text
stringlengths
4
267
በየማለዳው እያንዳንዱ ሰው የሚበላውን ያህል ይሰበስብ ነበር። ፀሐዩ እየበረታ በሚሄድበት ጊዜም ይቀልጥ ነበር።
በስድስተኛውም ቀን ሁለት እጥፍ ምግብ ይኸውም ለአንድ ሰው ሁለት ኦሜር ሰበሰቡ። በመሆኑም የማኅበረሰቡ አለቆች በሙሉ መጥተው ሁኔታውን ለሙሴ ነገሩት።
በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ይሄማ ይሖዋ የተናገረው ነገር ነው። ነገ ሙሉ በሙሉ የእረፍት ቀን ይኸውም ለይሖዋ ቅዱስ ሰንበት ይሆናል። የምትጋግሩትን ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈውን ሁሉ አስቀምጡ፤ እስከ ጠዋትም ድረስ አቆዩት።”
እነሱም ልክ ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት እስከ ጠዋት ድረስ አቆዩት፤ ምግቡም አልሸተተም ወይም አልተላም።
ከዚያም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ዛሬ ይህን ብሉ፤ ምክንያቱም ዛሬ የይሖዋ ሰንበት ነው። ዛሬ ሜዳው ላይ አታገኙትም።
ስድስት ቀን ትሰበስባላችሁ፤ በሰባተኛው ቀን ይኸውም በሰንበት ቀን ግን ምንም አይገኝም።”
ይሁንና ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ በሰባተኛው ቀን ሊሰበስቡ ወጡ፤ ሆኖም ምንም አላገኙም።
በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ሰዎች ትእዛዛቴንና ሕጎቼን ለማክበር እንቢተኛ የምትሆኑት እስከ መቼ ነው?
ይሖዋ ሰንበትን እንደሰጣችሁ ልብ በሉ። በስድስተኛው ቀን ለሁለት ቀን የሚሆን ምግብ የሰጣችሁም ለዚህ ነው። እያንዳንዱ ሰው ባለበት ስፍራ መቆየት አለበት፤ በሰባተኛውም ቀን ማንም ሰው ካለበት ቦታ መውጣት የለበትም።”
ሕዝቡም በሰባተኛው ቀን ሰንበትን አከበረ።
የእስራኤልም ቤት ምግቡን “መና” አሉት። እሱም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ ሲሆን ጣዕሙም ማር እንደተቀባ ቂጣ ነበር።
ከዚያም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንዲህ ሲል አዟል፦ ‘ከግብፅ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ እንድትበሉት የሰጠኋችሁን ምግብ እንዲያዩ ከእሱ አንድ ኦሜር ሰፍራችሁ ለሚመጡት ትውልዶቻችሁ ሁሉ አስቀምጡ።’”
በመሆኑም ሙሴ አሮንን “ማሰሮ ወስደህ አንድ ኦሜር መና ጨምርበት፤ ለሚመጡት ትውልዶቻችሁ ሁሉ ተጠብቆ እንዲቆይ በይሖዋ ፊት አስቀምጠው” አለው።
አሮንም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተጠብቆ እንዲቆይ መናውን በምሥክሩ ፊት አስቀመጠው።
እስራኤላውያንም ወደሚኖሩበት ምድር እስከሚመጡ ድረስ ለ40 ዓመት መናውን በሉ። ወደ ከነአን ምድር ድንበር እስከሚደርሱ ድረስ መናውን በሉ።
አንድ ኦሜር፣ የኢፍ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ ነው።
ከዚያ በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያከብርልኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ይላል።”
ፈርዖን ግን እንዲህ አለ፦ “የእሱን ቃል ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለመሆኑ ይሖዋ ማነው? እኔ ይሖዋ የምትሉትን ፈጽሞ አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም።”
ሆኖም እነሱ እንዲህ አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ አነጋግሮን ነበር። በመሆኑም እባክህ የሦስት ቀን መንገድ ወደ ምድረ በዳ ተጉዘን ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት ማቅረብ እንፈልጋለን፤ ካልሆነ ግን በበሽታ ወይም በሰይፍ ይጨርሰናል።”
የግብፅም ንጉሥ “ሙሴና አሮን፣ ሕዝቡን ሥራ የምታስፈቱት ለምንድን ነው? አርፋችሁ ወደ ጉልበት ሥራችሁ ተመለሱ!” አላቸው።
ፈርዖንም በመቀጠል “የምድሩ ሕዝብ ምን ያህል ብዙ እንደሆነ ተመልከት፤ አንተ ደግሞ ሥራ ልታስፈታቸው ነው” አለ።
ፈርዖንም በዚያኑ ዕለት የሥራ ኃላፊዎቹንና አሠሪዎቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦
“ከአሁን በኋላ ለጡብ መሥሪያ የሚሆን ጭድ ለሕዝቡ እንዳትሰጡ። ራሳቸው ሄደው ጭድ ይሰብስቡ።
ሆኖም በፊት ይሠሩት የነበረውን ያህል ጡብ ሠርተው እንዲያስረክቡ አድርጉ። ዘና እያሉ ስለሆነ ማስረከብ ከሚጠበቅባቸው ጡብ ምንም እንዳትቀንሱላቸው። ‘መሄድ እንፈልጋለን፤ ሄደን ለአምላካችን መሥዋዕት ማቅረብ እንፈልጋለን!’ እያሉ የሚጮኹት ለዚህ ነው።
ለሐሰት ወሬ ጆሯቸውን እንዳይሰጡ ሥራውን አክብዱባቸው፤ እንዲሁም ፋታ አሳጧቸው።”
ስለዚህ የሥራ ኃላፊዎቹና አሠሪዎቹ ወጥተው ለሕዝቡ እንዲህ አሉ፦ “ፈርዖን እንዲህ ይላል፦ ‘ከእንግዲህ ጭድ አላቀርብላችሁም።
ራሳችሁ ሄዳችሁ ከየትም ፈልጋችሁ ጭድ አምጡ፤ ሥራችሁ ግን በምንም ዓይነት አይቀነስም።’”
ከዚያም ሕዝቡ እንደ ጭድ ሆኖ የሚያገለግለውን የእህል ቆረን ለመሰብሰብ በመላው የግብፅ ምድር ተሰማራ።
የሥራ ኃላፊዎቹም “እያንዳንዳችሁ ጭድ ይቀርብላችሁ በነበረበት ጊዜ ታደርጉት እንደነበረው ሁሉ አሁንም በየዕለቱ የሚጠበቅባችሁን ሥራ ሠርታችሁ ማጠናቀቅ አለባችሁ” እያሉ ያስገድዷቸው ነበር።
በተጨማሪም የፈርዖን የሥራ ኃላፊዎች የሾሟቸው የእስራኤላውያን አሠሪዎች ተገረፉ። እነሱንም “ቀደም ሲል ሠርታችሁ ታስረክቡት የነበረውን ያህል ጡብ ሠርታችሁ ያላስረከባችሁት ለምንድን ነው? ትናንትም ሆነ ዛሬ እንዲህ አላደረጋችሁም” ብለው ጠየቋቸው።
በመሆኑም የእስራኤላውያን አሠሪዎች ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ በማለት እሮሯቸውን አሰሙ፦ “በአገልጋዮችህ ላይ እንዲህ ያለ ድርጊት የምትፈጽመው ለምንድን ነው?
ለእኛ ለአገልጋዮችህ ምንም ጭድ አይሰጠንም፤ እነሱ ግን ‘ጡብ ሥሩ!’ ይሉናል። ጥፋቱ የገዛ ሰዎችህ ሆኖ ሳለ እኛ አገልጋዮችህ እንገረፋለን።”
እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እኮ ተዝናንታችኋል፤ አዎ፣ ዘና እያላችሁ ነው! ‘መሄድ እንፈልጋለን፤ ሄደን ለይሖዋ መሥዋዕት ማቅረብ እንፈልጋለን!’ የምትሉት ለዚህ ነው።
በሉ አሁን ወደ ሥራችሁ ተመለሱ! ምንም ጭድ አይቀርብላችሁም፤ ሆኖም የሚጠበቅባችሁን ያህል ጡብ መሥራት አለባችሁ።”
የእስራኤል አሠሪዎችም “በየዕለቱ ማስረከብ ከሚጠበቅባችሁ ጡብ ምንም ማጉደል የለባችሁም” የሚለውን ትእዛዝ ሲሰሙ ከባድ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ተረዱ።
እነሱም ፈርዖንን አነጋግረው ሲወጡ በዚያ ቆመው ይጠብቋቸው የነበሩትን ሙሴንና አሮንን አገኟቸው።
እነሱም እንዲህ አሏቸው፦ “በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት እንድንጠላ ስላደረጋችሁና እንዲገድሉን በእጃቸው ሰይፍ ስለሰጣችኋቸው ይሖዋ ይይላችሁ፤ ደግሞም ይፍረድባችሁ።”
በዚህ ጊዜ ሙሴ ወደ ይሖዋ ተመልሶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ሕዝብ ለመከራ የዳረግከው ለምንድን ነው? እኔንስ የላክኸኝ ለምንድን ነው?
ፈርዖን በስምህ ለመናገር ወደ እሱ ከገባሁበት ጊዜ አንስቶ ይህን ሕዝብ ይበልጥ ማንገላታቱን ቀጥሏል፤ አንተም ብትሆን ሕዝብህን አላዳንክም።”
በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
“ወደ ኋላ ተመልሰው በሚግዶልና በባሕሩ መካከል ባለው በበዓልጸፎን ትይዩ በሚገኘው በፊሃሂሮት ፊት ለፊት እንዲሰፍሩ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። በበዓልጸፎን ፊት ለፊት በባሕሩ አጠገብ ስፈሩ።
ፈርዖንም ስለ እስራኤላውያን ‘ግራ ተጋብተው በምድሪቱ ላይ እየተንከራተቱ ነው። ምድረ በዳው ጋሬጣ ሆኖባቸዋል’ ማለቱ አይቀርም።
እኔም የፈርዖን ልብ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤ እሱም ያሳድዳቸዋል፤ እኔም ፈርዖንንና ሠራዊቱን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን እጎናጸፋለሁ፤ ግብፃውያንም እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።” እነሱም ልክ እንዲሁ አደረጉ።
በኋላም ለግብፁ ንጉሥ ሕዝቡ እንደኮበለለ ተነገረው። ፈርዖንና አገልጋዮቹም ስለ ሕዝቡ የነበራቸውን ሐሳብ ወዲያው በመቀየር “ምን ማድረጋችን ነው? እስራኤላውያን ባሪያ ሆነው እንዳያገለግሉን የለቀቅናቸው ምን ነክቶን ነው?” አሉ።
በመሆኑም ፈርዖን የጦር ሠረገሎቹ እንዲዘጋጁለት አደረገ፤ ሠራዊቱንም ከጎኑ አሰለፈ።
ከዚያም 600 የተመረጡ ሠረገሎችንና ሌሎች የግብፅ ሠረገሎችን ሁሉ ይዞ ተነሳ፤ በእያንዳንዱም ሠረገላ ላይ ተዋጊዎች ነበሩ።
በዚህ መንገድ ይሖዋ የግብፁ ንጉሥ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ እስራኤላውያን ወጥተው በልበ ሙሉነት እየሄዱ ሳሉ ፈርዖን እነሱን ማሳደዱን ተያያዘው።
ግብፃውያኑ ተከታተሏቸው፤ እስራኤላውያን በበዓልጸፎን ፊት ለፊት በባሕሩ አጠገብ ባለው በፊሃሂሮት ሰፍረው ሳሉም የፈርዖን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞቹና ሠራዊቱ በሙሉ ደረሱባቸው።
ፈርዖን ወደ እነሱ ሲቀርብ እስራኤላውያን ቀና ብለው ተመለከቱ፤ ግብፃውያኑ እነሱን እየተከታተሏቸው ነበር። እስራኤላውያንም ተሸበሩ፤ ወደ ይሖዋም ይጮኹ ጀመር።
እነሱም ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እዚህ ምድረ በዳ ውስጥ እንድንሞት ያመጣኸን በግብፅ የመቃብር ቦታ ጠፍቶ ነው? ከግብፅ መርተህ በማውጣት ምን ያደረግክልን ነገር አለ?
በግብፅ ሳለን ‘እባክህ ተወን፤ አርፈን ግብፃውያንን እናገልግል’ ብለንህ አልነበረም? እዚህ ምድረ በዳ ውስጥ ከመሞት ግብፃውያንን ብናገለግል ይሻለን ነበር።”
በዚህ ጊዜ ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ። ጸንታችሁ ቁሙ፤ በዛሬው ዕለት ይሖዋ ለእናንተ ሲል የሚፈጽመውን የእሱን ማዳን እዩ። ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያን ዳግመኛ አታዩአቸውም፤ በጭራሽ አታዩአቸውም።
ይሖዋ ራሱ ስለ እናንተ ይዋጋል፤ ብቻ እናንተ ዝም በሉ።”
በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለምን ወደ እኔ ትጮኻለህ? እስራኤላውያን ድንኳናቸውን ነቅለው እንዲጓዙ ንገራቸው።
አንተም እስራኤላውያን በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት እንዲሻገሩ በትርህን አንሳና እጅህን በባሕሩ ላይ ሰንዝር፤ ባሕሩንም ክፈለው።
እኔ ደግሞ የግብፃውያን ልብ እንዲደነድን ስለምፈቅድ እስራኤላውያንን ተከትለው ይገባሉ፤ እኔም ፈርዖንን፣ ሠራዊቱን ሁሉ፣ የጦር ሠረገሎቹንና ፈረሰኞቹን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን እጎናጸፋለሁ።
ፈርዖንን፣ የጦር ሠረገሎቹንና ፈረሰኞቹን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን በምጎናጸፍበት ጊዜ ግብፃውያን እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።”
ከዚያም ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ፊት ይሄድ የነበረው የእውነተኛው አምላክ መልአክ ከዚያ ተነስቶ ወደኋላቸው ሄደ፤ ከፊታቸው የነበረውም የደመና ዓምድ ወደኋላቸው ሄዶ በስተ ጀርባቸው ቆመ።
በመሆኑም የደመናው ዓምድ በግብፃውያንና በእስራኤላውያን መካከል ሆነ። ዓምዱ በአንደኛው በኩል ጭልም ያለ ደመና ነበር። በሌላኛው በኩል ደግሞ ለሌሊቱ ብርሃን ይሰጥ ነበር። ስለሆነም ሌሊቱን ሙሉ አንደኛው ወገን ወደ ሌላኛው ወገን መቅረብ አልቻለም።
ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤ ይሖዋም ሌሊቱን ሙሉ ኃይለኛ የምሥራቅ ነፋስ በማምጣት ባሕሩ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፤ የባሕሩንም ወለል ወደ ደረቅ መሬት ለወጠው፤ ውኃውም ተከፈለ።
በመሆኑም እስራኤላውያን ውኃው በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ቆሞ በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተሻገሩ።
ግብፃውያኑም እነሱን ማሳደዳቸውን ተያያዙት፤ የፈርዖን ፈረሶች፣ የጦር ሠረገሎችና ፈረሰኞች ሁሉ ተከትለዋቸው ወደ ባሕሩ መሃል ገቡ።
በማለዳውም ክፍለ ሌሊት ይሖዋ በእሳትና በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፤ የግብፃውያንም ሠራዊት ግራ እንዲጋባ አደረገ።
ሠረገሎቻቸውን መንዳት አስቸጋሪ እንዲሆንባቸው የሠረገሎቻቸውን መንኮራኩሮች አወላለቀባቸው፤ ግብፃውያኑም “ይሖዋ እስራኤላውያንን በመደገፍ ግብፃውያንን እየተዋጋላቸው ስለሆነ ከእስራኤላውያን ፊት እንሽሽ” አሉ።
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ውኃው በግብፃውያን፣ በጦር ሠረገሎቻቸውና በፈረሰኞቻቸው ላይ ተመልሶ እንዲመጣባቸው እጅህን በባሕሩ ላይ ሰንዝር” አለው።
ሙሴም ወዲያውኑ እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤ ሊነጋጋ ሲልም ባሕሩ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ተመለሰ። ግብፃውያንም ውኃው እንዳይደርስባቸው ለመሸሽ ሲሞክሩ ይሖዋ ግብፃውያኑን ባሕሩ መሃል ጣላቸው።
ውኃውም ተመልሶ እስራኤላውያንን ተከትለው የገቡትን የጦር ሠረገሎችና ፈረሰኞች እንዲሁም የፈርዖንን ሠራዊት በሙሉ አለበሳቸው። ከእነሱም መካከል አንድም የተረፈ የለም።
እስራኤላውያን ግን ውኃው በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ቆሞ በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተጓዙ።
በዚህ መንገድ ይሖዋ በዚያ ቀን እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ አዳነ፤ እስራኤላውያንም የግብፃውያን ሬሳ በባሕሩ ዳርቻ ላይ ወድቆ ተመለከቱ።
በተጨማሪም እስራኤላውያን ይሖዋ ግብፃውያንን የመታበትን ኃያል ክንድ ተመለከቱ፤ ሕዝቡም ይሖዋን መፍራት ጀመረ፤ በይሖዋና በአገልጋዩ በሙሴም አመነ።
“አንተም ለእኔ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ ወንድምህን አሮንን ከወንዶች ልጆቹ ጋር ከእስራኤላውያን መካከል ለይተህ ትጠራዋለህ፤ አሮንን እንዲሁም የአሮንን ወንዶች ልጆች ናዳብን፣ አቢሁን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ትጠራቸዋለህ።
ለወንድምህ ለአሮንም ክብርና ውበት የሚያጎናጽፉትን ቅዱስ ልብሶች ትሠራለታለህ።
የጥበብ መንፈስ የሞላሁባቸውን ጥሩ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ አንተ ራስህ ታናግራቸዋለህ፤ እነሱም አሮን ለእኔ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ እሱን ለመቀደስ ልብሶቹን ይሠሩለታል።
“የሚሠሯቸው ልብሶችም እነዚህ ናቸው፦ የደረት ኪስ፣ ኤፉድ፣ እጅጌ የሌለው ቀሚስ፣ በካሬ ንድፍ የተሸመነ ረጅም ቀሚስ፣ ጥምጥምና መቀነት፤ ወንድምህ አሮንና ወንዶች ልጆቹ ካህን ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነዚህን ቅዱስ ልብሶች ይሠሩላቸዋል።
እነዚህ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ወርቁን፣ ሰማያዊውን ክር፣ ሐምራዊውን ሱፍ፣ ደማቁን ቀይ ማግና ጥሩውን በፍታ ተጠቅመው ይሠሯቸዋል።
“ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ኤፉዱን ያዘጋጃሉ፤ ኤፉዱም ጥልፍ የተጠለፈበት ይሁን።
ኤፉዱ ላዩ ላይ የተጣበቁ ሁለት የትከሻ ጥብጣቦች የሚኖሩት ሲሆን እነሱም ኤፉዱን በሁለቱ ጫፎቹ ላይ ያያይዙታል።
ኤፉዱ ወዲያ ወዲህ እንዳይንቀሳቀስ ለማሰር የሚያገለግለው ከኤፉዱ ጋር የተያያዘው በሽመና የተሠራው መቀነት ልክ እንደ ኤፉዱ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ መሆን ይኖርበታል።
“ሁለት የኦኒክስ ድንጋዮችን ወስደህ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች ትቀርጽባቸዋለህ፤
በትውልዳቸው ቅደም ተከተል መሠረት የስድስቱን ስሞች በአንዱ ድንጋይ ላይ፣ የቀሩትን የስድስቱን ስሞች ደግሞ በሌላኛው ድንጋይ ላይ ትቀርጻለህ።
አንድ ቅርጽ አውጪ በድንጋይ ላይ ማኅተም እንደሚቀርጽ ሁሉ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ይቀርጽባቸዋል። ከዚያም በወርቅ አቃፊዎች ውስጥ እንዲቀመጡ ታደርጋለህ።
ለእስራኤል ልጆች እንደ መታሰቢያ ድንጋዮች ሆነው እንዲያገለግሉ ሁለቱን ድንጋዮች በኤፉዱ የትከሻ ጥብጣቦች ላይ ታስቀምጣቸዋለህ፤ አሮንም እንደ መታሰቢያ ሆነው እንዲያገለግሉ ስሞቻቸውን በሁለቱ የትከሻ ጥብጣቦች ላይ በይሖዋ ፊት ይሸከማል።
አንተም የወርቅ አቃፊዎችን
እንዲሁም እንደ ገመድ የተገመዱ ሁለት ሰንሰለቶችን ከንጹሕ ወርቅ ትሠራለህ፤ የተገመዱትንም ሰንሰለቶች ከአቃፊዎቹ ጋር አያይዛቸው።
“የፍርዱን የደረት ኪስ የጥልፍ ባለሙያ እንዲሠራው ታደርጋለህ። የደረት ኪሱ ልክ እንደ ኤፉዱ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ መሠራት ይኖርበታል።
ለሁለት በሚታጠፍበትም ጊዜ ቁመቱ አንድ ስንዝር፣ ወርዱ ደግሞ አንድ ስንዝር የሆነ ካሬ ይሁን።
የከበሩ ድንጋዮችን በአራት ረድፍ በማቀፊያ ውስጥ ታደርግበታለህ። በመጀመሪያው ረድፍ ሩቢ፣ ቶጳዝዮንና መረግድ ይደርደር።
በሁለተኛው ረድፍ በሉር፣ ሰንፔርና ኢያስጲድ ይደርደር።
በሦስተኛው ረድፍ ለሼም፣ አካትምና አሜቴስጢኖስ ይደርደር።
በአራተኛውም ረድፍ ክርስቲሎቤ፣ ኦኒክስና ጄድ ይደርደር። በወርቅ አቃፊዎችም ውስጥ ይቀመጡ።
ድንጋዮቹም የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች ማለትም 12ቱን በየስማቸው የሚወክሉ ይሆናሉ። ለ12ቱም ነገዶች ልክ ማኅተም በሚቀረጽበት መንገድ ለእያንዳንዳቸው በየስማቸው ይቀረጽላቸው።
“በደረት ኪሱም ላይ ከንጹሕ ወርቅ እንደተሠሩ ገመዶች የተጎነጎኑ ሰንሰለቶችን ትሠራለህ።
ለደረት ኪሱም ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህ ሁለቱን ቀለበቶች ከሁለቱ የደረት ኪሱ ጫፎች ጋር ታያይዛቸዋለህ።
ሁለቱን የወርቅ ገመዶችም በደረት ኪሱ ዳርና ዳር ባሉት ጫፎች ላይ በሚገኙት በሁለቱ ቀለበቶች ውስጥ ታስገባቸዋለህ።
የሁለቱን ገመዶች ሁለት ጫፎች በሁለቱ አቃፊዎች ውስጥ ታስገባለህ፤ እነሱንም ከኤፉዱ የትከሻ ጥብጣቦች ጋር በፊት በኩል ታያይዛቸዋለህ።
ሁለት የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርተህ በኤፉዱ በኩል በሚውለው በደረት ኪሱ ውስጠኛ ጠርዝ ላይ ባሉት ሁለት ጫፎች ላይ ታደርጋቸዋለህ።
ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርተህ በኤፉዱ በፊት በኩል ከሁለቱ የትከሻ ጥብጣቦች በታች ኤፉዱ በተጋጠመበት ቦታ አካባቢ፣ በሽመና ከተሠራው የኤፉዱ መቀነት በላይ አድርጋቸው።
የደረት ኪሱ ከቦታው እንዳይንቀሳቀስ የደረት ኪሱ ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ገመድ መያያዝ ይኖርባቸዋል። ይህም የደረት ኪሱ ከመቀነቱ በላይ ከኤፉዱ ላይ ሳይንቀሳቀስ እንዲቀመጥ ያደርገዋል።
“አሮን ወደ ቅድስቱ በሚገባበት ጊዜ በይሖዋ ፊት ቋሚ መታሰቢያ እንዲሆን በልቡ ላይ በሚገኘው የፍርድ የደረት ኪስ የእስራኤልን ልጆች ስሞች ይሸከም።
ኡሪሙንና ቱሚሙን በፍርድ የደረት ኪሱ ውስጥ ታስቀምጣቸዋለህ፤ አሮን በይሖዋ ፊት ለመቅረብ በሚገባበት ጊዜ በልቡ ላይ መሆን አለባቸው፤ አሮን በይሖዋ ፊት በሚቀርብበት ጊዜ ለእስራኤላውያን ፍርድ መስጫውን ዘወትር በልቡ ላይ ይሸከም።