text stringlengths 4 267 |
|---|
መቆንጠጫዎቹና መኮስተሪያዎቹ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ይሁኑ። |
ቁሳቁሶቹ ሁሉ ከአንድ ታላንት ንጹሕ ወርቅ ይሠሩ። |
በተራራው ላይ ተገልጦልህ ባየኸው ንድፍ መሠረት ተጠንቅቀህ ሥራቸው። |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“ከእስራኤል ሕዝብ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ። ከሰውም ሆነ ከእንስሳ መካከል በኩር የሆነው ወንድ ሁሉ የእኔ ነው።” |
ከዚያም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “ከግብፅ ከባርነት ቤት የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስቡ፤ ምክንያቱም ይሖዋ በኃያል ክንድ ከዚህ አውጥቷችኋል። በመሆኑም እርሾ የገባበት ምንም ነገር መበላት የለበትም። |
ይኸው በዛሬው ዕለት በአቢብ ወር ከዚህ ለቃችሁ እየወጣችሁ ነው። |
ይሖዋ ለአንተ ይሰጥህ ዘንድ ለቀድሞ አባቶችህ ወደማለላቸው ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር ይኸውም ወደ ከነአናውያን፣ ሂታውያን፣ አሞራውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ሲያስገባህ አንተ ደግሞ በዚህ ወር ይህን በዓል ማክበር አለብህ። |
ለሰባት ቀን ቂጣ ትበላለህ፤ በሰባተኛውም ቀን ለይሖዋ በዓል ይከበራል። |
በእነዚህ ሰባት ቀናት መበላት ያለበት እርሾ ያልገባበት ቂጣ ነው፤ በአንተ ዘንድ እርሾ የገባበት ምንም ነገር መገኘት የለበትም፤ በወሰንህም ውስጥ ሁሉ ምንም እርሾ መገኘት የለበትም። |
በዚያ ቀን ለልጅህ ‘ይህን የማደርገው ከግብፅ በወጣሁበት ጊዜ ይሖዋ ባደረገልኝ ነገር የተነሳ ነው’ ብለህ ንገረው። |
የይሖዋ ሕግ በአፍህ ላይ እንዲሆን ይህ በዓል በእጅህ ላይ እንደታሰረ ምልክትና በግንባርህ ላይ እንዳለ መታሰቢያ ሆኖ ያገለግልሃል፤ ምክንያቱም ይሖዋ በኃያል ክንድ ከግብፅ አውጥቶሃል። |
አንተም ይህን ደንብ በየዓመቱ በተወሰነለት ጊዜ አክብረው። |
“ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአንተም ሆነ ለቀድሞ አባቶችህ ወደማለላችሁ ወደ ከነአናውያን ምድር ሲያስገባህ |
በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ እንዲሁም የአንተ ከሆነው እንስሳ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለይሖዋ መስጠት አለብህ። ወንዶቹ ሁሉ የይሖዋ ናቸው። |
የእያንዳንዱን አህያ በኩር በበግ ዋጀው፤ የማትዋጀው ከሆነ ግን አንገቱን ስበረው። ከወንዶች ልጆችህ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ ልትዋጀው ይገባል። |
“ምናልባት ወደፊት ልጅህ ‘ይህን የምታደርገው ለምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ በኃያል ክንድ ከግብፅ ከባርነት ቤት አወጣን። |
ፈርዖን እኛን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆን ግትር አቋም በያዘ ጊዜ ይሖዋ ከሰው በኩር አንስቶ እስከ እንስሳ በኩር ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ ገደለ። በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለይሖዋ የምሠዋው እንዲሁም ከወንዶች ልጆቼ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ የምዋጀው ለዚህ ነው።’ |
ይሖዋ በኃያል ክንድ ከግብፅ ስላወጣን ይህ በዓል በእጅህ ላይ እንዳለ ምልክትና በግንባርህ ላይ እንደታሰረ ነገር ሆኖ ያገልግል።” |
ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ አምላክ ምንም እንኳ አቋራጭ ቢሆንም ወደ ፍልስጤማውያን ምድር በሚወስደው መንገድ አልመራቸውም። ምክንያቱም “ሕዝቡ ጦርነት ቢያጋጥመው ሐሳቡን ለውጦ ወደ ግብፅ ሊመለስ ይችላል” በማለት አስቦ ነበር። |
በመሆኑም አምላክ ሕዝቡ በቀይ ባሕር አቅራቢያ ባለው ምድረ በዳ በኩል ዞሮ እንዲሄድ አደረገ። እስራኤላውያንም ከግብፅ ምድር የወጡት የጦርነት አሰላለፍ ተከትለው ነበር። |
በተጨማሪም ሙሴ የዮሴፍን አፅም ይዞ ነበር፤ ምክንያቱም ዮሴፍ እስራኤላውያንን “አምላክ ፊቱን ወደ እናንተ መመለሱ አይቀርም፤ በመሆኑም አፅሜን ከዚህ ይዛችሁ ውጡ” በማለት በጥብቅ አስምሏቸው ነበር። |
እነሱም ከሱኮት ተነስተው በምድረ በዳው ዳርቻ ላይ በሚገኘው በኤታም ሰፈሩ። |
ይሖዋ የሚሄዱበትን መንገድ ይመራቸው ዘንድ ቀን ቀን በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፤ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን እንዲያገኙ ለማድረግ በእሳት ዓምድ ውስጥ ሆኖ ይመራቸው ነበር፤ በመሆኑም ቀንም ሆነ ሌሊት ይጓዙ ነበር። |
ቀን ቀን የደመናው ዓምድ ሌሊት ሌሊት ደግሞ የእሳቱ ዓምድ ከሕዝቡ ፊት አይለይም ነበር። |
“ለእነሱ የምትነግራቸው ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፦ |
“ዕብራዊ ባሪያ ከገዛህ ለስድስት ዓመት ባሪያ ሆኖ ያገለግልሃል፤ በሰባተኛው ዓመት ግን ያለምንም ክፍያ ነፃ ይወጣል። |
የመጣው ብቻውን ከሆነ ብቻውን ነፃ ይወጣል። ሚስት ካለችው ግን ሚስቱም አብራው ነፃ ትውጣ። |
ጌታው ሚስት ቢያጋባውና ሚስቱ ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆችን ብትወልድለት ሚስቱና ልጆቿ የጌታዋ ይሆናሉ፤ እሱም ብቻውን ነፃ ይወጣል። |
ሆኖም ባሪያው ‘ጌታዬን፣ ሚስቴንና ልጆቼን እወዳለሁ፤ ነፃ መውጣት አልፈልግም’ በማለት በአቋሙ ከጸና |
ጌታው በእውነተኛው አምላክ ፊት ያቅርበው። ከዚያም ጌታው ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ አምጥቶ ጆሮውን በወስፌ ይበሳዋል፤ እሱም ዕድሜውን ሙሉ ባሪያው ይሆናል። |
“አንድ ሰው ሴት ልጁን ባሪያ አድርጎ ቢሸጣት ነፃ የምትወጣው ወንድ ባሪያ ነፃ በሚወጣበት መንገድ አይደለም። |
ጌታዋ ደስ ባይሰኝባትና ቁባቱ እንድትሆን ባይፈልግ ከዚህ ይልቅ ሌላ ሰው እንዲገዛት ቢያደርግ እሷን ለባዕድ አገር ሰው የመሸጥ መብት አይኖረውም፤ ምክንያቱም ክህደት ፈጽሞባታል። |
ለወንድ ልጁ እንድትሆን ከመረጣት ደግሞ አንዲት ልጅ ማግኘት የሚገባትን መብት እንድታገኝ ያድርግ። |
ሌላ ሚስት ካገባም የመጀመሪያ ሚስቱ ምግቧ፣ ልብሷና የጋብቻ መብቷ ሊጓደልባት አይገባም። |
እነዚህን ሦስት ነገሮች የማያሟላላት ከሆነ ግን ምንም ገንዘብ ሳትከፍል እንዲሁ ነፃ ትውጣ። |
“አንድ ሰው ሌላውን ሰው መትቶ ቢገድል ገዳዩ ይገደል። |
ሆኖም የገደለው ሆን ብሎ ባይሆንና እውነተኛው አምላክ ይህ ነገር እንዲሆን ቢፈቅድ ገዳዩ የሚሸሽበት ቦታ እኔ አዘጋጅልሃለሁ። |
አንድ ሰው በባልንጀራው ላይ እጅግ ቢቆጣና ሆን ብሎ ቢገድለው ይህን ሰው ከመሠዊያዬ አጠገብም እንኳ ቢሆን ወስደህ ግደለው። |
አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ይገደል። |
“ማንኛውም ግለሰብ አንድን ሰው አፍኖ ቢወስድና ቢሸጠው ወይም ይህን ሰው ይዞት ቢገኝ ይገደል። |
“አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ይገደል። |
“ሰዎች ተጣልተው አንደኛው ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታውና ተመቺው ባይሞት ከዚህ ይልቅ አልጋ ላይ ቢውል መደረግ ያለበት ነገር ይህ ነው፦ |
ሰውየው ከአልጋው በመነሳት ከቤት ወጥቶ በምርኩዝ መንቀሳቀስ ከቻለ የመታው ሰው ከቅጣት ነፃ ይሆናል። ተጎጂው ሙሉ በሙሉ እስኪድን ድረስ ከሥራ በመስተጓጎሉ ለባከነበት ጊዜ ብቻ ካሳ ይከፍላል። |
“አንድ ሰው ወንድ ባሪያውን ወይም ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታና እጁ ላይ ቢሞትበት ወይም ብትሞትበት ይህ ሰው የበቀል ቅጣት መቀጣት አለበት። |
ሆኖም ባሪያው ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን በሕይወት ከቆየ የበቀል ቅጣት መቀጣት የለበትም፤ ምክንያቱም ይህ ሰው በጌታው ገንዘብ የተገዛ ነው። |
“ሰዎች እርስ በርስ ሲታገሉ በአንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ላይ ጉዳት ቢያደርሱባትና ያለጊዜዋ ብትወልድ ሆኖም ለሞት የተዳረገ ባይኖር ጉዳት ያደረሰው ሰው የሴትየዋ ባል የጠየቀውን ካሳ መክፈል አለበት፤ ፈራጆቹ የወሰኑበትን ካሳ መክፈል ይኖርበታል። |
ሆኖም ለሞት የተዳረገ ካለ ሕይወት ስለ ሕይወት፣ |
ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፣ እጅ ስለ እጅ፣ እግር ስለ እግር፣ |
መቃጠል ስለ መቃጠል፣ ቁስል ስለ ቁስል እንዲሁም ምት ስለ ምት እንዲመለስ ማድረግ አለብህ። |
“አንድ ሰው የወንድ ባሪያውን ወይም የሴት ባሪያውን ዓይን ቢመታና ዓይኑን ቢያጠፋው ለዓይኑ ካሳ እንዲሆን ባሪያውን ነፃ ሊያወጣው ይገባል። |
የወንድ ባሪያውን ወይም የሴት ባሪያውን ጥርስ ቢያወልቅ ለጥርሱ ካሳ እንዲሆን ከባርነቱ ነፃ አድርጎ ሊያሰናብተው ይገባል። |
“አንድ በሬ አንድን ወንድ ወይም አንዲትን ሴት ቢወጋና የተወጋው ሰው ቢሞት በሬው በድንጋይ ተወግሮ ይገደል፤ ሥጋውም መበላት የለበትም። የበሬው ባለቤት ግን ከቅጣት ነፃ ነው። |
በሬው የመዋጋት አመል እንዳለው የሚታወቅ ከሆነና ለባለቤቱም ስለ በሬው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ከነበረ በሬውን ሳይጠብቀው ቀርቶ አንድን ወንድ ወይም አንዲትን ሴት ቢገድል፣ በሬው በድንጋይ ይወገር፤ ባለቤቱም ይገደል። |
ቤዛ እንዲከፍል ከተጠየቀ ለሕይወቱ መዋጃ የሚሆነውን ዋጋ ይክፈል፤ የተጠየቀውንም ሁሉ ይስጥ። |
በሬው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ቢወጋ የበሬው ባለቤት በዚሁ ድንጋጌ መሠረት ሊፈረድበት ይገባል። |
በሬው የወጋው አንድን ወንድ ባሪያ ወይም አንዲትን ሴት ባሪያ ከሆነ የበሬው ባለቤት ለባሪያው ጌታ 30 ሰቅል ይሰጠዋል፤ በሬውም በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል። |
“አንድ ሰው ጉድጓድ ከፍቶ ወይም ቆፍሮ ጉድጓዱን ሳይከድነው ቢተወውና አንድ በሬ ወይም አንድ አህያ ጉድጓዱ ውስጥ ቢወድቅ |
የጉድጓዱ ባለቤት ካሳ መክፈል አለበት። ዋጋውን ለእንስሳው ባለቤት መስጠት ይኖርበታል፤ የሞተውም እንስሳ የእሱ ይሆናል። |
የአንድ ሰው በሬ በሌላው ሰው በሬ ላይ ጉዳት ቢያደርስና በሬው ቢሞት ሰዎቹ በሕይወት ያለውን በሬ ሸጠው ገንዘቡን ይካፈሉ፤ የሞተውንም በሬ ይካፈሉ። |
ወይም በሬው የመዋጋት አመል እንዳለበት እየታወቀ ባለቤቱ ሳይጠብቀው ቀርቶ ከሆነ ባለቤቱ በበሬ ፋንታ በሬ ካሳ መክፈል አለበት፤ የሞተውም በሬ የእሱ ይሆናል። |
ሙሴ የምድያም ካህን የሆነው የአማቱ የዮቶር መንጋ እረኛ ሆነ። እሱም መንጋውን እየመራ ወደ ምድረ በዳው ምዕራባዊ ክፍል ከተጓዘ በኋላ በመጨረሻ ወደ እውነተኛው አምላክ ተራራ ወደ ኮሬብ ደረሰ። |
ከዚያም የይሖዋ መልአክ በቁጥቋጦ መሃል በሚነድ የእሳት ነበልባል ውስጥ ተገለጠለት። እሱም ትኩር ብሎ ሲመለከት ቁጥቋጦው በእሳት ቢያያዝም አለመቃጠሉን አስተዋለ። |
ስለዚህ ሙሴ “ይህ እንግዳ ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅና ቁጥቋጦው የማይቃጠለው ለምን እንደሆነ ለማየት እስቲ ቀረብ ልበል” አለ። |
ይሖዋም ሙሴ ሁኔታውን ለማየት ቀረብ ማለቱን ሲመለከት ከቁጥቋጦው መሃል “ሙሴ! ሙሴ!” ሲል ጠራው፤ እሱም “አቤት” አለ። |
ከዚያም አምላክ “ከዚህ በላይ እንዳትቀርብ። የቆምክበት ስፍራ ቅዱስ መሬት ስለሆነ ጫማህን አውልቅ” አለው። |
እሱም በመቀጠል “እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ነኝ” አለው። በዚህ ጊዜ ሙሴ እውነተኛውን አምላክ ለማየት ስለፈራ ፊቱን ከለለ። |
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “በግብፅ የሚኖረውን የሕዝቤን መከራ በእርግጥ አይቻለሁ፤ አስገድደው በሚያሠሯቸው ሰዎች የተነሳ የሚያሰሙትን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ እየደረሰባቸው ያለውንም ሥቃይ በሚገባ አውቃለሁ። |
እኔም ከግብፃውያን እጅ ልታደጋቸው እንዲሁም ከዚያ ምድር አውጥቼ ወደ ከነአናውያን፣ ወደ ሂታውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ፈሪዛውያን፣ ወደ ሂዋውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ግዛት ይኸውም ወተትና ማር ወደምታፈሰው መልካምና ሰፊ ምድር ላስገባቸው እወርዳለሁ። |
እነሆ የእስራኤል ሕዝብ የሚያሰማው ጩኸት ወደ እኔ ደርሷል፤ ግብፃውያኑ እነሱን በመጨቆን እያደረሱባቸው ያለውን በደል ተመልክቻለሁ። |
ስለዚህ አሁን ና፤ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ፤ አንተም ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ታወጣለህ።” |
ይሁን እንጂ ሙሴ እውነተኛውን አምላክ “ወደ ፈርዖን የምሄደውና እስራኤላውያንን ከግብፅ የማወጣው ለመሆኑ እኔ ማን ነኝ?” አለው። |
እሱም በዚህ ጊዜ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ የላክሁህ እኔ ለመሆኔም ምልክቱ ይህ ነው፦ ሕዝቡን ከግብፅ ካወጣሃቸው በኋላ እውነተኛውን አምላክ በዚህ ተራራ ላይ ታገለግላላችሁ” አለው። |
ሆኖም ሙሴ እውነተኛውን አምላክ “ወደ እስራኤላውያን ሄጄ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል’ ስላቸው እነሱ ደግሞ ‘ስሙ ማን ነው?’ ብለው ቢጠይቁኝ ምን ልበላቸው?” አለው። |
በዚህ ጊዜ አምላክ ሙሴን “መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ” አለው። በመቀጠልም “እስራኤላውያንን ‘“እሆናለሁ” ወደ እናንተ ልኮኛል’ በላቸው” አለው። |
ከዚያም አምላክ ሙሴን በድጋሚ እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ የሆነው ይሖዋ ወደ እናንተ ልኮኛል።’ ይህ ለዘላለም ስሜ ነው፤ ከትውልድ እስከ ትውልድ የምታወሰውም በዚህ ነው። |
አሁን ሄደህ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ የሆነው ይሖዋ ተገልጦልኝ እንዲህ አለኝ፦ “እናንተንም ሆነ ግብፅ ውስጥ እየደረሰባችሁ ያለውን ነገር በእርግጥ ተመልክቻለሁ። |
በመሆኑም እንዲህ አልኩ፦ ግብፃውያን ከሚያደርሱባችሁ መከራ አውጥቼ ከነአናውያን፣ ሂታውያን፣ አሞራውያን፣ ፈሪዛውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን ወደሚኖሩባት ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር አስገባችኋለሁ።”’ |
“እነሱም በእርግጥ ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎችም ወደ ግብፁ ንጉሥ ሄዳችሁ እንዲህ በሉት፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ አነጋግሮን ነበር። በመሆኑም እባክህ ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ የሦስት ቀን መንገድ ወደ ምድረ በዳ እንድንጓዝ ፍቀድልን።’ |
ይሁንና የግብፁ ንጉሥ ኃያል የሆነ ክንድ ካላስገደደው በስተቀር እንድትሄዱ እንደማይፈቅድላችሁ እኔ ራሴ በሚገባ አውቃለሁ። |
በመሆኑም እጄን እዘረጋለሁ፤ ግብፅንም በመካከሏ በምፈጽማቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ እመታለሁ፤ ከዚያ በኋላ ይለቃችኋል። |
እኔም ለዚህ ሕዝብ በግብፃውያን ፊት ሞገስ እሰጠዋለሁ፤ በምትወጡበትም ጊዜ በምንም ዓይነት ባዶ እጃችሁን አትሄዱም። |
እያንዳንዷ ሴት ከጎረቤቷና ቤቷ ካረፈችው ሴት የብርና የወርቅ ዕቃዎችን እንዲሁም ልብሶችን ትጠይቅ፤ እነዚህንም ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻችሁ ታደርጉላቸዋላችሁ፤ ግብፃውያኑንም ትበዘብዛላችሁ።” |
“ዕጣን የሚጨስበት መሠዊያ ትሠራለህ፤ ከግራር እንጨትም ትሠራዋለህ። |
ርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ ሆኖ አራቱም ጎኖቹ እኩል ይሁኑ፤ ቁመቱ ደግሞ ሁለት ክንድ ይሁን። ቀንዶቹም ከዚያው ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሆናሉ። |
ላዩን፣ ሁሉንም ጎኖቹን እንዲሁም ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ ዙሪያውንም የወርቅ ክፈፍ ትሠራለታለህ። |
በተጨማሪም በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ትሠራለታለህ፤ ቀለበቶቹም መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች የሚገቡባቸው ይሆናሉ። |
መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው። |
ራሴን ለአንተ ከምገልጥበት ከምሥክሩ ታቦት አጠገብ ካለው መጋረጃ በፊት ይኸውም ምሥክሩን ከሚጋርደው መከለያ በፊት ታስቀምጠዋለህ። |
“አሮንም ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን ያጨስበታል፤ በየማለዳው መብራቶቹን በሚያዘገጃጅበት ጊዜም ዕጣኑ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል። |
በተጨማሪም አሮን አመሻሹ ላይ መብራቶቹን በሚያበራበት ጊዜ ዕጣኑን ያጨሰዋል። ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘወትር በይሖዋ ፊት የሚቀርብ የዕጣን መባ ነው። |
በዚህ መሠዊያ ላይ ያልተፈቀደ ዕጣን ወይም የሚቃጠል መባ አሊያም የእህል መባ አታቅርቡ፤ እንዲሁም በላዩ ላይ የመጠጥ መባ አታፍስሱ። |
አሮንም በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተሰረያ ያድርግ። ለማስተሰረያ ከቀረበው የኃጢአት መባ ላይ የተወሰነ ደም ወስዶ በዓመት አንድ ጊዜ ለመሠዊያው ማስተሰረያ ያደርጋል፤ ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይደረጋል። ይህ ለይሖዋ እጅግ የተቀደሰ ነው።” |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“የሕዝብ ቆጠራ በማካሄድ የእስራኤልን ልጆች በምትቆጥርበት ጊዜ ሁሉ እያንዳንዱ ሰው በቆጠራው ወቅት ለይሖዋ ስለ ሕይወቱ ቤዛ መስጠት አለበት። ይህን የሚያደርጉት በሚመዘገቡበት ጊዜ መቅሰፍት እንዳይመጣባቸው ነው። |
የተመዘገቡት ሁሉ የሚሰጡት ይህን ነው፦ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣሉ። አንድ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው። ለይሖዋ የሚሰጠው መዋጮ ግማሽ ሰቅል ነው። |
ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ሁሉ ለይሖዋ መዋጮ ይሰጣሉ። |
ለሕይወታችሁ ማስተሰረያ እንዲሆን ለይሖዋ መዋጮ በምትሰጡበት ጊዜ ባለጸጋው ከግማሽ ሰቅል አብልጦ፣ ችግረኛውም ከግማሽ ሰቅል አሳንሶ አይስጥ። |
ለሕይወታችሁ ማስተሰረያ በመሆን በይሖዋ ፊት ለእስራኤላውያን እንደ መታሰቢያ ሆኖ እንዲያገለግል ለማስተሰረያ የቀረበውን የብር ገንዘብ ከእስራኤላውያን ወስደህ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ለሚቀርበው አገልግሎት ትሰጠዋለህ።” |
በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.