text
stringlengths
4
267
ባወጧቸውም ድንጋዮች ቦታ ሌሎች ድንጋዮችን ያስገቡ፤ ቤቱም በአዲስ ምርጊት እንዲለሰን ያድርግ።
“ድንጋዮቹ ተሰርስረው ከወጡና ቤቱ ተፈቅፍቆ ዳግመኛ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ እንደገና ተመልሶ በቤቱ ላይ ከታየ
ካህኑ ገብቶ ይመረምረዋል። ብክለቱ በቤቱ ውስጥ ተስፋፍቶ ከሆነ ይህ በቤቱ ላይ የወጣ አደገኛ ደዌ ነው። ቤቱ ርኩስ ነው።
ቤቱ ይኸውም ድንጋዮቹ፣ እንጨቶቹ፣ ልስኑና ምርጊቱ እንዲፈርስ ያደርጋል፤ ከከተማዋ ውጭ በሚገኝ ርኩስ የሆነ ስፍራም እንዲጣል ያደርጋል።
ሆኖም ቤቱ ታሽጎ በነበረበት በየትኛውም ቀን ወደዚያ ቤት የገባ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤
እዚያ ቤት ውስጥ የተኛ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ እንዲሁም እዚያ ቤት ውስጥ የበላ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል።
“ይሁንና ካህኑ መጥቶ ሲያየው ቤቱ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ በቤቱ ውስጥ ካልተስፋፋ ቤቱ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል፤ ምክንያቱም ብክለቱ ጠፍቷል።
ቤቱንም ከርኩሰት ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ማግና ሂሶጵ ይወስዳል።
አንደኛዋንም ወፍ ከወራጅ ውኃ የተቀዳ ውኃ ባለበት የሸክላ ዕቃ ውስጥ ያርዳታል።
ከዚያም የአርዘ ሊባኖስ እንጨቱን፣ ሂሶጱን፣ ደማቁን ቀይ ማግና በሕይወት ያለችውን ወፍ ወስዶ በታረደችው ወፍ ደምና ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ ውስጥ ይነክራቸዋል፤ ወደ ቤቱም ሰባት ጊዜ ይርጨው።
ቤቱንም በወፏ ደም፣ ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ፣ በሕይወት ባለችው ወፍ፣ በአርዘ ሊባኖስ እንጨቱ፣ በሂሶጱና በደማቁ ቀይ ማግ ከርኩሰት ያነጻዋል።
በሕይወት ያለችውንም ወፍ ከከተማዋ ውጭ ወደ ሜዳ ይለቃታል፤ ለቤቱም ያስተሰርይለታል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል።
“ከማንኛውም ዓይነት የሥጋ ደዌ፣ በራስ ቆዳ ወይም በጢም ላይ ከሚወጣ ቁስል፣
በልብስ ወይም በቤት ላይ ከሚወጣ ደዌ፣
ከእባጭ፣ ከእከክና ከቋቁቻ ጋር በተያያዘ
አንድ ነገር ርኩስ ወይም ንጹሕ መሆኑን ለመወሰን የሚያገለግለው ሕግ ይህ ነው። የሥጋ ደዌን በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው።”
በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
“ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ፣ እስራኤላውያን የሚያመጧቸውን ቅዱስ ነገሮች የሚይዙበትን መንገድ በተመለከተ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ለእኔ የተቀደሱ አድርገው በለዩአቸው ነገሮች ቅዱስ ስሜን እንዳያረክሱ ንገራቸው። እኔ ይሖዋ ነኝ።
እንዲህ በላቸው፦ ‘በትውልዶቻችሁ ሁሉ ከልጆቻችሁ መካከል ረክሶ እያለ እስራኤላውያን ለይሖዋ የተቀደሱ አድርገው ወደለዩአቸው ቅዱስ ነገሮች የሚቀርብ ሰው ካለ ያ ሰው ከፊቴ እንዲጠፋ ይደረግ። እኔ ይሖዋ ነኝ።
ከአሮን ልጆች መካከል የሥጋ ደዌ ያለበት ወይም ፈሳሽ የሚወጣው ማንኛውም ሰው ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት የለበትም፤ የሞተን ሰው በመንካት የረከሰን ሰው የነካ ወይም ከሰውነቱ የዘር ፈሳሽ የሚወጣው
አሊያም ርኩስ የሆነን የሚርመሰመስ ፍጡር የነካ ወይም ደግሞ ሊያረክሰው በሚችል በማንኛውም ዓይነት ነገር የረከሰን ሰው የነካ ሰው ከእነዚህ ነገሮች አይብላ።
እንደነዚህ ያሉ ነገሮችን የነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውንም በውኃ እስካልታጠበ ድረስ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት አይችልም።
ፀሐይ በምትጠልቅበት ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያ በኋላ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት ይችላል፤ ምክንያቱም ይህ ምግቡ ነው።
በተጨማሪም እንዳይረክስ ሞቶ የተገኘን ወይም አውሬ የቦጫጨቀውን የማንኛውንም እንስሳ ሥጋ መብላት የለበትም። እኔ ይሖዋ ነኝ።
“‘ለእኔ የገቡትን ግዴታ ባለመጠበቅ በራሳቸው ላይ ኃጢአት እንዳያመጡና በዚህም የተነሳ ቅዱስ የሆነውን ነገር በማርከስ እንዳይሞቱ የገቡትን ግዴታ መጠበቅ አለባቸው። የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ ነኝ።
“‘ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው ቅዱስ የሆነውን የትኛውንም ነገር መብላት የለበትም። ካህኑ ቤት በእንግድነት ያረፈ ሰው ወይም ቅጥር ሠራተኛ ቅዱስ ከሆነው ነገር መብላት የለበትም።
ሆኖም አንድ ካህን በገዛ ገንዘቡ አንድ ሰው ቢገዛ ያ ሰው ከምግቡ መካፈል ይችላል። በቤቱ የተወለዱ ባሪያዎችም ከእሱ ምግብ መካፈል ይችላሉ።
የአንድ ካህን ሴት ልጅ፣ ካህን ያልሆነን ሰው ብታገባ በመዋጮ ከተሰጡት ቅዱስ የሆኑ ነገሮች መብላት አትችልም።
ይሁንና የአንድ ካህን ሴት ልጅ፣ ባሏ ቢሞት ወይም ብትፋታና ልጅ ባይኖራት እንደ ወጣትነቷም ጊዜ ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ ከአባቷ ምግብ መብላት ትችላለች፤ ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው ግን ከዚያ መብላት የለበትም።
“‘አንድ ሰው ቅዱስ ከሆነው ነገር ባለማወቅ ቢበላ የቅዱሱን ነገር ዋጋ አንድ አምስተኛ በመጨመር ቅዱስ የሆነውን መባ ለካህኑ ይስጥ።
ካህናቱ፣ እስራኤላውያን ለይሖዋ መዋጮ አድርገው የሰጧቸውን ቅዱስ ነገሮች ማርከስ
እንዲሁም ሕዝቡ ያመጣቸውን ቅዱስ ነገሮች እንዲበላና በራሱ ላይ ቅጣት የሚያስከትል በደል እንዲፈጽም ማድረግ የለባቸውም፤ ምክንያቱም የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ ነኝ።’”
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦
“ለአሮን፣ ለወንዶች ልጆቹና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ስእለቱን ለመፈጸም ወይም የፈቃደኝነት መባ ለማቅረብ ሲል የሚቃጠል መባውን ለይሖዋ የሚያቀርብ አንድ እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል ውስጥ የሚኖር አንድ የባዕድ አገር ሰው
ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፈለገ መሥዋዕቱ ከመንጋው፣ ከጠቦቶቹ ወይም ከፍየሎቹ መካከል የተወሰደ እንከን የሌለበት ተባዕት መሆን ይኖርበታል።
ተቀባይነት ስለማያስገኝላችሁ እንከን ያለበትን ማንኛውንም ነገር አታቅርቡ።
“‘አንድ ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም የፈቃደኝነት መባ ለመስጠት ሲል ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት ቢያቀርብ መሥዋዕቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከከብቶቹ ወይም ከመንጋው መካከል እንከን የሌለበትን ማቅረብ ይኖርበታል። ምንም ዓይነት እንከን ሊኖርበት አይገባም።
መባ ሆኖ የሚቀርበው እንስሳ ዕውር ወይም ሰባራ አሊያም ቆራጣ ወይም ደግሞ ኪንታሮት አሊያም እከክ ወይም ጭርት ያለበት መሆን የለበትም፤ እንዲህ ያለውን እንስሳ ለይሖዋ ማቅረብ የለባችሁም ወይም እንዲህ ያለውን መባ ለይሖዋ በመሠዊያው ላይ ማቅረብ የለባችሁም።
አንዱ እግሩ የረዘመን ወይም ያጠረን በሬ ወይም በግ የፈቃደኝነት መባ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፤ የስእለት መባ አድርጋችሁ ብታቀርቡት ግን ተቀባይነት አይኖረውም።
የዘር ፍሬው ጉዳት የደረሰበትን ወይም የተቀጠቀጠን አሊያም ተሰንጥቆ የወጣን ወይም የተቆረጠን እንስሳ ለይሖዋ ማቅረብ የለባችሁም፤ በምድራችሁ እነዚህን የመሰሉ እንስሳትን ማቅረብ አይኖርባችሁም።
እነዚህ ጉድለትና እንከን ስላለባቸው ከመካከላቸው የትኛውንም ከባዕድ ሰው እጅ በመቀበል የአምላካችሁ ምግብ አድርጋችሁ ማቅረብ የለባችሁም። ተቀባይነት አያገኙላችሁም።’”
በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
“ጥጃ ወይም የበግ ግልገል አሊያም የፍየል ግልገል በሚወለድበት ጊዜ ለሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቆይ፤ ከስምንተኛው ቀን አንስቶ ግን መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ሆኖ ቢቀርብ ተቀባይነት ይኖረዋል።
ላምን ከጥጃዋ ወይም በግን ከግልገሏ ጋር በአንድ ቀን አትረዱ።
“ለይሖዋ የምሥጋና መሥዋዕት የምትሠዉ ከሆነ ተቀባይነት በሚያስገኝላችሁ መንገድ ልትሠዉት ይገባል።
መሥዋዕቱ በዚያው ዕለት መበላት ይኖርበታል። ከእሱም ላይ ምንም አስተርፋችሁ አታሳድሩ። እኔ ይሖዋ ነኝ።
“እናንተም ትእዛዛቴን ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው። እኔ ይሖዋ ነኝ።
ቅዱሱን ስሜን አታርክሱ፤ እኔ በእስራኤላውያን መካከል ልቀደስ ይገባኛል። የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ነኝ፤
አምላክ መሆኔን ለእናንተ ለማሳየት ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ነኝ። እኔ ይሖዋ ነኝ።”
ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦
“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብላችሁ ንገሯቸው፦ ‘አንድ ወንድ ከብልቱ ፈሳሽ የሚወጣ ከሆነ ይህ ፈሳሽ ርኩስ ያደርገዋል።
ሰውየው በፈሳሹ የተነሳ ርኩስ ነው፤ ፈሳሹ ከብልቱ እየፈሰሰ ቢሆንም ወይም ብልቱን ቢዘጋው ሰውየው ርኩስ ነው።
“‘ፈሳሽ የሚወጣው ሰው የተኛበት አልጋም ርኩስ ይሆናል፤ ይህ ሰው የተቀመጠበት ማንኛውም ነገርም ርኩስ ይሆናል።
የሰውየውን አልጋ የነካ ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
እንዲሁም ፈሳሽ የሚወጣው ሰው ተቀምጦበት በነበረ ነገር ላይ የተቀመጠ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ፈሳሽ የሚወጣውን ሰው፣ ሰውነት የነካ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ፈሳሽ የሚወጣው ሰው ንጹሕ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ የተተፋበት ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ፈሳሽ የሚወጣው ሰው የተቀመጠበት ኮርቻ ርኩስ ይሆናል።
ይህ ሰው የተቀመጠበትን የትኛውንም ነገር የነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እነዚህን ነገሮች የያዘ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ፈሳሽ የሚወጣው ሰው እጆቹን በውኃ ሳይታጠብ አንድን ሰው ቢነካ የተነካው ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ፈሳሽ የሚወጣው ሰው የነካው የሸክላ ዕቃ ይሰበር፤ ማንኛውም የእንጨት ዕቃ ደግሞ በውኃ ይታጠብ።
“‘እንግዲህ ፈሳሹ ቢቆምና ሰውየው ከፈሳሹ ቢነጻ ንጹሕ ለመሆን ሰባት ቀን ይቁጠር፤ ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።
በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን ይውሰድ፤ እነዚህንም ይዞ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት በመቅረብ ለካህኑ ይስጥ።
ካህኑም አንዱን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም ስለ ፈሳሹ ለሰውየው በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል።
“‘አንድ ወንድ ዘር ቢፈሰው ገላውን በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
የፈሰሰው ዘር የነካውን ማንኛውንም ዓይነት ልብስ ወይም ቁርበት በውኃ ማጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
“‘አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ቢተኛና ዘሩ ቢፈስ ገላቸውን በውኃ መታጠብ አለባቸው፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናሉ።
“‘አንዲት ሴት ከሰውነቷ ደም ቢፈሳት በወር አበባዋ የተነሳ ርኩስ እንደሆነች ለሰባት ቀን ትቀጥላለች፤ እንዲሁም እሷን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።
በወር አበባዋ የተነሳ ርኩስ በሆነችባቸው ጊዜያት የተኛችበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም የተቀመጠችበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል።
አልጋዋን የነካ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
እሷ ተቀምጣበት የነበረውን የትኛውንም ነገር የነካ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
የተቀመጠችው አልጋ ላይም ይሁን ሌላ ነገር ላይ ሰውየው ያን መንካቱ እስከ ማታ ድረስ እንዲረክስ ያደርገዋል።
አንድ ወንድ ከእሷ ጋር ቢተኛና በወር አበባዋ ቢረክስ ሰውየው ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤ የተኛበት አልጋም ርኩስ ይሆናል።
“‘አንዲት ሴት የወር አበባዋ ከሚመጣበት ከተለመደው ጊዜ ውጭ ለብዙ ቀናት ደም ቢፈሳት ወይም በወር አበባዋ ወቅት ከወትሮው ረዘም ላለ ጊዜ ደም ቢፈሳት የወር አበባዋ በሚመጣባቸው ቀናት እንደሚሆነው ፈሳሽ በሚፈሳት ጊዜ ሁሉ ርኩስ ትሆናለች።
ፈሳሽ በሚፈሳት ቀናት ሁሉ የተኛችበት አልጋ በወር አበባዋ የተነሳ ርኩስ በሆነችባቸው ጊዜያት እንደተኛችበት አልጋ ይሆናል፤ እንዲሁም የተቀመጠችበት ማንኛውም ነገር በወር አበባዋ ወቅት ርኩስ እንደሚሆን ሁሉ በዚህ ጊዜም ርኩስ ይሆናል።
እነዚህን ነገሮች የነካ ማንኛውም ሰው ርኩስ ይሆናል፤ ልብሶቹንም ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
“‘ይሁን እንጂ ይፈሳት ከነበረው ፈሳሽ በምትነጻበት ጊዜ ለራሷ ሰባት ቀን ትቆጥራለች፤ ከዚያ በኋላ ንጹሕ ትሆናለች።
በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን ትውሰድ፤ እነዚህንም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወዳለው ወደ ካህኑ ታመጣቸዋለች።
ካህኑም አንዱን ለኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ ለሚቃጠል መባ ያደርገዋል፤ ካህኑም የሚፈሳትን ርኩስ ፈሳሽ አስመልክቶ ለሴትየዋ በይሖዋ ፊት ያስተሰርይላታል።
“‘በመካከላቸው ያለውን የማደሪያ ድንኳኔን በማርከስ በርኩሰታቸው እንዳይሞቱ በዚህ መንገድ እስራኤላውያንን ከርኩሰታቸው ለዩአቸው።
“‘ፈሳሽ የሚወጣውን ወንድ፣ ዘሩ በመፍሰሱ የተነሳ ርኩስ የሆነውን ወንድ፣
በወር አበባዋ ላይ በመሆኗ ርኩስ የሆነችን ሴት፣ ወንድም ሆነ ሴት ከሰውነቱ ፈሳሽ የሚወጣውን ማንኛውንም ሰው እንዲሁም ርኩስ ከሆነች ሴት ጋር የተኛን ወንድ በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው።’”
ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ሰው ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ እንዲህ መደረግ ይኖርበታል፦
“‘የተቀባው ካህን ኃጢአት ቢሠራና ሕዝቡ በደለኛ እንዲሆን ቢያደርግ ለፈጸመው ኃጢአት እንከን የሌለበትን ወይፈን የኃጢአት መባ አድርጎ ለይሖዋ ያቅርብ።
ወይፈኑን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወደ ይሖዋ ፊት ያመጣዋል፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናል፤ ወይፈኑንም በይሖዋ ፊት ያርደዋል።
ከዚያም የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም የተወሰነ ወስዶ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይዞ ይገባል፤
ካህኑም ጣቱን ደሙ ውስጥ ነክሮ ደሙን በቅዱሱ ስፍራ መጋረጃ ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።
በተጨማሪም ካህኑ ከደሙ የተወሰነውን ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በይሖዋ ፊት የሚገኘውን ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን የወይፈኑን ደም በሙሉ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሰዋል።
“‘ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብና በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ ጨምሮ ለኃጢአት መባ የቀረበውን ወይፈን ስብ በሙሉ ከላዩ ላይ ያነሳል፤
እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ላይ ያለውን በሽንጡ አካባቢ የሚገኝ ስብ ያነሳል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል።
ይህም ለኅብረት መሥዋዕት ከሚቀርበው በሬ ላይ ከሚነሳው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። ካህኑም የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል።
“‘ሆኖም የወይፈኑን ቆዳ እንዲሁም ሥጋውን በሙሉ ከጭንቅላቱ፣ ከእግሮቹ፣ ከሆድ ዕቃውና ከፈርሱ ጋር
እንዲሁም ከወይፈኑ የቀረውን በሙሉ ከሰፈሩ ውጭ ወዳለው አመድ ወደሚደፋበት ንጹሕ የሆነ ቦታ ይወስደዋል፤ በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ አድርጎም ያቃጥለዋል። አመዱ በሚደፋበት ቦታ ላይ ይቃጠል።
“‘መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ባለማወቅ ኃጢአት በመሥራቱ በደለኛ ቢሆንና ጉባኤው ግን ይሖዋ አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን መፈጸሙን ባይገነዘብ፣
በኋላም ኃጢአቱ ቢታወቅ ጉባኤው ለኃጢአት መባ የሚሆን ወይፈን ያቅርብ፤ ወደ መገናኛ ድንኳኑም ፊት ያምጣው።
የማኅበረሰቡ ሽማግሌዎች በይሖዋ ፊት እጃቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናሉ፤ ወይፈኑም በይሖዋ ፊት ይታረዳል።
“‘ከዚያም የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም የተወሰነ ወስዶ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይዞ ይገባል።
ካህኑም ጣቱን ደሙ ውስጥ ነክሮ የተወሰነውን በመጋረጃው ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።
የተወሰነውንም ደም ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በይሖዋ ፊት የሚገኘውን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን ደም በሙሉ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሰዋል።