text stringlengths 4 267 |
|---|
እንግዲህ ልጆቻችሁ በምድረ በዳ ለ40 ዓመት እረኞች ይሆናሉ፤ እነሱም የእናንተ የመጨረሻው ሬሳ በምድረ በዳ እስኪወድቅ ድረስ እናንተ ለፈጸማችሁት ታማኝነት የጎደለው ድርጊት መልስ ይሰጣሉ። |
እኔን መቃወም ምን ማለት እንደሆነ እንድታውቁ ምድሪቱን በሰለላችሁባቸው 40 ቀናት ልክ ይኸውም አንዱ ቀን እንደ አንድ ዓመት ተቆጥሮ፣ ለሠራችኋቸው ስህተቶች ለ40 ዓመት መልስ ትሰጣላችሁ። |
“‘“እኔ ይሖዋ ተናግሬአለሁ። በእኔ ላይ ተባብሮ በተነሳው በዚህ ክፉ ማኅበረሰብ ላይ በእርግጥ ይህን አደርጋለሁ፦ መጨረሻቸው በዚህ ምድረ በዳ ይሆናል፤ እዚሁም ይሞታሉ። |
ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸውና ስለ ምድሪቱ መጥፎ ወሬ ይዘው በመምጣት መላው ማኅበረሰብ በእሱ ላይ እንዲያጉረመርም ያደረጉት ሰዎች |
አዎ፣ ስለ ምድሪቱ መጥፎ ወሬ ይዘው የመጡት ሰዎች በይሖዋ ፊት ተቀስፈው ይሞታሉ። |
ምድሪቱን ለመሰለል ከሄዱት ሰዎች መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የየፎኒ ልጅ ካሌብ ግን በሕይወት ይኖራሉ።”’” |
ሙሴም ለእስራኤላውያን በሙሉ ይህን ሲነግራቸው ሕዝቡ እጅግ አዘነ። |
ከዚያም በጠዋት ወደ ተራራው አናት ለመውጣት ተነሱ፤ እነሱም “ኃጢአት ስለሠራን ይሖዋ ወደተናገረለት ቦታ ለመውጣት ይኸው ዝግጁ ነን” አሉ። |
ሙሴ ግን እንዲህ አለ፦ “የይሖዋን ትእዛዝ የምትጥሱት ለምንድን ነው? ይህ አይሳካላችሁም። |
ይሖዋ ከእናንተ ጋር ስላልሆነ አትውጡ፤ በጠላቶቻችሁ ድል ትመታላችሁ። |
ምክንያቱም አማሌቃውያንና ከነአናውያን በዚያ ይገጥሟችኋል፤ እናንተም በሰይፍ ትወድቃላችሁ። ምክንያቱም ይሖዋን ከመከተል ዞር ስላላችሁ ይሖዋ ከእናንተ ጋር አይሆንም።” |
እነሱ ግን በትዕቢት ወደ ተራራው አናት ወጡ፤ ሆኖም የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦትና ሙሴ ከሰፈሩ መካከል ንቅንቅ አላሉም። |
ከዚያም በዚያ ተራራ የሚኖሩት አማሌቃውያንና ከነአናውያን ወርደው መቷቸው፤ እስከ ሆርማም ድረስ በታተኗቸው። |
በመቀጠልም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን እዘዛቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ምግቤን ይኸውም መባዬን ለእኔ ማቅረባችሁን እንዳትዘነጉ። ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሰጡ በእሳት የሚቀርቡት መባዎቼ በተወሰነላቸው ጊዜ መቅረብ አለባቸው።’ |
“እንዲህም በላቸው፦ ‘ለይሖዋ የምታቀርቡት በእሳት የሚቃጠል መባ ይህ ነው፦ በየቀኑ፣ አንድ ዓመት የሆናቸው እንከን የሌለባቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ዘወትር አቅርቡ። |
አንደኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ጠዋት ላይ፣ ሌላኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ አቅርቡ፤ |
ከእነዚህም ጋር ተጨቅጭቆ በተጠለለ አንድ አራተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። |
ይህም በሲና ተራራ ላይ በወጣው ደንብ መሠረት ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው ዘወትር የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው፤ |
ከዚህም ጋር የመጠጥ መባውን ይኸውም ለእያንዳንዱ ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አራተኛ ሂን አቅርቡ። የሚያሰክረውን መጠጥ ለይሖዋ እንደሚቀርብ የመጠጥ መባ አድርጋችሁ በቅዱሱ ስፍራ አፍሱት። |
ሌላኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ አቅርቡት። ከእሱም ጋር ማለዳ ላይ የሚቀርበውን ዓይነት የእህል መባና ከእሱ ጋር አብሮ የሚቀርበውን ዓይነት የመጠጥ መባ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። |
“‘ይሁንና በሰንበት ቀን፣ አንድ ዓመት የሆናቸውን እንከን የሌለባቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች እንዲሁም በዘይት የተለወሰ ሁለት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ከመጠጥ መባው ጋር ታቀርባላችሁ። |
ይህ ዘወትር ከሚቀርበው የሚቃጠል መባና ከመጠጥ መባው ጋር በየሰንበቱ የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ነው። |
“‘በየወሩም መባቻ ላይ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው እንከን የሌለባቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ |
ለእያንዳንዱ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ |
ለእያንዳንዱም ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። |
በተጨማሪም ከእነዚህ ጋር ለአንድ ወይፈን ግማሽ ሂን፣ ለአውራው በግ አንድ ሦስተኛ ሂን እንዲሁም ለአንድ ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ የመጠጥ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። ይህም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚቀርብ ወርሃዊ የሚቃጠል መባ ነው። |
እንዲሁም ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ ሆኖ ለይሖዋ መቅረብ አለበት። |
“‘በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ14ኛው ቀን የይሖዋ ፋሲካ ይከበራል። |
በዚሁ ወር በ15ኛው ቀን በዓል ይሆናል። ለሰባት ቀን ቂጣ ይበላል። |
በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። |
ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። እንከን የሌለባቸውን እንስሳት ማቅረብ አለባችሁ። |
ከእነዚህም ጋር ለአንድ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። |
ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ ታቀርባላችሁ፤ |
እንዲሁም ለእናንተ ማስተሰረያ እንዲሆን አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። |
ለዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሆን ጠዋት ላይ ከሚቀርበው የሚቃጠል መባ በተጨማሪ እነዚህን ታቀርባላችሁ። |
እነዚህንም በተመሳሳይ መንገድ በየቀኑ ለሰባት ቀን እንደ ምግብ፣ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዳለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። ይህም ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና ከመጠጥ መባው ጋር ይቅረብ። |
በሰባተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። |
“‘መጀመሪያ የሚደርሰው ፍሬ በሚሰበሰብበት ቀን ለይሖዋ አዲስ የእህል መባ ስታቀርቡ በሳምንታት በዓላችሁ ላይ ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። |
ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ |
ከእነዚህም ጋር ለእያንዳንዱ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ |
እንዲሁም ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ |
በተጨማሪም ለእናንተ ማስተሰረያ እንዲሆን አንድ የፍየል ጠቦት ታቀርባላችሁ። |
ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና ከእህል መባው በተጨማሪ እነዚህን ታቀርባላችሁ። እንስሳቱም እንከን የሌለባቸው መሆን አለባቸው፤ ከመጠጥ መባቸውም ጋር መቅረብ ይኖርባቸዋል። |
እስራኤላውያንም ከዚያ ተነስተው በመጓዝ ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ በሚገኘው በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ሰፈሩ። |
የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤላውያን በአሞራውያን ላይ ያደረጉትን ሁሉ አየ፤ |
ሞዓብም ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ በጣም ፈራ፤ በእርግጥም ሞዓብ በእስራኤላውያን ምክንያት በፍርሃት ታውኮ ነበር። |
ስለዚህ ሞዓብ የምድያምን ሽማግሌዎች “በሬ በሜዳ ላይ ያለን ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ ይህም ጉባኤ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ ያጠፋል” አላቸው። በዚያን ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበር። |
እሱም የቢዖርን ልጅ በለዓምን እንዲጠሩት መልእክተኞችን ላከ፤ በለዓም የሚኖረው በትውልድ አገሩ ባለው ወንዝ ዳር በምትገኘው በጰቶር ነበር። እንዲህም ብለው እንዲነግሩት ላካቸው፦ “ከግብፅ ወጥቶ የመጣ አንድ ሕዝብ አለ። ይኸው የምድሪቱን ገጽ ሸፍኗል፤ ደግሞም መጥቶ አፍንጫዬ ሥር ሰፍሯል። |
እነሱ ከእኔ ይልቅ ኃያላን ስለሆኑ እባክህ መጥተህ ይህን ሕዝብ እርገምልኝ። ምናልባትም ድል አድርጌ ከምድሪቱ ላባርራቸው እችላለሁ፤ ምክንያቱም አንተ የባረክኸው ሁሉ የተባረከ፣ የረገምከውም ሁሉ የተረገመ እንደሚሆን በሚገባ አውቃለሁ።” |
በመሆኑም የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎች ለሟርት የሚከፈለውን ዋጋ ይዘው ወደ በለዓም ሄዱ፤ የባላቅንም መልእክት ነገሩት። |
እሱም “እንግዲህ እዚህ እደሩና ይሖዋ የሚለኝን ማንኛውንም ነገር መልሼ እነግራችኋለሁ” አላቸው። ስለዚህም የሞዓብ መኳንንት በለዓም ዘንድ አደሩ። |
ከዚያም አምላክ ወደ በለዓም መጥቶ “ከአንተ ጋር ያሉት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?” አለው። |
በለዓምም እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለው፦ “የሞዓብ ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ የሚል መልእክት ልኮብኛል፦ |
‘ከግብፅ ወጥቶ የመጣው ሕዝብ የምድሪቱን ገጽ ሸፍኗል። ስለዚህ መጥተህ እነሱን እርገምልኝ። ምናልባትም ድል አድርጌ ከምድሪቱ ላባርራቸው እችላለሁ።’” |
ሆኖም አምላክ በለዓምን “ከእነሱ ጋር እንዳትሄድ። ሕዝቡ የተባረከ ስለሆነ እንዳትረግመው” አለው። |
በለዓም በጠዋት ተነስቶ የባላቅን መኳንንት “ይሖዋ ከእናንተ ጋር እንዳልሄድ ስለከለከለኝ ወደ አገራችሁ ሂዱ” አላቸው። |
በመሆኑም የሞዓብ መኳንንት ተነስተው ወደ ባላቅ ተመለሱ፤ እንዲህም አሉት፦ “በለዓም ከእኛ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ አልሆነም።” |
ሆኖም ባላቅ ከበፊቶቹ ይልቅ ቁጥራቸው የበዛና ይበልጥ የተከበሩ ሌሎች መኳንንት እንደገና ላከ። |
እነሱም ወደ በለዓም መጥተው እንዲህ አሉት፦ “የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ ይላል፦ ‘እባክህ ወደ እኔ ከመምጣት ምንም ነገር እንዲያግድህ አትፍቀድ። |
እኔም ከፍ ያለ ክብር አጎናጽፍሃለሁ፤ የምትለኝንም ሁሉ አደርጋለሁ። ስለሆነም እባክህ መጥተህ ይህን ሕዝብ እርገምልኝ።’” |
ሆኖም በለዓም ለባላቅ አገልጋዮች እንዲህ የሚል መልስ ሰጣቸው፦ “ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላውን የገዛ ቤቱን ቢሰጠኝ እንኳ ከአምላኬ ከይሖዋ ትእዛዝ ወጥቼ ትንሽም ሆነ ትልቅ ምንም ነገር ማድረግ አልችልም። |
ሆኖም እባካችሁ፣ ይሖዋ ሌላ የሚለኝ ነገር ካለ እንዳውቅ ዛሬም እዚህ እደሩ።” |
ከዚያም አምላክ በሌሊት ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፦ “እነዚህ ሰዎች የመጡት አንተን ለመጥራት ከሆነ አብረሃቸው ሂድ። ይሁንና የምትናገረው እኔ የምልህን ብቻ ነው።” |
ስለዚህ በለዓም በጠዋት ተነስቶ አህያውን ከጫነ በኋላ ከሞዓብ መኳንንት ጋር ሄደ። |
ይሁን እንጂ በለዓም ጉዞ በመጀመሩ የአምላክ ቁጣ ነደደ፤ የይሖዋም መልአክ በለዓምን ሊቃወመው መንገዱ ላይ ቆመ። በዚህ ጊዜ በለዓም በአህያው ላይ ተቀምጦ እየተጓዘ ነበር፤ ሁለት አገልጋዮቹም አብረውት ነበሩ። |
አህያዋም የይሖዋ መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ መንገዱ ላይ መቆሙን ስታይ ከመንገዱ ወጥታ ወደ እርሻ ለመግባት ሞከረች። ሆኖም በለዓም አህያዋን ወደ መንገዱ ለመመለስ ይደበድባት ጀመር። |
ከዚያም የይሖዋ መልአክ በዚህም በዚያም በኩል በግንብ በታጠሩ ሁለት የወይን እርሻዎች መካከል በሚገኝ ጠባብ መንገድ ላይ ቆመ። |
አህያዋም የይሖዋን መልአክ ስታይ ግንቡን መታከክ ጀመረች፤ የበለዓምንም እግር ከግንቡ ጋር አጣበቀችው፤ በለዓምም እንደገና ይደበድባት ጀመር። |
የይሖዋም መልአክ እንደገና አልፎ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ መፈናፈን በማያስችል ጠባብ ቦታ ላይ ቆመ። |
አህያዋም የይሖዋን መልአክ ስታይ በለዓም ላይዋ ላይ እንዳለ ተኛች፤ በዚህ ጊዜ በለዓም እጅግ ተቆጣ፤ አህያዋንም በዱላው ይቀጠቅጣት ጀመር። |
በመጨረሻም ይሖዋ አህያዋ እንድትናገር አደረገ፤ እሷም በለዓምን “ሦስት ጊዜ እንዲህ የመታኸኝ ምን አድርጌህ ነው?” አለችው። |
በለዓምም አህያዋን “ስለተጫወትሽብኝ ነዋ! በእጄ ሰይፍ ይዤ ቢሆንማ ኖሮ እገድልሽ ነበር!” አላት። |
ከዚያም አህያዋ በለዓምን “እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወትህ ሙሉ የተቀመጥክብኝ አህያህ አይደለሁም? ከዚህ በፊት እንዲህ አድርጌህ አውቃለሁ?” አለችው። እሱም “በጭራሽ!” አላት። |
ከዚያም ይሖዋ የበለዓምን ዓይኖች ገለጠ፤ እሱም የይሖዋ መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ መንገዱ ላይ ቆሞ አየ። ወዲያውኑም በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደ። |
ከዚያም የይሖዋ መልአክ እንዲህ አለው፦ “አህያህን ሦስት ጊዜ እንዲህ አድርገህ የመታሃት ለምንድን ነው? መንገድህ ከፈቃዴ ጋር ስለሚቃረን እኔ ራሴ ከጉዞህ ልገታህ መጥቻለሁ። |
አህያዋ አይታኝ ሦስቱንም ጊዜ ከፊቴ ዞር ለማለት ሞከረች። እሷ ከፊቴ ዞር ባትልማ ኖሮ ምን ይከሰት እንደነበር አስብ! ይሄን ጊዜ አንተን ገድዬህ አህያዋን በሕይወት በተውኳት ነበር።” |
በዚህ ጊዜ በለዓም የይሖዋን መልአክ እንዲህ አለው፦ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ ምክንያቱም አንተ እኔን ለማግኘት መንገድ ላይ እንደቆምክ አላወቅኩም ነበር። አሁንም ቢሆን መሄዴ ጥሩ መስሎ ካልታየህ እመለሳለሁ።” |
ሆኖም የይሖዋ መልአክ በለዓምን “ከሰዎቹ ጋር መሄዱን እንኳ ሂድ፤ የምትናገረው ግን እኔ የምልህን ብቻ ነው” አለው። በመሆኑም በለዓም ከባላቅ መኳንንት ጋር ጉዞውን ቀጠለ። |
ባላቅ የበለዓምን መምጣት ሲሰማ በክልሉ ወሰን ላይ በሚገኘው በአርኖን ዳርቻ ባለው በሞዓብ ከተማ ሊቀበለው ወዲያውኑ ወጣ። |
ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “እንድትመጣ ልኬብህ አልነበረም? ታዲያ ወደ እኔ ያልመጣኸው ለምንድን ነው? ለመሆኑ እኔ አንተን ታላቅ ክብር ማጎናጸፍ የሚያቅተኝ ይመስልሃል?” |
በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “ይኸው አሁን ወደ አንተ መጥቻለሁ። ይሁንና ያሻኝን መናገር የምችል ይመስልሃል? እኔ መናገር የምችለው አምላክ በአፌ ላይ የሚያደርገውን ቃል ብቻ ነው።” |
በመሆኑም በለዓም ከባላቅ ጋር ሄደ፤ ወደ ቂርያትሁጾትም መጡ። |
ባላቅም ከብቶችንና በጎችን ሠዋ፤ የተወሰነውንም ለበለዓምና ከእሱ ጋር ለነበሩት መኳንንት ላከ። |
ጠዋት ላይም ባላቅ በለዓምን ይዞት ወደ ባሞትበዓል ወጣ፤ እዚያ ሆኖ ሕዝቡን ሁሉ ማየት ይችል ነበር። |
በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እንድትኖሩባት ወደምሰጣችሁ ምድር በምትገቡበትና |
ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠል መባም ሆነ ለየት ያለ ስእለት ለመሳል የሚቀርብ መሥዋዕት ወይም የፈቃደኝነት መባ አሊያም በየወቅቱ በምታከብሯቸው በዓላት ላይ የሚቀርብ መባ፣ ከከብታችሁ ወይም ከመንጋችሁ በመውሰድ ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ በምታቀርቡበት ጊዜ |
መባውን የሚያቀርበው ሰው በአንድ አራተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄትም የእህል መባ አድርጎ ለይሖዋ ማቅረብ ይኖርበታል። |
እንዲሁም ከሚቃጠለው መባ ወይም ከተባዕት የበግ ጠቦት መሥዋዕቱ ጋር አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ የመጠጥ መባ አድርገህ ማቅረብ አለብህ። |
ወይም ከአውራ በግ ጋር በአንድ ሦስተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ ሁለት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርገህ አቅርብ። |
እንዲሁም አንድ ሦስተኛ ሂን የወይን ጠጅ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው የመጠጥ መባ አድርገህ ማቅረብ አለብህ። |
“‘ሆኖም ከመንጋው መካከል አንድ ወይፈን የሚቃጠል መባ ወይም ለየት ያለ ስእለት ለመሳል የሚቀርብ መሥዋዕት አሊያም የኅብረት መሥዋዕት አድርገህ ለይሖዋ የምታቀርብ ከሆነ |
ከወይፈኑ ጋር በግማሽ ሂን ዘይት የተለወሰ ሦስት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርገህ ማቅረብ ይኖርብሃል። |
እንዲሁም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው የመጠጥ መባ እንዲሆን ግማሽ ሂን የወይን ጠጅ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርገህ ማቅረብ አለብህ። |
ለእያንዳንዱ በሬ ወይም ለእያንዳንዱ አውራ በግ ወይም ለእያንዳንዱ ተባዕት የበግ ጠቦት ወይም ለእያንዳንዱ ፍየል እንዲሁ መደረግ አለበት። |
የምታቀርቡት ብዛቱ ምንም ያህል ይሁን ምን ለእያንዳንዱ እንደየብዛቱ እንዲህ ማድረግ ይኖርባችኋል። |
የአገሩ ተወላጅ የሆነ እያንዳንዱ እስራኤላዊ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቃጠል መባ የሚያቀርበው በዚህ መንገድ ነው። |
“‘ከእናንተ ጋር እየኖረ ያለ ወይም ለብዙ ትውልድ በመካከላችሁ ሲኖር የነበረ የባዕድ አገር ሰው ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቃጠል መባ ቢያቀርብ ልክ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ። |
የጉባኤው ክፍል የሆናችሁት እናንተም ሆናችሁ አብሯችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው አንድ ዓይነት ደንብ ይኖራችኋል። ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘላቂ ደንብ ይሆናል። የባዕድ አገሩ ሰው በይሖዋ ፊት ልክ እንደ እናንተ ይታያል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.