text
stringlengths
4
267
ሽማግሌዎቹን ግን እንዲህ አላቸው፦ “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ እዚሁ ጠብቁን። አሮንና ሁር አብረዋችሁ ናቸው። ሙግት ያለው ሰው ቢኖር እነሱ ፊት መቅረብ ይችላል።”
ሙሴም ወደ ተራራው ሲወጣ ደመናው ተራራውን ሸፍኖት ነበር።
የይሖዋም ክብር በሲና ተራራ ላይ እንዳረፈ ነበር፤ ደመናውም ለስድስት ቀናት ተራራውን ሸፍኖት ነበር። በሰባተኛውም ቀን ከደመናው መሃል ሙሴን ጠራው።
ሁኔታውን ይከታተሉ ለነበሩት እስራኤላውያን የይሖዋ ክብር በተራራው አናት ላይ እንዳለ የሚባላ እሳት ሆኖ ታያቸው።
ከዚያም ሙሴ ወደ ደመናው ገባ፤ ወደ ተራራውም ወጣ። ሙሴም በተራራው ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆየ።
“ርዝመቱ አምስት ክንድ፣ ወርዱም አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ትሠራለህ። መሠዊያው አራቱም ጎኖቹ እኩል፣ ከፍታው ደግሞ ሦስት ክንድ መሆን አለበት።
በአራቱ ማዕዘኖቹ ላይ ቀንዶች ትሠራለታለህ፤ ቀንዶቹም የመሠዊያው ክፍል ይሆናሉ፤ መሠዊያውንም በመዳብ ትለብጠዋለህ።
አመዱን ማስወገጃ ባልዲዎችን፣ አካፋዎችን፣ ሳህኖችን፣ ሹካዎችንና መኮስተሪያዎችን ትሠራለህ፤ ዕቃዎቹንም ሁሉ ከመዳብ ትሠራቸዋለህ።
ለመሠዊያው እንደ መረብ አድርገህ የመዳብ ፍርግርግ ትሠራለታለህ፤ በፍርግርጉ በአራቱም ማዕዘኖቹ ላይ አራት የመዳብ ቀለበቶችን ትሠራለታለህ።
ፍርግርጉንም ከመሠዊያው ጠርዝ ወደ ታች ወረድ አድርገህ ታስቀምጠዋለህ፤ ፍርግርጉም መሠዊያው መሃል አካባቢ ይሆናል።
ለመሠዊያው የሚሆኑ መሎጊያዎችን ከግራር እንጨት ትሠራለህ፤ በመዳብም ትለብጣቸዋለህ።
መሎጊያዎቹም ቀለበቶቹ ውስጥ ይገባሉ፤ መሠዊያውን በምትሸከሙበትም ጊዜ መሎጊያዎቹ በሁለቱ ጎኖቹ በኩል ይሆናሉ።
መሠዊያውንም ባዶ ሣጥን አስመስለህ ከሳንቃ ትሠራዋለህ። ልክ ተራራው ላይ ባሳየህ መሠረት ይሠራ።
“የማደሪያ ድንኳኑን ግቢ ትሠራለህ። በስተ ደቡብ በኩል የሚገኘው፣ ፊቱ በደቡብ አቅጣጫ ያለው የግቢው ጎን በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ይኖሩታል፤ የአንዱ ጎን ርዝመት 100 ክንድ ይሆናል።
ግቢው 20 ቋሚዎችና ከመዳብ የተሠሩ 20 መሰኪያዎች ይኖሩታል። በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው ደግሞ ከብር የተሠሩ ይሆናሉ።
በስተ ሰሜን በኩል በሚገኘው ጎን ያሉት መጋረጃዎችም ርዝመታቸው 100 ክንድ ይሆናል፤ እንዲሁም 20 ቋሚዎችና ለቋሚዎቹ የሚሆኑ ከመዳብ የተሠሩ 20 መሰኪያዎች ይኖራሉ፤ በቋሚዎቹም ላይ ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎች ይኖራሉ።
በስተ ምዕራብ አቅጣጫ በግቢው ወርድ ልክ 50 ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖራሉ፤ አሥር ቋሚዎችና አሥር መሰኪያዎችም ይኖሯቸዋል።
በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በፀሐይ መውጫ በኩል ያለው የግቢው ወርድ 50 ክንድ ነው።
በአንዱ በኩል 15 ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖራሉ፤ ሦስት ቋሚዎችና ሦስት መሰኪያዎችም ይኖሯቸዋል።
በሌላኛውም በኩል 15 ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖራሉ፤ ሦስት ቋሚዎችና ሦስት መሰኪያዎችም ይኖሯቸዋል።
“የግቢው መግቢያ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር ተሸምኖ የተሠራ 20 ክንድ ርዝመት ያለው መከለያ ይኑረው፤ አራት ቋሚዎችና ለቋሚዎቹ የሚሆኑ አራት መሰኪያዎችም ይኑሩት።
በግቢው ዙሪያ ያሉት ቋሚዎች በሙሉ ከብር የተሠሩ መቆንጠጫዎችና ከብር የተሠሩ ማንጠልጠያዎች ይኖሯቸዋል፤ መሰኪያዎቻቸው ግን ከመዳብ የተሠሩ ይሆናሉ።
ግቢው ርዝመቱ 100 ክንድ፣ ወርዱ 50 ክንድ ሆኖ በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠሩ 5 ክንድ ከፍታ ያላቸው መጋረጃዎች ይኖሩታል፤ ከመዳብ የተሠሩ መሰኪያዎችም ይኑሩት።
በማደሪያ ድንኳኑ ውስጥ ለሚቀርበው አገልግሎት የሚውሉት ቁሳቁሶችና ዕቃዎች በሙሉ እንዲሁም የድንኳኑ ካስማዎችና የግቢው ካስማዎች በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ይሆናሉ።
“አንተም መብራቶቹ ያለማቋረጥ እንዲበሩ ለመብራት የሚሆን ተጨቅጭቆ የተጠለለ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን ታዛቸዋለህ።
አሮንና ወንዶች ልጆቹ መብራቶቹ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በምሥክሩ አጠገብ ካለው መጋረጃ ውጭ ከምሽት አንስቶ እስከ ጠዋት ድረስ በይሖዋ ፊት እንዲበሩ ያደርጋሉ። ይህ እስራኤላውያን በትውልዶቻቸው ሁሉ የሚፈጽሙት ዘላቂ ደንብ ነው።
በዚያን ጊዜ ከሌዊ ነገድ የሆነ አንድ ሰው የሌዊን ልጅ አገባ።
ሴቲቱም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። ልጁም በጣም የሚያምር መሆኑን ስታይ ለሦስት ወር ደብቃ አቆየችው።
ከዚያ በላይ ደብቃ ልታቆየው እንደማትችል ስታውቅ ግን የደንገል ቅርጫት ወስዳ ቅርጫቱን በቅጥራንና በዝፍት ለቀለቀችው፤ ከዚያም ልጁን በቅርጫቱ ውስጥ አድርጋ በአባይ ወንዝ ዳር በሚገኘው ቄጠማ መሃል አስቀመጠችው።
እህቱ ግን የሕፃኑ መጨረሻ ምን እንደሚሆን ለማወቅ ራቅ ብላ ቆማ ሁኔታውን ትከታተል ነበር።
በዚህ ጊዜ የፈርዖን ሴት ልጅ ገላዋን ልትታጠብ ወደ አባይ ወረደች፤ ደንገጡሮቿም በአባይ ወንዝ ዳር ዳር ይሄዱ ነበር። እሷም በቄጠማው መሃል ቅርጫቱን አየች። ወዲያውኑም ቅርጫቱን እንድታመጣላት ባሪያዋን ላከቻት።
ቅርጫቱንም ስትከፍት ሕፃኑን አየችው፤ ሕፃኑም እያለቀሰ ነበር። እሷም “ይህ ልጅ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች፤ ያም ሆኖ ለሕፃኑ አዘነችለት።
ከዚያም የሕፃኑ እህት የፈርዖንን ልጅ “ከዕብራውያን ሴቶች መካከል ልጁን እያጠባች የምታሳድግልሽ ሞግዚት ልጥራልሽ?” አለቻት።
የፈርዖንም ልጅ “አዎ፣ ሂጂ!” አለቻት። ልጅቷም ወዲያውኑ ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራቻት።
የፈርዖን ልጅም ሴትየዋን “ይህን ሕፃን ወስደሽ እያጠባሽ አሳድጊልኝ፤ እኔም እከፍልሻለሁ” አለቻት። በመሆኑም ሴትየዋ ልጁን ወስዳ እያጠባች ታሳድገው ጀመር።
ልጁም ባደገ ጊዜ አምጥታ ለፈርዖን ልጅ ሰጠቻት፤ እሱም ልጇ ሆነ። እሷም “ከውኃ ውስጥ አውጥቼዋለሁ” በማለት ስሙን ሙሴ አለችው።
ሙሴ በጎለመሰ ጊዜ ወንድሞቹ የተጫነባቸውን ሸክም ለማየት ወደ እነሱ ወጣ፤ ከዚያም ከወንድሞቹ አንዱ የሆነውን ዕብራዊ አንድ ግብፃዊ ሲደበድበው አየ።
በመሆኑም ወዲያና ወዲህ ተመልክቶ ማንም አለመኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ግብፃዊውን ገድሎ አሸዋ ውስጥ ደበቀው።
ሆኖም በማግስቱ ሲወጣ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ ተመለከተ። እሱም ጥፋተኛውን “የገዛ ወገንህን የምትመታው ለምንድን ነው?” አለው።
በዚህ ጊዜ “አንተን በእኛ ላይ አለቃና ፈራጅ ማን አደረገህ? ግብፃዊውን እንደገደልከው እኔንም ልትገድለኝ ታስባለህ?” አለው። ሙሴም “ይህ ነገር ታውቋል ማለት ነው!” ብሎ በማሰብ ፈራ።
ከዚያም ፈርዖን ይህን ነገር ሰማ፤ ሙሴንም ሊገድለው ሞከረ፤ ይሁን እንጂ ሙሴ ከፈርዖን ሸሽቶ በምድያም ምድር ለመኖር ሄደ፤ እዚያም በአንድ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ።
በምድያም የነበረው ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነሱም ውኃ ቀድተው ገንዳውን በመሙላት የአባታቸውን መንጋ ውኃ ለማጠጣት መጡ።
ሆኖም እንደወትሮው እረኞቹ መጥተው ሴቶቹን አባረሯቸው። በዚህ ጊዜ ሙሴ ተነስቶ ለሴቶቹ አገዘላቸው፤ መንጋቸውንም አጠጣላቸው።
ሴቶቹም ወደ ቤት፣ ወደ አባታቸው ወደ ረኡዔል በተመለሱ ጊዜ አባታቸው “ዛሬ እንዴት ቶሎ መጣችሁ?” ሲል በመገረም ጠየቃቸው።
እነሱም “አንድ ግብፃዊ ከእረኞቹ እጅ አዳነን፤ እንዲያውም ውኃ ቀድቶ መንጋችንን አጠጣልን” አሉት።
እሱም ልጆቹን “ታዲያ ሰውየው የት አለ? ለምን ትታችሁት መጣችሁ? አብሮን ይበላ ዘንድ ጥሩት” አላቸው።
ከዚያ በኋላ ሙሴ ከሰውየው ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ሰውየውም ልጁን ሲፓራን ለሙሴ ዳረለት።
እሷም ከጊዜ በኋላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም “በባዕድ አገር የምኖር የባዕድ አገር ሰው ሆንኩ” በማለት ስሙን ጌርሳም አለው።
ከረጅም ጊዜ በኋላ የግብፁ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያን ግን ካሉበት የባርነት ሕይወት የተነሳ መቃተታቸውንና እሮሮ ማሰማታቸውን አላቆሙም ነበር፤ ከባርነት ሕይወታቸው የተነሳ እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙት ጩኸት ወደ እውነተኛው አምላክ ወጣ።
ከጊዜ በኋላም አምላክ በመቃተት የሚያሰሙትን ጩኸት አዳመጠ፤ እንዲሁም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳኑን አሰበ።
በመሆኑም አምላክ እስራኤላውያንን አየ፤ ያሉበትንም ሁኔታ ተመለከተ።
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ ምክንያቱም የእሱም ሆነ የአገልጋዮቹ ልብ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤ ይህን የማደርገውም እነዚህን ተአምራዊ ምልክቶቼን በፊቱ እንዳሳይ
እንዲሁም ግብፅን እንዴት አድርጌ እንደቀጣሁና በመካከላቸው ተአምራዊ ምልክቶቼን እንዴት እንዳሳየሁ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ እንድታውጅ ነው፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በእርግጥ ታውቃላችሁ።”
በመሆኑም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለመሆኑ ለእኔ ለመገዛት ፈቃደኛ የማትሆነው እስከ መቼ ነው? እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ።
አሁንም ሕዝቤን ለመልቀቅ ፈቃደኛ የማትሆን ከሆነ ግን በነገው ዕለት በግዛትህ ላይ አንበጦችን አመጣለሁ።
አንበጦቹም ምድሪቱን ይሸፍናሉ፤ መሬቱንም ማየት አይቻልም። እነሱም ከበረዶው ያመለጠውንና የቀረላችሁን ነገር ሁሉ ሙልጭ አድርገው ይበሉታል፤ በመስክ ላይ እየበቀሉ ያሉትን ዛፎቻችሁን በሙሉ ይበሏቸዋል።
አንበጦቹ አባቶችህና አያቶችህ በዚህች ምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ አይተውት በማያውቁት ሁኔታ ቤቶችህን፣ የአገልጋዮችህን ቤቶች ሁሉና የግብፅን ቤቶች ሁሉ ይሞላሉ።’” እሱም ይህን ከተናገረ በኋላ ፊቱን አዙሮ ከፈርዖን ፊት ወጥቶ ሄደ።
ከዚያም የፈርዖን አገልጋዮች ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው ወጥመድ የሚሆንብን እስከ መቼ ነው? አምላካቸውን ይሖዋን እንዲያገለግሉ ሰዎቹን ልቀቃቸው። ግብፅ እየጠፋች እንደሆነ እስካሁን አልተገነዘብክም?”
በመሆኑም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ተመልሰው እንዲመጡ ተደረገ፤ እሱም “ሂዱ፤ አምላካችሁን ይሖዋን አገልግሉ። ይሁንና የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው።
በዚህ ጊዜ ሙሴ “ለይሖዋ የምናከብረው በዓል ስላለን ወጣቶቻችንን፣ አዛውንቶቻችንን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን እንዲሁም በጎቻችንንና ከብቶቻችንን ይዘን እንሄዳለን” አለ።
እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተንና ልጆቻችሁን ከለቀኩማ በእርግጥም ይሖዋ ከእናንተ ጋር ነው! መቼም የሆነ ተንኮል እንዳሰባችሁ ግልጽ ነው።
ይሄማ አይሆንም! ወንዶቹ ብቻ ሄደው ይሖዋን ያገልግሉ፤ ምክንያቱም የጠየቃችሁት ይህንኑ ነው።” ከዚያም ከፈርዖን ፊት እንዲወጡ ተደረገ።
በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንበጦች መጥተው የግብፅን ምድር እንዲወሩና ከበረዶ የተረፈውን በምድሩ ላይ ያለውን ማንኛውንም ተክል ጠራርገው እንዲበሉ በግብፅ ምድር ላይ እጅህን ዘርጋ።”
ሙሴም ወዲያው በግብፅ ምድር ላይ በትሩን ሰነዘረ፤ ይሖዋም በዚያን ዕለት ቀኑንና ሌሊቱን ሙሉ በምድሩ ላይ የምሥራቅ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ። ሲነጋም የምሥራቁ ነፋስ አንበጦችን አመጣ።
አንበጦቹም በመላው የግብፅ ምድር ላይ መውጣትና በግብፅ ግዛት ሁሉ ላይ መስፈር ጀመሩ። ሁኔታው እጅግ አስከፊ ነበር፤ ከዚህ በፊት ያን ያህል ብዛት ያለው አንበጣ ታይቶ አያውቅም፤ ዳግመኛም ያን ያህል ብዛት ያለው አንበጣ ፈጽሞ አይከሰትም።
አንበጦቹም መላውን ምድር ሸፈኑት፤ ምድሪቱም በእነሱ የተነሳ ጨለመች፤ እነሱም ከበረዶው የተረፈውን በምድሩ ላይ ያለውን ተክል ሁሉ እንዲሁም በዛፎች ላይ ያለውን ፍሬ ሁሉ ጠራርገው በሉት፤ በመላው የግብፅ ምድር በዛፎችም ሆነ በመስክ ባሉ ተክሎች ላይ አንድም ለምለም ቅጠል አልተረፈም።
በመሆኑም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን በአስቸኳይ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በአምላካችሁ በይሖዋም ሆነ በእናንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁ።
ስለሆነም አሁን እባካችሁ ይህን ኃጢአቴን ብቻ ይቅር በሉኝ፤ ይህን ገዳይ መቅሰፍት ከእኔ ላይ እንዲያስወግድልኝም አምላካችሁን ይሖዋን ለምኑልኝ።”
እሱም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ ይሖዋንም ለመነ።
ከዚያም ይሖዋ ነፋሱ እንዲቀየር አደረገ፤ ነፋሱም ኃይለኛ የምዕራብ ነፋስ ሆነ፤ ነፋሱም አንበጦቹን ወስዶ ቀይ ባሕር ውስጥ ከተታቸው። በመላው የግብፅ ግዛት አንድም አንበጣ አልቀረም።
ሆኖም ይሖዋ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ እሱም እስራኤላውያንን አለቀቀም።
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “በግብፅ ምድር ላይ ጨለማ ይኸውም የሚዳሰስ የሚመስል ድቅድቅ ጨለማ እንዲከሰት እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው።
ሙሴም ወዲያውኑ እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በመላው የግብፅ ምድር ላይም ለሦስት ቀን ያህል ድቅድቅ ጨለማ ተከሰተ።
እነሱም እርስ በርስ አይተያዩም ነበር፤ ለሦስት ቀን ማናቸውም ካሉበት ቦታ ንቅንቅ ማለት አልቻሉም፤ ሆኖም እስራኤላውያን ሁሉ በሚኖሩበት ስፍራ ብርሃን ነበር።
ከዚያም ፈርዖን ሙሴን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ሂዱ፣ ይሖዋን አገልግሉ። በጎቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ እዚሁ ይቀራሉ። ልጆቻችሁም አብረዋችሁ መሄድ ይችላሉ።”
ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦ “እንግዲያውስ ለመሥዋዕቶችና ለሚቃጠሉ መባዎች የሚሆኑትን እንስሳት አንተው ራስህ ትሰጠንና ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገን እናቀርባቸዋለን።
ከብቶቻችንም አብረውን መሄድ አለባቸው። አምላካችንን ይሖዋን ስናመልክ ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹን መሥዋዕት አድርገን ስለምናቀርብ አንድም እንስሳ እዚህ መቅረት የለበትም፤ ደግሞም እኛ ራሳችን ለይሖዋ አምልኮ ምን መሥዋዕት ማቅረብ እንዳለብን የምናውቀው እዚያ ስንደርስ ነው።”
ይሖዋም የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ እሱም ሊለቃቸው ፈቃደኛ አልሆነም።
ስለሆነም ፈርዖን “ከፊቴ ጥፋ! ዳግመኛ ፊቴን ለማየት እንዳትሞክር፤ ፊቴን የምታይበት ቀን መሞቻህ እንደሚሆን እወቅ” አለው።
በዚህ ጊዜ ሙሴ “እሺ፣ እንዳልከው ይሁን፤ ዳግመኛ ፊትህን አላይም” አለው።
ከኤሊም ከተነሱ በኋላም መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ከግብፅ ምድር በወጣ በሁለተኛው ወር በ15ኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወደሚገኘው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጣ።
ከዚያም መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ በምድረ በዳ ሳለ በሙሴና በአሮን ላይ ማጉረምረም ጀመረ።
እስራኤላውያንም እንዲህ ይሏቸው ነበር፦ “በግብፅ ምድር በሥጋው ድስት አጠገብ ተቀምጠን ሳለንና እስክንጠግብ ድረስ ዳቦ ስንበላ በነበረበት ጊዜ ምነው በይሖዋ እጅ ሞተን ባረፍነው ኖሮ። እናንተ ግን ይህን ጉባኤ በሙሉ በረሃብ ልትጨርሱት ወደዚህ ምድረ በዳ አመጣችሁን።”
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኔ ከሰማይ ምግብ አዘንብላችኋለሁ፤ ሕዝቡም ይውጣ፤ እያንዳንዱም ሰው ወጥቶ የሚበቃውን ያህል በየዕለቱ ይሰብስብ፤ በዚህም ሕጌን አክብረው ይመላለሱ እንደሆነና እንዳልሆነ እፈትናቸዋለሁ።
በስድስተኛው ቀን የሰበሰቡትን በሚያዘጋጁበት ጊዜ ግን በሌሎቹ ቀናት ከሚሰበስቡት እጥፍ ይሁን።”
በመሆኑም ሙሴና አሮን እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አሏቸው፦ “ከግብፅ ምድር ያወጣችሁ ይሖዋ መሆኑን በዚህ ምሽት በእርግጥ ታውቃላችሁ።
ጠዋት ላይ የይሖዋን ክብር ታያላችሁ፤ ምክንያቱም ይሖዋ በእሱ ላይ ማጉረምረማችሁን ሰምቷል። በእኛ ላይ የምታጉረመርሙት ለመሆኑ እኛ ማን ነን?”
ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ምሽት ላይ፣ የምትበሉት ሥጋ ጠዋት ላይ ደግሞ የምትፈልጉትን ያህል ዳቦ ሲሰጣችሁ ይሖዋ በእሱ ላይ ያጉረመረማችሁትን ማጉረምረም እንደሰማ ታያላችሁ። ታዲያ እኛ ማን ነን? ያጉረመረማችሁት በእኛ ላይ ሳይሆን በይሖዋ ላይ ነው።”
ሙሴም አሮንን “ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ‘ማጉረምረማችሁን ስለሰማ ኑ በይሖዋ ፊት ቅረቡ’ በላቸው” አለው።
አሮን ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ወደ ምድረ በዳው ዞሮ ቆመ፤ በዚህ ጊዜ የይሖዋ ክብር በደመናው ውስጥ ተገለጠ።
በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
“የእስራኤላውያንን ማጉረምረም ሰምቻለሁ። እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘አመሻሹ ላይ ሥጋ ትበላላችሁ፤ ጠዋት ላይ ደግሞ ዳቦ ትጠግባላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ታውቃላችሁ።’”
በዚህም መሠረት ምሽት ላይ ድርጭቶች መጥተው ሰፈሩን አለበሱት፤ ጠዋት ላይም በሰፈሩ ውስጥ ሁሉ ጤዛ ወርዶ ነበር።
በኋላም ጤዛው ሲተን በምድረ በዳው ላይ እንደ አመዳይ ደቃቅ የሆነ ቅርፊት የሚመስል ስስ ነገር መሬቱ ላይ ታየ።
እስራኤላውያንም ባዩት ጊዜ ምን እንደሆነ ስላላወቁ እርስ በርሳቸው “ይህ ነገር ምንድን ነው?” ይባባሉ ጀመር። ስለሆነም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንድትበሉት የሰጣችሁ ምግብ ነው።
ይሖዋ እንዲህ ሲል አዟል፦ ‘እያንዳንዱ ሰው የሚበላውን ያህል ይሰብስብ። እያንዳንዳችሁ በድንኳናችሁ ውስጥ ባሉት ሰዎች ቁጥር ልክ ለእያንዳንዱ ሰው አንድ ኦሜር ሰፍራችሁ ውሰዱ።’”
እስራኤላውያንም እንደተባሉት አደረጉ፤ ይሰበስቡም ጀመር፤ አንዳንዶቹ ብዙ ሌሎቹ ደግሞ ትንሽ ሰበሰቡ።
የሰበሰቡትን በኦሜር ሲሰፍሩት ብዙ የሰበሰበው ምንም ትርፍ አላገኘም፤ ጥቂት የሰበሰበውም ምንም አልጎደለበትም። እያንዳንዳቸው የሰበሰቡት የሚበሉትን ያህል ነበር።
ከዚያም ሙሴ “ማንም ሰው እስከ ጠዋት ድረስ ምንም ማስተረፍ የለበትም” አላቸው።
እነሱ ግን ሙሴን አልሰሙትም። አንዳንዶቹ ከሰበሰቡት ውስጥ የተወሰነውን አሳደሩት፤ ሆኖም ተልቶ መሽተት ጀመረ፤ በመሆኑም ሙሴ በእነሱ ላይ እጅግ ተቆጣ።