text stringlengths 4 267 |
|---|
የሜራሪ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ሆነው በመገናኛ ድንኳኑ የሚያገለግሉት በዚህ መሠረት ነው።” |
ከዚያም ሙሴ፣ አሮንና የማኅበረሰቡ አለቆች የቀአታውያንን ወንዶች ልጆች በየቤተሰቦቻቸውና በየአባቶቻቸው ቤት መዘገቡ፤ |
በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉትን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑትን ሁሉ መዘገቡ። |
በየቤተሰባቸው የተመዘገቡትም በአጠቃላይ 2,750 ነበሩ። |
ከቀአታውያን ቤተሰቦች መካከል የተመዘገቡትና በመገናኛ ድንኳኑ የሚያገለግሉት በአጠቃላይ እነዚህ ነበሩ። ሙሴና አሮንም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት መዘገቧቸው። |
የጌድሶን ወንዶች ልጆችም በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት ተመዘገቡ፤ |
በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉት ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑት ሁሉ ተመዘገቡ። |
በየቤተሰቦቻቸውና በየአባቶቻቸው ቤት የተመዘገቡት በአጠቃላይ 2,630 ነበሩ። |
በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግሉ የተመዘገቡት የጌድሶን ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች በአጠቃላይ እነዚህ ነበሩ። ሙሴና አሮንም ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት መዘገቧቸው። |
የሜራሪ ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት ተመዘገቡ፤ |
በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉት ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑት ሁሉ ተመዘገቡ። |
ከእነሱ መካከል በየቤተሰባቸው የተመዘገቡት በአጠቃላይ 3,200 ነበሩ። |
ሙሴና አሮን ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት የመዘገቧቸው የሜራሪ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ። |
ሙሴ፣ አሮንና የእስራኤል አለቆች እነዚህን ሌዋውያን ሁሉ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች መዘገቧቸው፤ |
እነሱም ከ30 እስከ 50 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ሁሉም ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ እንዲያገለግሉና ሸክም እንዲሸከሙ ተመድበው ነበር። |
የተመዘገቡትም በአጠቃላይ 8,580 ነበሩ። |
እነሱም ይሖዋ በሙሴ በኩል ባስተላለፈው ትእዛዝ መሠረት ተመዝግበው ነበር፤ የተመዘገቡትም እያንዳንዳቸው በሚያከናውኑት አገልግሎትና በሚሸከሙት ሸክም መሠረት ነበር፤ እነሱም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተመዘገቡ። |
በመጀመሪያው ወር መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ወደ ጺን ምድረ በዳ መጣ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጠ። ሚርያም የሞተችውም ሆነ የተቀበረችው በዚያ ነበር። |
በዚያ ለማኅበረሰቡ የሚሆን ውኃ አልነበረም፤ ሕዝቡም ሙሴንና አሮንን በመቃወም በእነሱ ላይ ተሰበሰበ። |
ሕዝቡም እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣላ፦ “ምነው ወንድሞቻችን በይሖዋ ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ሞተን ባረፍነው ኖሮ! |
እኛም ሆንን ከብቶቻችን እዚህ እንድናልቅ የይሖዋን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት ለምንድን ነው? |
ከግብፅ አውጥታችሁ ወደዚህ መጥፎ ቦታ እየመራችሁ ያመጣችሁን ለምንድን ነው? ይህ ቦታ እህልም ሆነ በለስ፣ የወይን ፍሬም ሆነ ሮማን የሌለበት ነው፤ የሚጠጣ ውኃም የለም።” |
ከዚያም ሙሴና አሮን ከጉባኤው ፊት ተነስተው ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በመሄድ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ፤ የይሖዋም ክብር ተገለጠላቸው። |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮንም ማኅበረሰቡን ሰብስቡ፤ ዓለቱም ውኃውን እንዲሰጥ በእነሱ ፊት ተናገሩት፤ አንተም ከዓለቱ ውኃ ታፈልቅላቸዋለህ፤ ማኅበረሰቡም ሆነ ከብቶቻቸው እንዲጠጡም ትሰጣቸዋለህ።” |
ሙሴም ልክ እንደታዘዘው በትሩን ከይሖዋ ፊት ወሰደ። |
ከዚያም ሙሴና አሮን ጉባኤውን በዓለቱ ፊት ሰበሰቡ፤ እሱም “እናንተ ዓመፀኞች ስሙ! ከዚህ ዓለት ለእናንተ ውኃ ማፍለቅ አለብን?” አላቸው። |
ሙሴም ይህን ካለ በኋላ እጁን አንስቶ ዓለቱን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ውኃውም ይንዶለዶል ጀመር፤ ማኅበረሰቡና ከብቶቻቸውም ጠጡ። |
በኋላም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “በእስራኤል ሕዝብ ፊት በእኔ ስላልታመናችሁና እኔን ስላልቀደሳችሁ ይህን ጉባኤ እኔ ወደምሰጠው ምድር ይዛችሁ አትገቡም።” |
ይሖዋ በመካከላቸው ይቀደስ ዘንድ እስራኤላውያን ከእሱ ጋር የተጣሉባቸው የመሪባ ውኃዎች እነዚህ ናቸው። |
ከዚያም ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት ከቃዴስ መልእክተኞችን ላከ፦ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ‘መቼም የደረሰብንን መከራ ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ። |
አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወርደው ነበር፤ እኛም በግብፅ ለብዙ ዓመታት ኖርን፤ ግብፃውያኑም በእኛም ሆነ በአባቶቻችን ላይ በደል ይፈጽሙብን ነበር። |
በመጨረሻም ወደ ይሖዋ ጮኽን፤ እሱም ጩኸታችንን ሰምቶ መልአክ በመላክ ከግብፅ አወጣን፤ ይኸው አሁን ድንበርህ ላይ ባለችው በቃዴስ ከተማ እንገኛለን። |
እናም አሁን እባክህ በምድርህ እንለፍ። በየትኛውም እርሻ ወይም በየትኛውም የወይን ቦታ አቋርጠን አንሄድም፤ ከየትኛውም ጉድጓድ ውኃ አንጠጣም። ክልልህን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር ሳንል በንጉሡ መንገድ እንሄዳለን።’” |
ኤዶም ግን “ክልላችንን አቋርጠህ ማለፍ አትችልም። እንዲህ ካደረግክ ወጥቼ በሰይፍ እገጥምሃለሁ” አለው። |
እስራኤላውያንም መልሰው እንዲህ አሉት፦ “አውራ ጎዳናውን ይዘን እናቀናለን፤ እኛም ሆን ከብቶቻችን ከውኃህ ከጠጣን ዋጋውን እንከፍልሃለን። በእግራችን አልፈን ከመሄድ በስተቀር ሌላ ምንም ነገር አንፈልግም።” |
እሱ ግን አሁንም “በዚህ ማለፍ አትችልም” ሲል መልስ ሰጠ። ከዚያም ኤዶም ብዙ ሕዝብና ኃያል ሠራዊት ይዞ ሊገጥመው ወጣ። |
በዚህ መንገድ ኤዶም እስራኤል በክልሉ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ስለዚህ እስራኤል ከእሱ ተመለሰ። |
የእስራኤል ሕዝብ ይኸውም መላው ማኅበረሰብ ከቃዴስ ተነስቶ ወደ ሆር ተራራ መጣ። |
ከዚያም ይሖዋ በኤዶም ምድር ወሰን ላይ ባለው በሆር ተራራ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ |
“አሮን ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል። ሁለታችሁም ከመሪባ ውኃ ጋር በተያያዘ በሰጠሁት ትእዛዝ ላይ ስላመፃችሁ ለእስራኤላውያን ወደምሰጣት ምድር አይገባም። |
አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሆር ተራራ ውጣ። |
የአሮንን ልብስ አውልቀህ ልጁን አልዓዛርን አልብሰው፤ አሮንም በዚያ ይሞታል።” |
በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ እነሱም መላው ማኅበረሰብ እያየ ወደ ሆር ተራራ ወጡ። |
ሙሴም የአሮንን ልብስ አውልቆ ልጁን አልዓዛርን አለበሰው። ከዚያም አሮን እዚያው ተራራው አናት ላይ ሞተ። ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ወረዱ። |
መላው ማኅበረሰብም አሮን መሞቱን አየ፤ በዚህ ጊዜ የእስራኤል ቤት በሙሉ ለአሮን 30 ቀን አለቀሰለት። |
ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት አግብቶ ስለነበር ባገባት ኢትዮጵያዊት ሴት የተነሳ ሚርያምና አሮን ይነቅፉት ጀመር። |
እነሱም “ለመሆኑ ይሖዋ የሚናገረው በሙሴ አማካኝነት ብቻ ነው? በእኛስ በኩል አልተናገረም?” ይሉ ነበር። ይሖዋም ይህን ይሰማ ነበር። |
ሙሴ በምድር ላይ ከነበሩ ሰዎች ሁሉ ይልቅ በጣም የዋህ ነበር። |
ይሖዋም ድንገት ሙሴን፣ አሮንንና ሚርያምን “ሦስታችሁም ወደ መገናኛ ድንኳኑ ውጡ” አላቸው። በመሆኑም ሦስቱም ወጡ። |
ይሖዋም በደመና ዓምድ ወርዶ በድንኳኑ መግቢያ ላይ በመቆም አሮንንና ሚርያምን ጠራቸው። በዚህ ጊዜ ሁለቱም ወደ ፊት ቀረቡ። |
እሱም እንዲህ አለ፦ “እባካችሁ ቃሌን ስሙ። አንድ የይሖዋ ነቢይ በመካከላችሁ ቢኖር በራእይ አማካኝነት ራሴን አሳውቀው በሕልምም አነጋግረው ነበር። |
አገልጋዬን ሙሴን በተመለከተ ግን እንዲህ አይደለም! እሱ በቤቴ ሁሉ ላይ አደራ የተጣለበት ሰው ነው። |
እኔ እሱን የማነጋግረው ፊት ለፊት በግልጽ እንጂ በእንቆቅልሽ አይደለም፤ እሱም የይሖዋን አምሳል ያያል። ታዲያ አገልጋዬን ሙሴን ስትነቅፉት ምነው አልፈራችሁም?” |
በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ በእነሱ ላይ ነደደ፤ ትቷቸውም ሄደ። |
ከዚያም ደመናው ከድንኳኑ ላይ ተነሳ፤ በዚህ ጊዜ ሚርያም በሥጋ ደዌ ተመታ እንደ በረዶ ነጭ ሆና ነበር። አሮንም ወደ ሚርያም ዞር ሲል በሥጋ ደዌ ተመታ አየ። |
አሮንም ወዲያውኑ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይቅርታ አድርግልኝ ጌታዬ! እባክህ ይህን ኃጢአት አትቁጠርብን! የፈጸምነው የሞኝነት ድርጊት ነው። |
እባክህ፣ ግማሽ አካሉ ተበልቶ የተወለደ ጭንጋፍ መስላ እንድትቀር አታድርግ!” |
ሙሴም “አምላክ ሆይ፣ እባክህ ፈውሳት! እባክህ!” በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ። |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባቷ ፊቷ ላይ ቢተፋባት ለሰባት ቀን ተዋርዳ ትቆይ አልነበረም? አሁንም ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀን ተገልላ እንድትቆይ ይደረግ፤ ከዚያ በኋላ እንድትመለስ ማድረግ ይቻላል።” |
ስለዚህ ሚርያም ለሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጭ ተገልላ እንድትቆይ ተደረገ፤ ሕዝቡም ሚርያም ተመልሳ እንድትቀላቀል እስኪደረግ ድረስ ጉዞውን አልቀጠለም። |
ከዚያም ሕዝቡ ከሃጼሮት ተነስቶ በፋራን ምድረ በዳ ሰፈረ። |
ከዚያም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ከመቅደሱ ጋር በተያያዘ ለሚፈጸመው ማንኛውም በደል አንተ፣ ከአንተም ጋር ወንዶች ልጆችህና የአባትህ ቤት ተጠያቂ ትሆናላችሁ፤ ከክህነታችሁ ጋር በተያያዘ ለሚፈጸመው ማንኛውም በደል አንተ፣ ከአንተም ጋር ወንዶች ልጆችህ ተጠያቂ ትሆናላችሁ። |
በተጨማሪም በምሥክሩ ድንኳን ፊት ከአንተ ጋር አብረው እንዲሆኑ እንዲሁም አንተንና ወንዶች ልጆችህን እንዲያገለግሉ ከአባትህ ነገድ ይኸውም ከሌዊ ነገድ የሆኑትን ወንድሞችህን አቅርባቸው። |
ከአንተም ሆነ በአጠቃላይ ከድንኳኑ ጋር በተያያዘ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ይወጡ። ይሁንና አንተም ሆንክ እነሱ እንዳትሞቱ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ዕቃዎችና ወደ መሠዊያው አይቅረቡ። |
እነሱም ከእናንተ ጋር በመሆን ከመገናኛ ድንኳኑና በድንኳኑ ከሚከናወነው አገልግሎት ሁሉ ጋር በተያያዘ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ይወጣሉ፤ ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው ወደ እናንተ መቅረብ የለበትም። |
እናንተም በእስራኤል ሕዝብ ላይ ዳግም ቁጣ እንዳይመጣ ከቅዱሱ ስፍራና ከመሠዊያው ጋር በተያያዘ የተጣለባችሁን ኃላፊነት ተወጡ። |
እኔ ራሴ ወንድሞቻችሁ የሆኑትን ሌዋውያን ከእስራኤላውያን መካከል ወስጄ ለእናንተ ስጦታ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ። እነሱም በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ የሚከናወነውን አገልግሎት እንዲፈጽሙ ለይሖዋ የተሰጡ ናቸው። |
ከመሠዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ካለው ነገር ጋር የተያያዙትን የክህነት ሥራዎቻችሁን የማከናወኑ ኃላፊነት የተጣለው በአንተና በወንዶች ልጆችህ ላይ ነው፤ እናንተም ይህን አገልግሎት ታከናውናላችሁ። የክህነት አገልግሎቱን ለእናንተ ስጦታ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ወደዚያ የሚቀርብ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው ይገደል።” |
በተጨማሪም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለእኔ በሚቀርቡት መዋጮዎች ላይ እኔ ራሴ ኃላፊ አድርጌ ሾሜሃለሁ። እስራኤላውያን የሚያዋጧቸውን ቅዱስ ነገሮች ሁሉ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ቋሚ ድርሻችሁ ነው። |
በእሳት ከሚቀርቡት እጅግ ቅዱስ የሆኑ መባዎች ውስጥ የሚከተሉት የአንተ ይሆናሉ፦ ለእኔ የሚያመጡትን የእህል መባቸውን፣ የኃጢአት መባቸውንና የበደል መባቸውን ጨምሮ የሚያቀርቡት ማንኛውም መባ የአንተ ይሆናል። ይህ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ እጅግ የተቀደሰ ነገር ነው። |
እጅግ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ብላው። እያንዳንዱ ወንድ ይብላው። ይህ ለአንተ የተቀደሰ ነገር ነው። |
እስራኤላውያን ከሚወዘወዝ መባቸው ሁሉ ጋር መዋጮ አድርገው የሚያመጧቸው ስጦታዎች የአንተ ይሆናሉ። እነዚህን ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለወንዶች ልጆችህና ለሴቶች ልጆችህ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ። በቤትህ ያለ ማንኛውም ንጹሕ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል። |
“ለይሖዋ የሚሰጡትን ምርጥ የሆነውን ዘይት ሁሉ፣ ምርጥ የሆነውን አዲስ የወይን ጠጅና እህል ሁሉ ይኸውም የፍሬያቸውን በኩራት ለአንተ ሰጥቼሃለሁ። |
በምድራቸው ላይ መጀመሪያ የደረሰው ለይሖዋ የሚያመጡት ፍሬ ሁሉ የአንተ ይሆናል። በቤትህ ያለ ማንኛውም ንጹሕ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል። |
“በእስራኤል ውስጥ ቅዱስ ለሆነ ዓላማ የተለየ ማንኛውም ነገር የአንተ ይሆናል። |
“ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ለይሖዋ የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ ሕይወት ያለው ነገር በኩር ሁሉ የአንተ መሆን ይኖርበታል። ሆኖም ከሰው በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይኖርብሃል፤ እንዲሁም ርኩስ ከሆነ እንስሳ በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይገባሃል። |
አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሲሆነው እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት በተተመነለት ዋጋ ይኸውም በአምስት የብር ሰቅል ወጆ ልትዋጀው ይገባል። አንዱ ሰቅል 20 ጌራ ነው። |
በኩር የሆነውን በሬ፣ በኩር የሆነውን ተባዕት በግና በኩር የሆነውን ፍየል ግን መዋጀት የለብህም። እነዚህ የተቀደሱ ነገሮች ናቸው። ደማቸውን በመሠዊያው ላይ እርጨው፤ ስባቸውን ደግሞ ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ የሚሰጥ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርገህ አጭሰው። |
ሥጋቸው የአንተ ይሆናል። እንደሚወዘወዘው መባ ፍርምባና እንደ ቀኙ እግር ሁሉ ይህም የአንተ ይሆናል። |
እስራኤላውያን ለይሖዋ የሚያዋጧቸውን ቅዱስ መዋጮዎች በሙሉ ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለወንዶች ልጆችህና ለሴቶች ልጆችህ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ። ይህም በይሖዋ ፊት ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለዘሮችህ የተገባ ዘላቂ የጨው ቃል ኪዳን ነው።” |
ይሖዋም በመቀጠል አሮንን እንዲህ አለው፦ “አንተ በምድራቸው ውርሻ አይኖርህም፤ በመካከላቸውም ርስት አይኖርህም። በእስራኤላውያን መካከል የአንተ ድርሻም ሆነ ውርሻ እኔ ነኝ። |
“እንግዲህ የሌዊ ወንዶች ልጆች ለሚያከናውኑት አገልግሎት ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ለሚሰጡት አገልግሎት በእስራኤል ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር አንድ አሥረኛ ውርሻ አድርጌ እንደሰጠኋቸው ልብ በል። |
ከእንግዲህ እስራኤላውያን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መቅረብ አይችሉም፤ ከቀረቡ ግን ኃጢአት ሆኖባቸው ይሞታሉ። |
በመገናኛ ድንኳኑ የሚቀርበውን አገልግሎት ማከናወን ያለባቸው ሌዋውያኑ ራሳቸው ናቸው፤ ሕዝቡ ለሚፈጽመው ስህተት ተጠያቂ የሚሆኑት እነሱ ናቸው። በእስራኤላውያን መካከል በውርስ የሚያገኙት ርስት አይኖራቸውም፤ ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ የሚቀጥል ዘላቂ ደንብ ነው። |
ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ መዋጮ አድርጎ ለይሖዋ የሚያዋጣውን አንድ አሥረኛ ለሌዋውያኑ ውርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። እኔም ‘በእስራኤላውያን መካከል በውርስ የሚያገኙት ርስት አይኖራቸውም’ ያልኳቸው ለዚህ ነው።” |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“ሌዋውያኑን እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእስራኤላውያን ላይ ውርሻችሁ አድርጌ የሰጠኋችሁን አንድ አሥረኛ ከእነሱ እጅ ትቀበላላችሁ፤ እናንተ ደግሞ የአንድ አሥረኛውን አንድ አሥረኛ ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ። |
ይህ ለእናንተ እንደ መዋጮ ይኸውም ከአውድማ እንደገባ እህል ወይም ከወይን መጭመቂያ አሊያም ከዘይት መጭመቂያ እንደተገኘ የተትረፈረፈ ምርት ተደርጎ ይታሰብላችኋል። |
በዚህ መንገድ እናንተም ከእስራኤላውያን ከምትቀበሉት አንድ አሥረኛ ሁሉ ላይ ለይሖዋ መዋጮ ታዋጣላችሁ፤ ከእሱም ላይ የይሖዋን መዋጮ ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ። |
ከምትቀበሏቸው ስጦታዎች ሁሉ ላይ ምርጥ የሆነውን እንደ ቅዱስ ነገር አድርጋችሁ ለይሖዋ ሁሉንም ዓይነት መዋጮ ታዋጣላችሁ።’ |
“እንዲህም በላቸው፦ ‘ከስጦታዎቹ ላይ ምርጥ የሆነውን በምታዋጡበት ጊዜ ይህ ለእናንተ ለሌዋውያኑ ከአውድማ እንደገባ ምርት እንዲሁም ከወይን መጭመቂያ ወይም ከዘይት መጭመቂያ እንደተገኘ ምርት ተደርጎ ይታሰብላችኋል። |
ይህ በመገናኛ ድንኳኑ ለምታከናውኑት አገልግሎት የተሰጠ ደሞዛችሁ ስለሆነ እናንተም ሆናችሁ ቤተሰባችሁ በየትኛውም ቦታ ልትበሉት ትችላላችሁ። |
ከስጦታዎቹ ላይ ምርጥ የሆነውን መዋጮ እስካደረጋችሁ ድረስ ኃጢአት አይሆንባችሁም፤ የእስራኤላውያንን ቅዱስ ነገሮች ማርከስ የለባችሁም፤ እንዲህ ካደረጋችሁ ግን ትሞታላችሁ።’” |
ከዚያም በለዓም ባላቅን “እዚህ ቦታ ላይ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፤ እንዲሁም ሰባት በሬዎችና ሰባት አውራ በጎች አዘጋጅልኝ” አለው። |
ባላቅም ወዲያውኑ በለዓም እንዳለው አደረገ። ባላቅና በለዓም በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረቡ። |
ከዚያም በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “አንተ እዚህ የሚቃጠለው መባህ አጠገብ ቆይ፤ እኔ ግን ልሂድ። ምናልባት ይሖዋ ይገለጥልኝ ይሆናል። እሱ የሚገልጥልኝን ማንኛውንም ነገር እነግርሃለሁ።” በመሆኑም በለዓም ወደ አንድ ገላጣ ኮረብታ ሄደ። |
በለዓምም ከአምላክ ጋር በተገናኘ ጊዜ “ሰባቱን መሠዊያዎች በመደዳ አቁሜያቸዋለሁ፤ በእያንዳንዱም መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቅርቤያለሁ” አለው። |
ይሖዋም በበለዓም አፍ ላይ ይህን ቃል አስቀመጠ፦ “ወደ ባላቅ ተመለስና እንዲህ ብለህ ንገረው።” |
በመሆኑም በለዓም ተመለሰ፤ እሱም ባላቅን ከሞዓብ መኳንንት ሁሉ ጋር በሚቃጠለው መባው አጠገብ ቆሞ አየው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.