text stringlengths 4 267 |
|---|
ከዚያም ሙሴ ወጥቶ እነዚህን ቃላት ለመላው እስራኤል ተናገረ፤ |
እንዲህም አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ አሁን 120 ዓመት ሆኖኛል። ይሖዋ ‘የዮርዳኖስን ወንዝ አትሻገርም’ ስላለኝ ከእንግዲህ ልመራችሁ አልችልም። |
ከፊትህ የሚሻገረው አምላክህ ይሖዋ ነው፤ እሱ ራሱም እነዚህን ብሔራት ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ታባርራቸዋለህ። ልክ ይሖዋ በተናገረውም መሠረት እየመራ የሚያሻግርህ ኢያሱ ነው። |
ይሖዋ የአሞራውያንን ነገሥታት ሲሖንን እና ኦግን እንዲሁም ምድራቸውን ባጠፋ ጊዜ በእነሱ ላይ እንዳደረገው ሁሉ በእነዚህም ብሔራት ላይ እንዲሁ ያደርግባቸዋል። |
ይሖዋ እነሱን ድል ያደርግላችኋል፤ እናንተም እኔ በሰጠኋችሁ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት ታደርጉባቸዋላችሁ። |
ደፋርና ብርቱ ሁኑ። ከእናንተ ጋር የሚሄደው አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው ወይም በፊታቸው አትሸበሩ። እሱ አይጥላችሁም ወይም አይተዋችሁም።” |
ከዚያም ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በመላው እስራኤል ፊት እንዲህ አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤ ምክንያቱም ይህን ሕዝብ ይሖዋ ለአባቶቻቸው ሊሰጣቸው ወደማለላቸው ምድር የምታስገባው አንተ ነህ፤ ደግሞም ይህን ምድር ርስት አድርገህ ትሰጣቸዋለህ። |
በፊትህ የሚሄደው ይሖዋ ነው፤ እሱ ምንጊዜም ከአንተ ጋር ይሆናል። አይጥልህም ወይም አይተውህም። አትፍራ ወይም አትሸበር።” |
ከዚያም ሙሴ ይህን ሕግ ጽፎ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ለሚሸከሙት ሌዋውያን ካህናትና ለእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ሰጣቸው። |
ሙሴ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “በየሰባት ዓመቱ መጨረሻ፣ በዓመቱ ውስጥ ዕዳ በሚሰረዝበት በተወሰነው ጊዜ ላይ ማለትም የዳስ በዓል ሲከበር |
መላው እስራኤል አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በፊቱ በሚሰበሰብበት ጊዜ ይህን ሕግ እስራኤላውያን በሙሉ እንዲሰሙት አንብብላቸው። |
ስለ አምላካችሁ ስለ ይሖዋ ይሰሙና ይማሩ እንዲሁም እሱን ይፈሩ ዘንድ ብሎም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ እንዲፈጽሙ ሕዝቡን ማለትም ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ልጆችንና በከተሞችህ ውስጥ የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው ሰብስብ። |
ከዚያም ይህን ሕግ የማያውቁት ልጆቻቸው ይሰማሉ፤ እንዲሁም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ አምላካችሁን ይሖዋን መፍራት ይማራሉ።” |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ የምትሞትበት ጊዜ ቀርቧል። ኢያሱን ጥራውና መሪ አድርጌ እንድሾመው በመገናኛ ድንኳኑ ተገኙ።” በመሆኑም ሙሴና ኢያሱ ሄደው በመገናኛ ድንኳኑ ተገኙ። |
ከዚያም ይሖዋ በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ በድንኳኑ ላይ ተገለጠ፤ የደመናውም ዓምድ በድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆመ። |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ መሞትህ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚሄድበት ምድር በዙሪያው ካሉ ባዕዳን አማልክት ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ይፈጽማል። እኔንም ይተዉኛል፤ ከእነሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ። |
በዚያን ጊዜ ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል፤ እኔም እተዋቸዋለሁ፤ ሙሉ በሙሉ እስኪደመሰሱም ድረስ ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ። ከዚያም ብዙ መከራና ችግር ይደርስባቸዋል፤ እነሱም ‘ይህ ሁሉ መከራ የደረሰብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደል?’ ይላሉ። |
ሆኖም ወደ ሌሎች አማልክት ዞር በማለት ከፈጸሙት መጥፎ ድርጊት ሁሉ የተነሳ በዚያ ቀን ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ። |
“እንግዲህ አሁን ይህን መዝሙር ለራሳችሁ ጻፉ፤ ለእስራኤላውያንም አስተምሯቸው። ይህ መዝሙር በእስራኤል ሕዝብ ላይ ምሥክሬ ሆኖ ያገለግል ዘንድ እንዲማሩት አድርጉ። |
ምክንያቱም ለአባቶቻቸው ወደማልኩላቸው ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር በማስገባቸው ጊዜ በልተው ሲጠግቡና ሲበለጽጉ ወደ ሌሎች አማልክት ዞር ይላሉ፤ እንዲሁም እነሱን ያገለግላሉ፤ እኔንም ይንቁኛል፤ ቃል ኪዳኔንም ያፈርሳሉ። |
ብዙ መከራና ችግር በሚደርስባቸው ጊዜ ይህ መዝሙር ምሥክር ይሆንባቸዋል፤ (ምክንያቱም ዘሮቻቸው ይህን መዝሙር ሊዘነጉት አይገባም፤) እኔ እንደሆነ ወደማልኩላቸው ምድር ገና ሳላስገባቸው ምን ዓይነት ዝንባሌ እንዳዳበሩ አውቄአለሁ።” |
ስለዚህ ሙሴ ይህን መዝሙር በዚያን ቀን ጻፈው፤ እስራኤላውያንንም አስተማራቸው። |
እሱም የነዌን ልጅ ኢያሱን ሾመው፤ እንዲህም አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤ ምክንያቱም እስራኤላውያንን ወደማልኩላቸው ምድር የምታስገባቸው አንተ ነህ፤ እኔም ምንጊዜም ከአንተ ጋር እሆናለሁ።” |
ሙሴም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በመጽሐፍ ላይ ጽፎ እንደጨረሰ |
የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያኑን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ |
“ይህን የሕግ መጽሐፍ ወስዳችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አስቀምጡት፤ ይህም በዚያ በእናንተ ላይ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል። |
ምክንያቱም እናንተ ዓመፀኛና ግትር መሆናችሁን በሚገባ አውቃለሁ። እኔ ዛሬ ከእናንተ ጋር በሕይወት እያለሁ በይሖዋ ላይ እንዲህ ካመፃችሁ ከሞትኩ በኋላማ ምን ያህል ታምፁ! |
የነገዶቻችሁን ሽማግሌዎችና አለቆቻችሁን በሙሉ ሰብስቡልኝ፤ እኔም ጆሯቸው እየሰማ እነዚህን ቃላት ልናገር፤ ሰማይንና ምድርንም በእነሱ ላይ ምሥክሮች አድርጌ ልጥራ። |
ምክንያቱም እኔ ከሞትኩ በኋላ ክፉ ድርጊት እንደምትፈጽሙና ካዘዝኳችሁ መንገድ ዞር እንደምትሉ በሚገባ አውቃለሁ። በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ስለምትፈጽሙና በእጆቻችሁ ሥራ ስለምታስቆጡት ወደፊት መከራ ይደርስባችኋል።” |
ከዚያም ሙሴ መላው የእስራኤል ጉባኤ እየሰማ የዚህን መዝሙር ቃላት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ |
“አምላክህ ይሖዋ ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥህን ብሔራት፣ ይሖዋ በሚያጠፋቸውና አንተም እነሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው መኖር በምትጀምርበት ጊዜ |
አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ሦስት ከተሞችን ለይ። |
አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት የሚሰጥህን ምድር ሦስት ቦታ ከፋፍላት፤ እንዲሁም ነፍስ ያጠፋ ማንኛውም ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ መሸሽ እንዲችል መንገድ አዘጋጅ። |
“እዚያ ለመኖር ሸሽቶ የሄደን፣ ነፍስ ያጠፋ ሰው በተመለከተ መደረግ ያለበት ነገር ይህ ነው፦ ለባልንጀራው የቆየ ጥላቻ የሌለው አንድ ሰው ሳያስበው ባልንጀራውን መትቶ ቢገድለው፣ |
ለምሳሌ ከባልንጀራው ጋር እንጨት ለመቁረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፣ ዛፉንም ለመቁረጥ መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ላይ ወልቆ ባልንጀራውን ቢመታውና ቢገድለው ነፍሰ ገዳዩ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል። |
አለዚያ በንዴት የበገነው ደም ተበቃይ ከተማዋ ሩቅ ከመሆኗ የተነሳ ነፍሰ ገዳዩን አሳዶ ሊደርስበትና ሊገድለው ይችላል። ይሁን እንጂ ይህ ሰው ለባልንጀራው የቆየ ጥላቻ ስለሌለው መሞት አይገባውም። |
‘ሦስት ከተሞችን ለይ’ በማለት ያዘዝኩህ ለዚህ ነው። |
“አምላክህ ይሖዋ ለአባቶችህ በማለላቸው መሠረት ግዛትህን ሲያሰፋልህና ለእነሱ ለመስጠት ቃል የገባላቸውን ምድር በሙሉ ሲሰጥህ |
ይኸውም አምላክህን ይሖዋን እንድትወድና ዘወትር በመንገዶቹ እንድትሄድ እኔ ዛሬ የማዝህን ይህን ትእዛዝ ሁሉ በመጠበቅህ ግዛትህን ሲያሰፋልህ ከእነዚህ ሦስት ከተሞች በተጨማሪ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትለያለህ። |
ይህም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ንጹሕ ደም እንዳይፈስና በደም ዕዳ ተጠያቂ እንዳትሆን ነው። |
“ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፣ አድብቶም ለሞት የሚያበቃ ጉዳት ቢያደርስበትና ሰውየው ቢሞት፣ ገዳዩም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ ቢሸሽ |
የሚኖርበት ከተማ ሽማግሌዎች ሰውየውን ከዚያ በማስመጣት ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት፤ ይህ ሰው ሞት ይገባዋል። |
አትዘንለት፤ መልካም እንዲሆንልህ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የሚመጣን በደል ከእስራኤል አስወግድ። |
“አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ርስትህን በምትቀበልበት ጊዜ የቀድሞ አባቶችህ የከለሉትን ወሰን በማለፍ የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንካ። |
“አንድ ሰው የትኛውንም ስህተት ወይም የትኛውንም ኃጢአት ቢፈጽም ግለሰቡን ጥፋተኛ ለማድረግ አንድ ምሥክር አይበቃም። ጉዳዩ የሚጸናው ሁለት ምሥክሮች ወይም ሦስት ምሥክሮች በሚሰጡት የምሥክርነት ቃል ነው። |
ተንኮል ያሰበ አንድ ምሥክር አንድን ግለሰብ የሆነ በደል ፈጽሟል በማለት ቢመሠክርበት |
ክርክር የገጠሙት ሁለቱ ሰዎች በይሖዋ ፊት፣ በካህናቱና በዚያን ጊዜ ዳኛ ሆነው በሚያገለግሉት ሰዎች ፊት ይቆማሉ። |
ዳኞቹም ጉዳዩን በጥንቃቄ ይመረምራሉ፤ ምሥክሩ ሐሰተኛ ምሥክር ከሆነና ወንድሙን የወነጀለው በሐሰት ከሆነ |
በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያቀደውን ነገር በራሱ ላይ አድርጉበት፤ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ። |
ሌሎችም ይህን ሲሰሙ ይፈራሉ፤ በመካከልህም እንዲህ ያለ መጥፎ ነገር ፈጽሞ ዳግመኛ አያደርጉም። |
አዘኔታ አታሳይ፤ ሕይወት ስለ ሕይወት፣ ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፣ እጅ ስለ እጅ እንዲሁም እግር ስለ እግር ይሁን። |
የእውነተኛው አምላክ ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት እስራኤላውያንን የባረካቸው በረከት ይህ ነው። |
እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ከሲና መጣ፤ከሴይርም ሆኖ አበራባቸው። ከፋራን ተራራማ አካባቢዎችም በክብር አበራ፤ከእሱም ጋር አእላፋት ቅዱሳን ነበሩ፤በቀኙም ተዋጊዎቹ አሉ። |
እሱ ሕዝቡን ይወዳል፤ቅዱስ የሆነው ሕዝብ ሁሉ እጅህ ውስጥ ነው። እነሱም እግርህ ሥር ተቀምጠዋል፤ቃልህንም ይሰማሉ። |
(ሙሴ ትእዛዝን ይኸውም ሕግን ሰጠን፤ይህም ለያዕቆብ ጉባኤ እንደ ርስት ነው።) |
የሕዝቡ መሪዎች ከመላው የእስራኤል ነገድ ጋርአንድ ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ፣አምላክ በየሹሩን ላይ ንጉሥ ሆነ። |
ሮቤል በሕይወት ይኑር፣ አይሙት፤የወገኖቹም ቁጥር አይቀንስ።” |
ይሁዳንም እንዲህ ሲል ባረከው፦ “ይሖዋ ሆይ፣ የይሁዳን ድምፅ ስማ፤ወደ ሕዝቦቹም መልሰህ አምጣው። እጆቹ የእሱ ለሆነው ይከላከላሉ፤አንተም ጠላቶቹን እንዲዋጋ እርዳው።” |
ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ “የአንተ ቱሚምና ኡሪም ለአንተ ታማኝ ለሆነ፣በማሳህ ለፈተንከው ሰው ይሆናል፤ በመሪባ ውኃዎች አጠገብ ተጣላኸው፤ |
ሰውየው አባቱንና እናቱን በተመለከተ ‘ስለ እነሱ ግድ የለኝም’ አለ። ሌላው ቀርቶ ወንድሞቹን እንኳ አልተቀበለም፤የገዛ ልጆቹንም ችላ አለ። ቃልህን ታዘዋልና፤ቃል ኪዳንህንም ጠብቀዋል። |
ለያዕቆብ ድንጋጌህን፣ለእስራኤልም ሕግህን ያስተምሩ። ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሸትህ ዕጣን ያቅርቡልህ፤በመሠዊያህም ላይ ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባ ይሠዉልህ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ጉልበቱን ባርክለት፤በእጆቹም ሥራ ደስ ይበልህ። እሱን የሚጠሉት ዳግመኛ እንዳያንሰራሩበእሱ ላይ የሚነሱትን እግራቸውን አድቅቅ።” |
ስለ ቢንያም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ የወደደው ያለስጋት አብሮት ይኑር፤ቀኑን ሙሉ ይከልለዋልና፤በትከሻዎቹም መካከል ይኖራል።” |
ስለ ዮሴፍ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ከሰማይ በሚወርዱ ምርጥ ነገሮች፣በጤዛና ከታች በሚመነጩ ውኃዎችምድሩን ይባርክ፤ |
እንዲሁም ፀሐይ በምታስገኛቸው ምርጥ ነገሮች፣በየወሩ በሚገኝ ምርጥ ፍሬ፣ |
ጥንታዊ ከሆኑ ተራሮች በሚገኙ ምርጥ ነገሮች፣ጸንተው ከሚኖሩት ኮረብቶች በሚገኙ ምርጥ ነገሮች፣ |
ከምድር በሚገኙ ምርጥ ነገሮችና ምድርን በሞሉ ምርጥ ነገሮች፣በቁጥቋጦው ውስጥ በተገለጠው በእሱ ሞገስ ይባርክ። እነዚህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ፣ከወንድሞቹ መካከል ተነጥሎ በወጣው አናት ላይ ይውረዱ። |
ግርማው እንደ በኩር በሬ ነው፤ቀንዶቹም የዱር በሬ ቀንድ ናቸው። በእነሱም ሰዎችን፣ሕዝቦችን ሁሉ እስከ ምድር ዳርቻ ይገፋል። እነሱ የኤፍሬም አሥር ሺዎች ናቸው፤የምናሴም ሺዎች ናቸው።” |
ስለ ዛብሎን እንዲህ አለ፦ “ዛብሎን ሆይ፣ በመውጣትህ ደስ ይበልህ፤አንተም ይሳኮር፣ በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ። |
ሰዎችን ወደ ተራራው ይጠራሉ። በዚያም የጽድቅ መሥዋዕቶችን ያቀርባሉ። ምክንያቱም በባሕሮች ውስጥ ካለው የተትረፈረፈ ሀብት፣በአሸዋም ውስጥ ተሰውሮ ከተከማቸው ነገር ዝቀው ያወጣሉ።” |
ስለ ጋድ እንዲህ አለ፦ “የጋድን ድንበሮች የሚያሰፋ የተባረከ ነው። በዚያ እንደ አንበሳ ይተኛል፤ክንድን፣ አዎ አናትን ለመዘነጣጠል ተዘጋጅቶ ይጠብቃል። |
የመጀመሪያውን መርጦ ለራሱ ይወስዳል፤በዚያ የሕግ ሰጪው ድርሻ ተለይቶ ተቀምጧልና። የሕዝቡ መሪዎች አንድ ላይ ይሰበሰባሉ። የይሖዋን ጽድቅና ድንጋጌዎች፣በእስራኤል ያስፈጽማል።” |
ስለ ዳን እንዲህ አለ፦ “ዳን የአንበሳ ደቦል ነው። ከባሳን ዘሎ ይወጣል።” |
ስለ ንፍታሌም እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በይሖዋ ሞገስ ረክቷል፤በእሱም በረከት ተሞልቷል። ምዕራቡንና ደቡቡን ውረስ።” |
ስለ አሴር እንዲህ አለ፦ “አሴር በልጆች የተባረከ ነው። በወንድሞቹ ፊት ሞገስ ያግኝ፤እግሩንም ዘይት ውስጥ ይንከር። |
የበርህ መቀርቀሪያ ብረትና መዳብ ናቸው፤በዘመንህ ሁሉ ያለስጋት ትኖራለህ። |
አንተን ለመርዳት በሰማይ ውስጥ የሚጋልብ፣በግርማው በደመና ላይ የሚገሰግስ፣እንደ እውነተኛው የየሹሩን አምላክ ያለ ማንም የለም። |
አምላክ ከጥንት ጀምሮ መሸሸጊያ ነው፤ዘላለማዊ ክንዶቹ ከበታችህ ናቸው። ጠላትን ከፊትህ ያባርራል፤እንዲሁም ‘አጥፋቸው!’ ይላል። |
እህልና አዲስ ወይን ባለበት ምድር፣ሰማያቱ ጠል በሚያንጠባጥቡበትእስራኤል ያለስጋት ይቀመጣል፤የያዕቆብም ምንጭ የተገለለ ይሆናል። |
እስራኤል ሆይ፣ ደስተኛ ነህ! የይሖዋን ማዳን ያየ፣እንደ አንተ ያለ ሕዝብ ማን አለ?እሱ የሚከልል ጋሻህናታላቅ ሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፤አንተም በጀርባቸው ላይ ትራመዳለህ።” |
“አንተም አምላክህን ይሖዋን ውደድ፤ ለእሱ ያለብህንም ግዴታ ምንጊዜም ተወጣ፤ እንዲሁም ደንቦቹን፣ ድንጋጌዎቹንና ትእዛዛቱን ሁልጊዜ ጠብቅ። |
ዛሬ እየተናገርኩ ያለሁት ለእናንተ እንጂ የአምላካችሁን የይሖዋን ተግሣጽ፣ የእሱን ታላቅነት፣ የእሱን ብርቱ እጅና የተዘረጋ ክንድ ላላወቁት ወይም ላላዩት ለልጆቻችሁ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። |
እነሱ በግብፅ ይኸውም በግብፁ ንጉሥ በፈርዖን ፊትና በመላው ምድሩ ላይ ያሳየውን ተአምራዊ ምልክትም ሆነ ያደረገውን ነገር አልተመለከቱም፤ |
ወይም እናንተን እያሳደዱ ሳሉ በቀይ ባሕር ውስጥ በሰጠሙት በግብፅ ሠራዊት፣ በፈርዖን ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች ላይ ያደረገውን አላዩም፤ ይሖዋም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጠፋቸው። |
እናንተ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን ነገር አልተመለከቱም፤ |
ወይም ደግሞ የሮቤል ልጅ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንን እና አቤሮንን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ ድንኳኖቻቸውንና ከእነሱ ጋር ያበረውን ማንኛውንም ሕያው ፍጡር እስራኤላውያን ሁሉ እያዩ ምድር ተከፍታ በዋጠቻቸው ጊዜ በእነሱ ላይ ያደረገውን ነገር አልተመለከቱም። |
እናንተ፣ ይሖዋ ያደረጋቸውን ታላላቅ ሥራዎች በሙሉ በገዛ ዓይናችሁ አይታችኋል። |
“ብርታት እንድታገኙና ወደምትወርሷት ምድር ተሻግራችሁ እንድትገቡ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ፤ |
ይሖዋ ለአባቶቻችሁና ለዘሮቻቸው ለመስጠት በማለላቸው ወተትና ማር በምታፈሰው ምድር ላይ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም እነዚህን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ። |
“የምትወርሳት ምድር ዘር ትዘራባት እንዲሁም ልክ እንደ አትክልት ስፍራ በእግርህ በመስኖ ታጠጣት እንደነበረችው እንደወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም። |
ከዚህ ይልቅ ተሻግራችሁ የምትወርሷት ምድር ተራሮችና ሸለቋማ ሜዳዎች ያሉባት ምድር ናት። የሰማይን ዝናብ የምትጠጣ ምድር ናት፤ |
አምላክህ ይሖዋ የሚንከባከባት ምድር ናት። የአምላክህም የይሖዋ ዓይን ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ መጨረሻው ድረስ ዘወትር በእሷ ላይ ነው። |
“እኔ ዛሬ የማዛችሁን ትእዛዛቴን በትጋት ብትፈጽሙ፣ አምላካችሁን ይሖዋን ብትወዱት እንዲሁም በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ ብታገለግሉት፣ |
እኔ ደግሞ ለምድራችሁ በወቅቱ ዝናብን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እሰጣለሁ፤ አንተም እህልህን፣ አዲስ የወይን ጠጅህንና ዘይትህን ትሰበስባለህ። |
ለእንስሶችህም በሜዳህ ላይ ዕፀዋት አበቅልልሃለሁ፤ አንተም በልተህ ትጠግባለህ። |
ልባችሁ እንዳይታለልና ዞር ብላችሁ ሌሎች አማልክትን እንዳታመልኩ እንዲሁም እንዳትሰግዱላቸው ተጠንቀቁ። |
አለዚያ የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ ዝናብ ዘንቦ ምድሪቱ ምርት እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም ይሖዋ ከሚሰጣችሁ መልካም ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ። |
“እነዚህን ቃሎቼን በልባችሁና በነፍሳችሁ ላይ አትሟቸው፤ በእጃችሁም ላይ እንደ ማስታወሻ እሰሯቸው፤ በግንባራችሁም ላይ እንደታሰረ ነገር ይሁኑ። |
በቤታችሁ ስትቀመጡ፣ በመንገድ ላይ ስትሄዱ፣ ስትተኙና ስትነሱ ስለ እነሱ በመናገር ለልጆቻችሁ አስተምሯቸው። |
በቤታችሁ መቃኖችና በግቢያችሁ በሮች ላይ ጻፏቸው፤ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.