text
stringlengths
4
267
ለምሳሌ ያህል፣ የፆታ ብልግና የሚፈጽሙ ሰዎች የቅርብ ጓደኞቻችን ከሆኑ እኛም ብልግና ለመፈጸም ልንፈተን እንችላለን።
ራሳቸውን የወሰኑ አንዳንድ ክርስቲያኖች እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ደርሶባቸዋል፤ እንዲያውም አንዳንዶቹ ንስሐ ባለመግባታቸው ተወግደዋል።
እነዚህ ሰዎች ንስሐ ካልገቡ ጴጥሮስ የገለጸው ዓይነት ሁኔታ ይደርስባቸዋል።
በቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራም ወቅት ቤተሰቡ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ያደርጋል፤ ይህ ደግሞ ቤተሰቡ አንድነት እንዲኖረው ያስችላል።
በዚህ ወቅት ለመስክ አገልግሎት ልምምድ ማድረግ ሁሉም የቤተሰቡ አባላት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመስበክ የታጠቁ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል።
ከዚህም ሌላ የአንድ ቤተሰብ አባላት ለአምላክ ፍቅር ያላቸውና የእሱን ፈቃድ ማድረግ የሚፈልጉ እንደመሆናቸው መጠን ከአምላክ ቃል ባገኟቸው ሐሳቦች ላይ መወያየታቸው እርስ በርስ እንደሚያቀራርባቸው መገመት አያዳግትም።
ባለትዳሮች እርስ በርስ በመተባበር ለይሖዋ ውዳሴ ለማምጣት ምን ማድረግ ይችላሉ?
ሁለቱም ይሖዋን በታማኝነት ማገልገላቸው ደስታና አንድነት ያስገኝላቸዋል።
አብርሃምና ሣራ፣ ይስሐቅና ርብቃ እንዲሁም ሕልቃናና ሐና ለትዳር ጓደኛቸው ያላቸውን ፍቅር ገልጸዋል።
እኛም የእነሱን ምሳሌ መከተል ይኖርብናል።
ይህም ከትዳር ጓደኛችን ጋር አንድነት እንዲኖረን የሚያደርግ ከመሆኑም ሌላ በሰማይ ወዳለው አባታችን ይበልጥ እንድንቀርብ ያስችለናል።
ሰይጣን በቅቡዓን ቀሪዎችና በሌሎች በጎች ላይ ጦርነት አውጇል።
የዲያብሎስ ዓላማ በቀረው ጥቂት ጊዜ ውስጥ ከይሖዋ አገልጋዮች መካከል የቻለውን ያህል ብዙዎችን መዋጥ ነው።
ታዲያ ከሰይጣን ጋር በምናደርገው ውጊያ ማሸነፍ እንችላለን?
እንዴታ! መጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ እሱም ከእናንተ ይሸሻል ይላል።
ብዙዎች ሰይጣን አለ ብሎ ማመን ቂልነት እንደሆነ ይሰማቸዋል።
እነዚህ ሰዎች ሰይጣንና አጋንንቱ በልብ ወለድ መጻሕፍት፣ በአስፈሪ ፊልሞችና በቪዲዮ ጨዋታዎች ውስጥ የሚገኙ ምናብ የፈጠራቸው ገጸ ባሕርያት እንደሆኑ ያስባሉ።
የማመዛዘን ችሎታ ያለው ማንኛውም ሰው በክፉ መናፍስት እንደማያምን ይናገራሉ።
ታዲያ ሰይጣን፣ እሱና በዓይን የማይታዩት ግብረ አበሮቹ በተረት ዓለም ውስጥ የሚገኙ ባለታሪኮች ብቻ እንደሆኑ ተደርገው መቆጠራቸው ቅር የሚያሰኘው ይመስልሃል?
ይህ የሚያስከፋው አይመስልም! እንዲያውም ሰይጣን፣ እሱ መኖሩን የሚጠራጠሩ ሰዎችን አእምሮ ማሳወር ይቀለዋል።
ሰይጣን ሰዎችን ለማሳሳት ከሚጠቀምባቸው በርካታ ዘዴዎች አንዱ መንፈሳዊ ፍጥረታት የሉም የሚለውን ሐሳብ ማስፋፋት ነው።
ይሖዋ አቅማችን ምን ያህል እንደሆነ በደንብ ያውቃል።
ስለዚህ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች በራሳችን ኃይል እንድንወጣቸው አይጠብቅብንም፤ ከዚህ ይልቅ ልክ እንደ አባት እርዳታ ይሰጠናል።
እርግጥ ነው፣ አንዳንድ ጊዜ ፈተናውን መቋቋም የማንችልበት ደረጃ ላይ እንደደረስን ይሰማን ይሆናል።
ያም ቢሆን ይሖዋ፣ አገልጋዮቹ ከሚችሉት በላይ እንዲፈተኑ ፈጽሞ እንደማይፈቅድ ማረጋገጫ ሰጥቶናል።
እንዲያውም መውጫ መንገዱን ያዘጋጅልናል።
እንግዲያው ይሖዋ መሸከም የምንችለው ምን ያህል እንደሆነ በትክክል እንደሚያውቅ ለመተማመን የሚያበቃ ምክንያት አለን።
እርዳታ ለማግኘት ከጸለይን በኋላ ወዲያውኑ ምላሽ እንዳላገኘን ከተሰማን፣ እኛን ለመርዳት መቼ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት የሚያውቀውን አምላካችንን በትዕግሥት እንጠብቅ።
ይሖዋ እኛን ለመርዳት በጣም ስለሚጓጓ እሱም ቢሆን መታገሥ እንደሚያስፈልገው እናስታውስ።
ይሖዋ ሞገስ ሊያሳያችሁ በትዕግሥት ይጠባበቃል፤ ምሕረት ሊያሳያችሁም ይነሳል።
ይሖዋ የፍትሕ አምላክ ነውና።
ወደ 3,000 ከሚጠጉ ዓመታት በፊት ነቢዩ ኤልያስ፣ ኤልሳዕ የተባለን አንድ ወጣት አገልጋዩ እንዲሆን ጠይቆት ነበር።
ኤልሳዕም ግብዣውን ወዲያውኑ በመቀበል ዝቅ ተደርገው የሚታዩ ሥራዎችን በማከናወን በዕድሜ የገፋውን ነቢይ በታማኝነት ማገልገል ጀመረ።
ኤልሳዕ ለስድስት ዓመት ያህል ከሠለጠነ በኋላ ኤልያስ በእስራኤል ውስጥ የሚያከናውነው አገልግሎት ሊያበቃ እንደሆነ ተገነዘበ።
በዚህ ወቅት ኤልያስ በደንብ የሠለጠነው አገልጋዩ እሱን መከተሉን እንዲያቆም ጠየቀው፤ ኤልሳዕ ግን ከአስተማሪው ጋር የሚችለውን ያህል ረጅም ጊዜ ለማሳለፍ ቆርጦ ነበር።
ወጣት ወንድም ከሆንክ የኤልሳዕን ምሳሌ መከተል የምትችለው እንዴት ነው?
ዝቅ ተደርገው የሚቆጠሩ ሥራዎችን ጨምሮ ማንኛውም ኃላፊነት ሲሰጥህ ሥራውን ለማከናወን ፈጣን እርምጃ በመውሰድ ነው።
አስተማሪህን እንደ ጓደኛ ተመልከተው፤ እንዲሁም አንተን ለመርዳት የሚያደርገውን ጥረት እንደምታደንቅ ንገረው።
ከሁሉም በላይ ደግሞ የተሰጠህን ማንኛውንም ኃላፊነት በመወጣት ረገድ ታማኝ መሆንህን አሳይ።
ይህ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ይሖዋ በጉባኤ ውስጥ ተጨማሪ ኃላፊነት እንድትቀበል የሚፈልግ መሆኑን ሽማግሌዎቹ እርግጠኞች የሚሆኑት ታማኝና እምነት የሚጣልበት ሰው መሆንህን ስታስመሠክር ነው።
አምላካችን፣ ይሖዋ ብቻ ነው፤ በመሆኑም እሱን ብቻ ልናመልክ ይገባል።
እሱን እያመለክን ሌሎች አማልክትንም ማምለክ አሊያም ለእሱ በምናቀርበው አምልኮ ውስጥ የሐሰት ትምህርቶችንና ልማዶችን መቀላቀል አንችልም።
ይሖዋን በዓለም ላይ ካሉ በርካታ አማልክት አንዱ እንደሆነ አሊያም ከሌሎች አማልክት ሁሉ የበላይና ኃያል እንደሆነ ብቻ አድርገን ልንመለከተው አይገባም።
ሊመለክ የሚገባው ይሖዋ ብቻ ነው።
ይሖዋን ብቻ ማምለክ ከፈለግን በሕይወታችን ውስጥ ለእሱ ብቻ ልንሰጠው የሚገባውን ቦታ ሌላ ነገር እንዲወስደው ሌላው ቀርቶ እንዲጋራው እንኳ ልንፈቅድ አይገባም።
የይሖዋን ቦታ ሊይዙብን የሚችሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
ይሖዋ ለእስራኤላውያን አሥርቱን ትእዛዛት ሲሰጥ፣ ከእሱ በቀር ሌሎች አማልክትን እንዳያመልኩና ከማንኛውም ዓይነት የጣዖት አምልኮ እንዲርቁ አዟቸው ነበር።
በዘመናችን እንደ ጣዖት የሚመለኩ ብዙ ነገሮች አሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች እነዚህን ነገሮች እንደ ጣዖት እያመለኳቸው እንዳሉ እንኳ ላይገነዘቡ ይችላሉ።
የይሖዋ መመሪያዎች ግን አልተለወጡም፤ እሱ አሁንም አንድ ይሖዋ ነው።
ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ እስከ ሰባት ጊዜ ይቅር ማለት ይኖርበት እንደሆነ ሲጠይቀው ኢየሱስ እስከ 77 ጊዜ እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ ብቻ አልልህም ብሎ መለሰለት።
ኢየሱስ ይህን የተናገረው ምንጊዜም ይቅር ለማለት ፈቃደኞች መሆን እንዳለብን ለማጉላት ነው፤ ሌሎችን ይቅር ማለት የሚቀናን ዓይነት ሰዎች መሆን አለብን።
ሁላችንም ስህተት ስለምንሠራ እኛም ሌሎችን ልንበድል እንደምንችል ማስታወሳችን ጠቃሚ ነው።
የበደልነው ሰው እንዳለ ከተገነዘብን የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያ በመከተል ወደ ግለሰቡ ሄደን እርቅ ለማውረድ ጥረት ማድረግ አለብን።
ሌሎች የፈጸምነውን በደል ይቅር ሲሉን ደስ ይለናል፤ እኛም እነሱ ሲበድሉን እንዲሁ ማድረግ ይኖርብናል።
ሌሎችን ይቅር የምንል ከሆነ ይሖዋም ይቅር ይለናል።
በእርግጥም እኛ ስህተት ስንሠራ በሰማይ ያለው አባታችን ይቅር እንደሚለን ሁሉ እኛም ሌሎች ስህተት በሚሠሩበት ጊዜ ይቅር ባዮች ልንሆን ይገባል።
የሙሴ ወላጆች ስለ ይሖዋ እንዲሁም ዕብራውያንን ከባርነት ነፃ አውጥቶ ተስፋይቱን ምድር ለመስጠት ስላለው ዓላማ ሙሴን አስተምረውት መሆን አለበት።
ሙሴ፣ ይሖዋ ለእስራኤላውያን ቃል ስለገባው ነገር በጥልቅ ባሰላሰለ መጠን በአምላክ ላይ ያለው እምነትና ለእሱ ያለው ፍቅር እያደገ ሄዷል።
ፈሪሃ አምላክ እንዳላቸው ሌሎች ሰዎች ሁሉ እሱም፣ ይሖዋ የሰውን ዘር ከሞት ባርነት ነፃ የሚያወጣበትን ጊዜ በዓይነ ሕሊናው ተመልክቶ ሊሆን ይችላል።
ሙሴ፣ ለዕብራውያንም ሆነ ለመላው የሰው ዘር ርኅራኄ ያለውን አምላክ መውደዱ የሚያስገርም አይደለም።
በመላው ሕይወቱ ይሖዋን እንዲያገለግል የረዳው፣ እምነትና ፍቅር ያለው መሆኑ ነው።
ፈርዖን እንደሚገድለው ቢዝትበትም እንኳ እምነቱ፣ ለአምላክ ያለው ፍቅርና ምናልባትም ወደፊት የሚጠብቀውን ግሩም ሕይወት በአእምሮው መሳሉ ፈርዖንን በድፍረት ለመጋፈጥ አጠናክሮታል።
ኢየሱስ የመጀመሪያ ተአምሩን የፈጸመው በገሊላ በምትገኘው በቃና በተከናወነ የሠርግ ድግስ ላይ ነው።
በድግሱ ላይ ከተጠበቀው በላይ ብዙ እንግዶች መጥተው ሊሆን ይችላል።
ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን የወይን ጠጅ አለቀ።
ከተጠሩት እንግዶች መካከል የኢየሱስ እናት ማርያም ትገኝበታለች።
ማርያም ስለ ልጇ በተነገሩት ትንቢቶች ላይ ለዓመታት ስታሰላስል እንደቆየች ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም ልጇ የልዑሉ አምላክ ልጅ ተብሎ እንደሚጠራ ታውቃለች።
ማርያም፣ ኢየሱስ ለሰዎች እስካሁን ያላሳየው ኃይል እንዳለው ተማምና ይሆን?
ያም ሆነ ይህ ማርያምና ኢየሱስ ለአዲሶቹ ተጋቢዎች እንዳዘኑላቸውና ከእፍረት ሊታደጓቸው እንደፈለጉ አሳይተዋል።
ተጋቢዎቹ ለእንግዶች ጥሩ መስተንግዶ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ኢየሱስ ያውቃል።
በመሆኑም 380 ሊትር የሚሆነውን ውኃ በተአምር ወደ ጥሩ የወይን ጠጅ ለወጠው።
ኢየሱስ ይህን ተአምር የመፈጸም ግዴታ ነበረበት?
በፍጹም።
ይህን ያደረገው ለሰዎች ስለሚያስብና ለጋስ የሆነውን በሰማይ ያለውን አባቱን ምሳሌ ስለተከተለ ነው።
የክርስቲያን ጉባኤ አባል እንደመሆናችን መጠን ይህን ግብዣ በተሳካ ሁኔታ ማከናወን የምንችለው እንዴት ነው?
እንደ አንድ አካል ተገጣጥመንና እርስ በርስ ተስማምተን የምንሠራ ከሆነ ብቻ ነው።
የመንግሥቱን ምሥራች በተቻለን መጠን ለብዙ ሰዎች ማካፈል ከፈለግን የስብከቱን ሥራ በተደራጀ መልኩ ማከናወን ይኖርብናል።
ለዚህም ሲባል መመሪያዎች ይሰጡናል።
በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ጉባኤዎች አማካኝነት የሚሰጠን መመሪያ ጥረታችንን አስተባብረን እንድንሠራ ያስታጥቀናል።
የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ካደረግን በኋላ የመንግሥቱን መልእክት ለሰው ሁሉ ለመስበክ እንወጣለን።
በአንደበታችንም ሆነ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች በማበርከት ለሰዎች ምሥራቹን እናሰራጫለን።
አንተስ በልዩ የአገልግሎት ዘመቻዎች እንድንካፈል የሚሰጡንን መመሪያዎች ለመታዘዝ ጥረት ታደርጋለህ?
እንዲህ የምታደርግ ከሆነ ላይ የተገለጸው በሰማይ መካከል የሚበረው መልአክ የያዘውን መልእክት ከሚያስተጋቡት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ምሥራቹን በኅብረት ታውጃለህ።
አብርሃም ከእሱና ከይስሐቅ ጋር ከተጓዙት አገልጋዮቹ ከመለየቱ በፊት እናንተ አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ግን ወደዚያ በመሄድ በአምላክ ፊት ሰግደን ወደ እናንተ እንመለሳለን ብሏቸዋል።
አብርሃም ምን ማለቱ ነበር?
ይስሐቅን መሥዋዕት ሊያደርገው እንደሆነ እያወቀ ከይስሐቅ ጋር እንደሚመለስ ለአገልጋዮቹ ሲናገር እየዋሸ ነበር?
በፍጹም።
መጽሐፍ ቅዱስ አብርሃም ምን አስቦ እንደነበር ለማወቅ ይረዳናል።
አብርሃም አምላክ ይስሐቅን ከሞት እንኳ ሳይቀር ሊያስነሳው እንደሚችል ተገንዝቦ ነበር።
አዎ፣ አብርሃም በትንሣኤ ያምን ነበር።
እሱም ሆነ ሣራ በስተርጅናቸው ልጅ መውለድ እንዲችሉ ይሖዋ እንደረዳቸው ያውቃል።
አብርሃም በይሖዋ ዘንድ የማይቻል ነገር እንደሌለ ተገንዝቧል።
በመሆኑም በዚያ ፈታኝ ወቅት የሚፈጠረው ነገር ምንም ይሁን ምን፣ የሚወደውን ልጁን መልሶ እንደሚያገኘው እርግጠኛ ነበር፤ ምክንያቱም ይሖዋ ቃል የገባቸው ነገሮች በሙሉ የሚፈጸሙት በይስሐቅ በኩል ነው።
በእርግጥም አብርሃም በእምነታቸው የተነሳ እንደ ጻድቃን ለተቆጠሩት ሁሉ አባት ተብሎ መጠራቱ ምንም አያስደንቅም!
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ወጣቶችን ጨምሮ የይሖዋ ሕዝብ በአጠቃላይ ለአምላክ አገልግሎት በገዛ ፈቃዱ ራሱን ያቀርባል።
በመሆኑም ለመጠመቅ የሚያስብ አንድ ሰው ይህን ውሳኔ የሚያደርገው በራሱ ፍላጎት ተነሳስቶ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን አለበት።
ይህ ደግሞ ራስህን በጥሞና መመርመር ይጠይቅብህ ይሆናል።
ለምን?
በወጣትነት ዕድሜህ ያለህበት ሁኔታ ለየት ያለ ሊሆን ስለሚችል ነው።