text stringlengths 4 267 |
|---|
ስቡንም በሙሉ አንስቶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። |
በወይፈኑ ላይ ለኃጢአት መባ እንዲሆን በቀረበው በሌላኛው ወይፈን ላይ እንዳደረገው ሁሉ ያደርጋል። በዚህኛውም ላይ የሚያደርገው ይህንኑ ይሆናል፤ ካህኑም ለእነሱ ያስተሰርይላቸዋል፤ እነሱም ይቅር ይባላሉ። |
ወይፈኑንም ከሰፈሩ ውጭ እንዲወሰድ ካደረገ በኋላ ልክ የመጀመሪያውን ወይፈን እንዳቃጠለው ሁሉ ይሄኛውንም ያቃጥለዋል። ይህ ስለ ጉባኤው የሚቀርብ የኃጢአት መባ ነው። |
“‘አንድ አለቃ አምላኩ ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ ኃጢአት ሠርቶ በደለኛ ቢሆን |
ወይም ትእዛዙን በመተላለፍ ኃጢአት እንደሠራ ቢያውቅ እንከን የሌለበትን ተባዕት የፍየል ጠቦት መባ አድርጎ ያምጣ። |
እጁንም በፍየል ጠቦቱ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም የሚቃጠለው መባ በይሖዋ ፊት ዘወትር በሚታረድበት ስፍራ ያርደዋል። ይህ የኃጢአት መባ ነው። |
ካህኑም ለኃጢአት መባ ከቀረበው እንስሳ ደም ላይ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን ደሙን የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሳል። |
ስቡንም በሙሉ ልክ እንደ ኅብረት መሥዋዕቱ ስብ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል፤ ካህኑም የእሱን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። |
“‘በምድሩ ከሚኖሩ ሕዝቦች መካከል ማንኛውም ሰው ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራና በደለኛ ቢሆን፣ |
በኋላም የሠራውን ኃጢአት ቢያውቅ ለፈጸመው ኃጢአት እንከን የሌለባትን እንስት የፍየል ጠቦት መባ አድርጎ ያምጣ። |
እጁንም ለኃጢአት መባ በቀረበችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም ለኃጢአት መባ የቀረበችውን እንስሳ የሚቃጠለው መባ በሚታረድበት ስፍራ ያርዳታል። |
ካህኑም ከደሙ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን ደሙን በሙሉ በመሠዊያው ሥር ያፈሰዋል። |
ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይ ስቡ እንደሚነሳ ሁሉ ከዚህ ላይም ስቡን በሙሉ ያነሳዋል፤ ካህኑም ስቡ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሰጥ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል፤ ካህኑም ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። |
“‘ሆኖም የኃጢአት መባ አድርጎ የሚያቀርበው የበግ ጠቦት ከሆነ እንከን የሌለባትን እንስት የበግ ጠቦት ማምጣት አለበት። |
እጁንም ለኃጢአት መባ በቀረበችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም እንስሳዋን የሚቃጠለው መባ በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአት መባ አድርጎ ያርዳታል። |
ካህኑም ለኃጢአት መባ ከቀረበችው እንስሳ ደም ላይ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን ደሙን በሙሉ በመሠዊያው ሥር ያፈሰዋል። |
የኅብረት መሥዋዕት ሆኖ ከሚቀርበው የበግ ጠቦት ላይ ስቡ እንደሚነሳ ሁሉ ከዚህ ላይም ስቡን በሙሉ ያነሳዋል፤ እሱም በመሠዊያው ላይ ባሉት ለይሖዋ በእሳት በሚቀርቡት መባዎች ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል። ካህኑም ሰውየው የሠራውን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። |
ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ልጁን ለሞሎክ የሚሰጥ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም እስራኤል ውስጥ የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ይገደል። የአገሩ ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉት። |
ልጆቹን ለሞሎክ ስለሰጠ እንዲሁም ቅዱሱን ስፍራዬን ስላረከሰና ቅዱሱን ስሜን ስላቃለለ እኔ ራሴ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። |
የአገሩ ሰዎች ሰውየው ልጁን ለሞሎክ በመስጠት የፈጸመውን ድርጊት አይተው እንዳላዩ ቢሆኑና ሳይገድሉት ቢቀሩ |
እኔ ራሴ በዚህ ሰውና በቤተሰቡ ላይ እነሳባቸዋለሁ። ያንን ሰውም ሆነ ከሞሎክ ጋር ምንዝር በመፈጸም የእሱን ፈለግ የተከተሉትን ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋቸዋለሁ። |
“‘አንድ ሰው ከመናፍስት ጠሪዎችና ከጠንቋዮች ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ወደ እነሱ ቢሄድ እኔ በዚያ ሰው ላይ በእርግጥ እነሳበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። |
“‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆንኩ ራሳችሁን ቀድሱ፤ ቅዱሳንም ሁኑ። |
ደንቦቼን ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው። የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ነኝ። |
“‘አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ማንኛውም ሰው ይገደል። አባቱን ወይም እናቱን ስለረገመ ደሙ በራሱ ላይ ነው። |
“‘ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ምንዝር የሚፈጽምን ሰው በተመለከተ እንዲህ ይደረግ፦ ከባልንጀራው ሚስት ጋር ምንዝር የሚፈጽም ሰው ይገደል፤ አመንዝራውም ሆነ አመንዝራይቱ ይገደሉ። |
ከአባቱ ሚስት ጋር የተኛ ሰው አባቱን ለኀፍረት ዳርጎታል። ሁለቱም ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። |
አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋር ቢተኛ ሁለቱም ይገደሉ። ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ድርጊት ፈጽመዋል። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። |
“‘አንድ ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱም አስጸያፊ ድርጊት ፈጽመዋል። ስለዚህ ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። |
“‘አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቷን ቢያገባ፣ ይህ ጸያፍ ድርጊት ነው። ይህ ጸያፍ ምግባር በመካከላችሁ እንዳይቀጥል እሱንም ሆነ እነሱን በእሳት ያቃጥሏቸው። |
“‘አንድ ሰው ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም ይገደል፤ እንስሳውንም ግደሉት። |
አንዲት ሴት የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ ማንኛውም እንስሳ ብትቀርብ ሴትየዋንም ሆነ እንስሳውን ግደል፤ ሁለቱም ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። |
“‘አንድ ሰው ከእህቱ ማለትም ከአባቱ ሴት ልጅ ወይም ከእናቱ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽምና እርቃኗን ቢያይ፣ እሷም የእሱን እርቃን ብታይ ይህ አሳፋሪ ድርጊት ነው። በሕዝቦቻቸው ልጆች ፊት እንዲጠፉ ይደረጉ። እህቱን ለኀፍረት ዳርጓል። ለፈጸመው ጥፋት ይጠየቅበታል። |
“‘አንድ ሰው በወር አበባዋ ወቅት ከአንዲት ሴት ጋር ቢተኛና ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም እሱም ሆነ እሷ የሚፈሰውን ደሟን ገልጠዋል። ስለሆነም ሁለቱም ከሕዝቦቻቸው መካከል ተለይተው እንዲጠፉ ይደረጉ። |
“‘ከእናትህ እህት ወይም ከአባትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም ይህ የሥጋ ዘመድን ለኀፍረት መዳረግ ነው። ለፈጸሙት ጥፋት ይጠየቁበታል። |
ከአጎቱ ሚስት ጋር የተኛ ሰው አጎቱን ለኀፍረት ዳርጓል። ለፈጸሙት ኃጢአት ይጠየቁበታል። ልጅ ሳይኖራቸው ይሙቱ። |
አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ቢወስድ ይህ አስጸያፊ ድርጊት ነው። ወንድሙን ለኀፍረት ዳርጓል። ያለልጅም ይቅሩ። |
“‘ትኖሩባት ዘንድ እናንተን የማስገባባት ምድር እንዳትተፋችሁ ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ሁሉ ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው። |
ከፊታችሁ አባርሬ የማስወጣቸው ብሔራት በሚመሩባቸው ደንቦች አትሂዱ፤ ምክንያቱም እነሱ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርገዋል፤ እኔም እጸየፋቸዋለሁ። |
በመሆኑም እንዲህ አልኳችሁ፦ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እኔ ደግሞ ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር እንድትወርሷት እሰጣችኋለሁ። ከሕዝቦች የለየኋችሁ አምላካችሁ ይሖዋ እኔ ነኝ።” |
ንጹሕ በሆነውና ርኩስ በሆነው እንስሳ እንዲሁም ርኩስ በሆነውና ንጹሕ በሆነው ወፍ መካከል ልዩነት አድርጉ፤ እኔ ርኩስ ነው ብዬ በለየሁላችሁ እንስሳ ወይም ወፍ አሊያም መሬት ለመሬት በሚሄድ ማንኛውም ነገር ራሳችሁን አታርክሱ። |
እኔ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ለእኔ ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል፤ የእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ሕዝቦች ለየኋችሁ። |
“‘መናፍስት ጠሪ ወይም ጠንቋይ የሆነ ወንድ ወይም የሆነች ሴት ካሉ ይገደሉ። ሕዝቡ በድንጋይ ወግሮ ይግደላቸው። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።’” |
ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንዲት ሴት ብታረግዝና ወንድ ልጅ ብትወልድ በወር አበባዋ ወቅት እንደምትረክሰው ሁሉ ለሰባት ቀን ትረክሳለች። |
ሕፃኑም በስምንተኛው ቀን ይገረዛል። |
እሷም ከደም ራሷን ለማንጻት ለቀጣዮቹ 33 ቀናት ትቆያለች። የምትነጻባቸው ቀናት እስኪያበቁ ድረስ ምንም ዓይነት ቅዱስ ነገር መንካትም ሆነ ወደ ቅዱሱ ስፍራ መግባት የለባትም። |
“‘ሴት ልጅ ከወለደች ደግሞ በወር አበባዋ ወቅት እንደምትረክሰው ሁሉ ለ14 ቀን ትረክሳለች። ከደም ራሷን ለማንጻትም ለቀጣዮቹ 66 ቀናት ትቆያለች። |
ሴትየዋ ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ ወልዳ የመንጻቷ ጊዜ ሲያበቃ ለሚቃጠል መባ እንዲሆን አንድ ዓመት ገደማ የሆነው የበግ ጠቦት፣ ለኃጢአት መባ እንዲሆን ደግሞ አንድ የርግብ ጫጩት ወይም አንድ ዋኖስ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወደ ካህኑ ታመጣለች። |
እሱም መባዎቹን በይሖዋ ፊት በማቅረብ ያስተሰርይላታል፤ እሷም ከሚፈሳት ደም ትነጻለች። ወንድ ልጅም ሆነ ሴት ልጅ ለወለደች ሴት የሚሠራው ሕግ ይህ ነው። |
ሆኖም ሴትየዋ በግ ለማቅረብ አቅሟ የማይፈቅድላት ከሆነ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ታምጣ፤ አንዱ ለሚቃጠል መባ ሌላው ደግሞ ለኃጢአት መባ ይሆናል። ካህኑም ያስተሰርይላታል፤ እሷም ንጹሕ ትሆናለች።’” |
ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። |
ትኖሩበት በነበረው በግብፅ ምድር ያሉ ሰዎች እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነአን ምድር ያሉ ሰዎች እንደሚያደርጉትም አታድርጉ። እንዲሁም እነሱ የሚከተሏቸውን ደንቦች አትከተሉ። |
ድንጋጌዎቼን ተግባር ላይ አውሉ፤ ደንቦቼንም በመጠበቅ በእነሱ ሂዱ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። |
ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ጠብቁ፤ እንዲህ የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት ይኖራል። እኔ ይሖዋ ነኝ። |
“‘ከመካከላችሁ ማንም ሰው የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ ማንኛውም የቅርብ ዘመዱ አይቅረብ። እኔ ይሖዋ ነኝ። |
ከአባትህ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ከእናትህም ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። እሷ እናትህ ናት፤ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። |
“‘ከአባትህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። ይህ አባትህን ለኀፍረት መዳረግ ነው። |
“‘የአባትህ ልጅም ሆነች የእናትህ ልጅ ወይም በቤት የተወለደችም ሆነች በውጭ፣ ከእህትህ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። |
“‘ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እነሱ የአንተው እርቃን ናቸው። |
“‘የአባትህ ልጅ ከሆነችው ከአባትህ ሚስት ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እሷ እህትህ ናት። |
“‘ከአባትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። እሷ የአባትህ የሥጋ ዘመድ ናት። |
“‘ከእናትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እሷ የእናትህ የሥጋ ዘመድ ናት። |
“‘ከአባትህ ወንድም ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም እሱን ለኀፍረት አትዳርገው። እሷ ዘመድህ ናት። |
“‘ከልጅህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። እሷ የልጅህ ሚስት ናት፤ ከእሷ ጋር ግንኙነት መፈጸም የለብህም። |
“‘ከወንድምህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም ይህ ወንድምህን ለኀፍረት መዳረግ ነው። |
“‘ከአንዲት ሴትና ከሴት ልጇ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። ከወንድ ልጇ ሴት ልጅም ሆነ ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም እነሱን አትውሰድ። እነሱ የእሷ የቅርብ ዘመዶች ናቸው፤ ይህ ጸያፍ ድርጊት ነው። |
“‘እህቷ ጣውንቷ እንዳትሆን ሚስትህ በሕይወት እያለች ከእህቷ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። |
“‘አንዲት ሴት በወር አበባዋ ረክሳ እያለች ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ እሷ አትቅረብ። |
“‘ከጓደኛህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም ራስህን አታርክስ። |
“‘ከልጆችህ መካከል የትኛውንም ለሞሎክ እንዲሰጥ አታድርግ። በዚህ መንገድ የአምላክህን ስም አታርክስ። እኔ ይሖዋ ነኝ። |
“‘ከሴት ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ። ይህ አስጸያፊ ድርጊት ነው። |
“‘አንድ ወንድ ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም ራሱን አያርክስ፤ ሴትም ብትሆን ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ራሷን ለእንስሳ አታቅርብ። ይህ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ነገር ነው። |
“‘ከእነዚህ ነገሮች በየትኛውም ራሳችሁን አታርክሱ፤ ምክንያቱም ከእናንተ ፊት አባርሬ የማስወጣቸው ብሔራት ራሳቸውን በእነዚህ ነገሮች አርክሰዋል። |
ስለሆነም ምድሪቱ ረክሳለች፤ እኔም ለሠራችው ስህተት ቅጣት አመጣባታለሁ፤ ምድሪቱም ነዋሪዎቿን ትተፋቸዋለች። |
እናንተ ግን ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ጠብቁ፤ ከእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች መካከል የትኛውንም ማድረግ የለባችሁም፤ የአገራችሁ ሰውም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው እንዲህ ማድረግ የለበትም። |
ምክንያቱም ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ላይ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ፈጽመዋል፤ በዚህም የተነሳ አሁን ምድሪቱ ረክሳለች። |
እናንተ ግን ምድሪቱን ስለማታረክሷት ከእናንተ በፊት የነበሩትን ብሔራት እንደተፋቻቸው እናንተን አትተፋችሁም። |
ማንኛውም ሰው ከእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች መካከል የትኛውንም ቢፈጽም ይህን የፈጸመው ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ። |
ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች ይከተሏቸው ከነበሩት አስጸያፊ ልማዶች በመራቅ ለእኔ የገባችሁትን ግዴታ ፈጽሙ፤ አለዚያ በእነሱ ምክንያት ራሳችሁን ታረክሳላችሁ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ልታውጇቸው የሚገቡት በየወቅቱ የሚከበሩ የይሖዋ በዓላት ቅዱስ ጉባኤዎች ናቸው። በየወቅቱ የሚከበሩት የእኔ በዓላት የሚከተሉት ናቸው፦ |
“‘ለስድስት ቀን ሥራ መሥራት ይቻላል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይኸውም ቅዱስ ጉባኤ ነው። ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። በምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ይህ የይሖዋ ሰንበት ነው። |
“‘በተወሰነላቸው ጊዜ ላይ ልታውጇቸው የሚገቡት በየወቅቱ የሚከበሩ የይሖዋ በዓላት ማለትም ቅዱስ ጉባኤዎች የሚከተሉት ናቸው፦ |
በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ ለይሖዋ ፋሲካ ይከበራል። |
“‘በዚህ ወር 15ኛ ቀን ላይ የቂጣ በዓል ለይሖዋ ይከበራል። ለሰባት ቀንም ቂጣ መብላት ይኖርባችኋል። |
በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። |
ሆኖም ለሰባት ቀን ያህል ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ታቀርባላችሁ። በሰባተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም።’” |
በመቀጠልም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ የምድሪቱን አዝመራ በምታጭዱበት ጊዜ ከአዝመራችሁ መጀመሪያ የደረሰውን እህል ነዶ ለካህኑ ማምጣት አለባችሁ። |
እሱም ተቀባይነት እንድታገኙ ነዶውን በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዝውዘው። ካህኑ በሰንበት ማግስት ነዶውን ወዲያና ወዲህ ሊወዘውዘው ይገባል። |
ነዶው ወዲያና ወዲህ እንዲወዘወዝ በምታደርጉበት ቀን አንድ ዓመት ገደማ የሆነው እንከን የሌለበት ጠቦት ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ማቅረብ አለባችሁ። |
ከዚህም ጋር ሁለት አሥረኛ ኢፍ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። በተጨማሪም አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ ከዚያ ጋር የመጠጥ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። |
የአምላካችሁን መባ እስከምታቀርቡበት እስከዚህ ቀን ድረስ ምንም ዓይነት ዳቦም ሆነ ቆሎ ወይም እሸት መብላት የለባችሁም። በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላቂ ደንብ ነው። |
“‘ከሰንበት ማግስት ይኸውም ለሚወዘወዝ መባ የሚሆነውን ነዶ ካመጣችሁበት ቀን ጀምሮ ሰባት ሰንበቶችን ቁጠሩ። እነሱም ሙሉ ሳምንታት መሆን አለባቸው። |
እስከ ሰባተኛው ሰንበት ማግስት ድረስ 50 ቀን ቁጠሩ፤ ከዚያም ለይሖዋ አዲስ የእህል መባ አቅርቡ። |
ከምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁለት ቂጣዎችን ለሚወዘወዝ መባ ማምጣት ይኖርባችኋል። እነሱም ከሁለት አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄት የተዘጋጁ መሆን አለባቸው። ለይሖዋ የሚቀርቡ መጀመሪያ የደረሱ ፍሬዎች እንደመሆናቸው መጠን እርሾ ገብቶባቸው መጋገር ይኖርባቸዋል። |
ከቂጣዎቹም ጋር እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸውና እንከን የሌለባቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች አቅርቡ። እነዚህም ከእህል መባቸውና ከመጠጥ መባዎቻቸው ጋር ለይሖዋ የሚቃጠል መባ ማለትም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ሆነው ይቀርባሉ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.