ነው።
በሕይወትህ ውስጥ የይሖዋን ፈቃድ ከምንም ነገር በላይ እንደምታስቀድም በመግለጽ ለእሱ ቃል ትገባለህ።
መቼም ቢሆን ቃል ስትገባ ጉዳዩን አክብደህ ማየት ይኖርብሃል፤ ይህ ከሆነ ታዲያ ለይሖዋ አምላክ የምትገባውን ቃል እጅግ አክብደህ ልታየው አይገባም?—⁠፤
ኃላፊነት ያለው አንድ ሰው ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲፈጽምብን ለአምላክ ያለን ታማኝነት ሊፈተን ይችላል።
ዮናታን እንዲህ ያለ ተፈታታኝ ሁኔታ አጋጥሞት ሊሆን ይችላል።
አምላክ የቀባው ንጉሥ ሳኦል፣ ልጁ ከዳዊት ጋር ጓደኝነት እንደመሠረተ ቢገነዘብም ይህን ያደረገው ለምን እንደሆነ አልገባውም ነበር።
በመሆኑም ሳኦል ዮናታንን ተቆጥቶ ኃይለ ቃል በመናገር አዋረደው።
ያም ሆኖ ዮናታን አጸፋውን አልመለሰም።
ለአምላክም ሆነ ከጊዜ በኋላ የእስራኤል ንጉሥ ለሚሆነው ለዳዊት ያለውን ታማኝነት አላጓደለም።
በዛሬው ጊዜ በይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤ ውስጥ ተገቢ ያልሆነ ነገር ሊፈጸምብን የሚችልበት አጋጣሚ በጣም ጠባብ ነው።
ሆኖም በመካከላችን ሆነው አመራር የሚሰጡን ወንድሞች ፍጹም ባለመሆናቸው፣ የምናደርገውን ነገር በተሳሳተ መንገድ ሊረዱት ይችላሉ።
ሰዎች ተገቢ ያልሆነ ነገር በሚፈጽሙብን ወይም በተሳሳተ መንገድ በሚረዱን ጊዜም ለይሖዋ ታማኝ መሆናችንን እንቀጥል።
መልካሙ አመላችን እንዳይበላሽ ከፈለግን መጥፎ ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች የቅርብ ጓደኞቻችን ሊሆኑ አይገባም።
ይህም ሲባል መጥፎ ድርጊት የሚፈጽሙ የማያምኑ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ይሖዋን እናመልካለን እያሉ ሆን ብለው ሕጎቹን የሚጥሱ ሰዎችም ጓደኞቻችን መሆን የለባቸውም ማለት ነው።
ክርስቲያን ነን የሚሉ እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ከባድ ኃጢአት ፈጽመው ንስሐ የማይገቡ ከሆነ ከእነሱ ጋር ያለን ጓደኝነት መቋረጥ ይኖርበታል።
የአምላክን ሕግጋት ከማይታዘዙ ሰዎች ጋር ጓደኝነት ከመሠረትን በእነሱ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ስንል እነሱ የሚያደርጉትን ነገር ለመፈጸም ልንገፋፋ እንችላለን።